Wednesday, 19 August 2026 19:40

የደራሲያን ፊርማ ያረፈባቸው 2,652 መጻሕፍት፡ የጊነስ ክብረ ወሰን!

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለሥነ-ጽሑፍ የነበራት ፍቅር ያስገኘላት ድል! ቪዮሌታ ሳዶቭስካ የተባለች ፖላንዳዊት ብሎገር፤ በደራሲያን እጅ የተፈረሙ 2,652 መጻሕፍትን በመሰብሰብ የዓለም ትልቁ ስብስብ ባለቤት በመሆን በጊነስ የዓለም መዝገብ ላይ ሰፍራለች። ከልጅነቷ ጀምሮ የጀመረችው ይህ የመጽሐፍ ማሰባሰብ ጉዞ አሁን ላይ ከ43 እስከ 65 ሚሊዮን ብር የሚገመት ውድ ቤተ-መጻሕፍትን ባለቤት አድርጓታል።

ይህ አስደናቂ ስብስብ ከጓደኞቿ፣ ከአታሚዎች እና በፖስታ ከተላኩላት ስጦታዎች የተሰበሰበ ነው። ቪዮሌታ ይህ ስኬት የሀገሯን የማንበብ ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ብርታት እንደሆናት ገልጻ፣ ቀጣይዋ ትልቅ ሕልም የታዋቂውን ደራሲ ስቲቨን ኪንግን የተፈረመ መጽሐፍ ማግኘት እንደሆነ ተናግራለች።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 4867 times