የደባርቅ ከተማን የቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግና ጽዱ፣ ውብ እንዲሁም ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የበርካታ ወገኖችን ድጋፍና ትብብር በማግኘት ላይ ይገኛል። ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ተገኝተዋል። በዚህ ታላቅ መድረክ በጥሬ ገንዘብና በአይነት ከ450 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን፣ የሃብት ማሰባሰብ ሂደቱ አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዚሁ መድረክ ታዋቂ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ከፍተኛ አጋርነታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ፍቅሬ 20 ሚሊዮን ብር፣ አቶ በላይነህ ክንዴ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢአይካ (BIKA) 15 ሚሊዮን ብር በመለገስ ግንባር ቀደም ተሳትፎ አድርገዋል። ይህ የልማት እንቅስቃሴ ደባርቅን በቱሪዝም፣ በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት ሲሆን፣ በቀጣይም ነዋሪዎችንና የከተማዋን ወዳጆች ያካተተ ሰፊ የልማት ምዕራፍ እንደሚቀጥል የከተማዋ ልማት ኮሚቴ አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Tuesday, 01 September 2026 13:15
የደባርቅ ከተማ የኮሪደር ልማት ከ450 ሚ. ብር በላይ ድጋፍ አገኘ
Written by Administrator
Published in
ዜና

