Thursday, 27 August 2026 12:41

አንጋፋው ድምጻዊ መሐሙድ አህመድ የመጨረሻውን አልበሙን ሊያቀርብ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ አርአያ የሆነው የክብር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አህመድ፤ የኪነ ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ሥራ የሆነውን እና ለትውልድ የሚሻገር አዲስ የሙዚቃ አሻራ ለማስቀመጥ ያዘጋጀውን 26ኛ አልበሙን በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስተዋውቋል። "ለታሪክ" የተሰኘው ይህ አልበም የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶችና ወጎች ከአዲሱ ትውልድ ጋር ለማገናኘት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችንና ባህላዊ ቅኝቶችን በማቀናጀት በፍቅር፣ በሀገርና በማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮሩ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ዜማዎችን አካትቷል።

አልበሙ በይፋ ከመለቀቁ በፊት በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ የሚለቀቅ ሲሆን፣ ሙሉው አልበም በመስከረም አጋማሽ በስፖቲፋይ፣ አፕል ሙዚክ፣ ዩቲዩብ እና በሌሎችም ዲጂታል መድረኮች ለአድማጮች ይደርሳል። ይህንን ታሪካዊ ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚያሰራጨው የሙዚቃ ኩባንያ ጋር በአጋርነት የሚያስተባብረው "ይሳቃል ኢንተርቴይመንት" መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አርቲስቱ አዲሱ ትውልድ የሀገርን ባህልና ቅኝት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 2918 times