Thursday, 27 August 2026 10:44

ደጉ…ባለ አገሩ !!!!

Written by 
Rate this item
(0 votes)
የጎጃም ገበሬ ልጁ ተመርቆ በመምጣቱ በግቢው ዳስ ተጥሎ….
አባወራው! ኩታ እንደ ደረበ ሽክናውን ጨብጦ… ከእንግዶቹ ጋር እየተጫወተ …ባለቤቱን ያስተውላል፡፡ እሷ እንጀራ በእንቅብ አሲዛ በየገበታው እየዞረች፣ ብሉ እንጂ በሞቴ እያለች ገበታው ሳይጉድል እንጀራ እያጠፈች በመጨመር ትጋብዛለች፡፡
አረፍ ብላ ደሞ ጠላ በትልቅ መንቆርቆሪያ እያዞረች ጠጡ እንጂ እያለች በየሽክናው በመቅዳት ትሞላለች፣ መቺም ከፈገግታዋ ጋር ጥለት ቀሚሶን በአንድ እጆ ሰብሰብ አድርጋ፣ በእንግዶች ማሃል እየዞረች ብሉ እንጂ ጠጡ እንጂ በሞቴ እያለች፡ ግብዣው ሰምሮላት ዳሱን ሙሉ እየዞረች ያለ እረፍት እየጋበዘች ትፍነከነካለች፡፡
አባወራው የጎተራው መጉደል …..የሚስቱ ልግስናን ታዝቦ!!!!
አያ በሪ ሆይ!! …አያ በሪ ሆይ!!! እኛ በደከም-ነው!
ሴቱ ይፉልላል……በየግብዣው ላይ!!! አለ ይባላል፡፡
እድምተኛው…እንደ ባህል...ወጉ ይመርቃል፡፡
በልጉ ………ይስመርለት
አዝመራው……..ያሽትለት
ጎተራው……….ይሙላለት
ማሪቱ………..ወለላይቱ
ማጀቷ ……..አይጉደ ልባት
ልጁን………..ይባርክላት
አገር/ወገን ሰላማ ውሎ ሰላም ይደር!!! እያለ
ከዳስ ሲወጣ ኩታውን እያጣፉ፣ ሽመሉን ከትከሻው ጣል አርጎ፣ ሳይመሽ…ከመንደሩ ለመድረስ…ወጉን እያወጋ ከርምጃው ፈጠን እያለ ዳገት ቁልቁለቱን ይዘልቀዋል፡፡
ደጉ…ባለ አገሩ !!!!
አፈወርቅ-
ምንጭ:- Kibru Books የቴሌግራም ቻናል
Read 2015 times