Thursday, 17 September 2026 11:29

“ኢሬቻ በአንጻራዊነት“ የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
በሃይለሚካኤል ታደሰ የተዘጋጀው እና "ኢሬቻ"ን ከባህል፣ ከሃይማኖት እና ከሰብአዊ መብት አንጻር በጥልቀት የሚዳስሰው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ ባለ 547 ገጾች እና 6 አጠቃላይ ምዕራፎች ያሉት ሲሆን፤ አምና በአፋን ኦሮሞ ከወጣው 'Irreecha Bir-qabaan' መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦችን ጨምሮ በርካታ ተጨማሪ ጥናታዊ ይዘቶችን አካትቷል።
ደራሲው በመጀመሪያው ምዕራፍ የኦሮሞን ባህላዊ በዓላት ከክርስትና እና ከአፍሪካ ሀገር በቀል በዓላት ጋር በማነጻጸር፣ የሚሰዋውን መሥዋዕትነት እና የበዓላትን ሕጋዊ መብት በኢፌዴሪ ሕገመንግሥትና በሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች መሠረት በስፋት ይተነትናል። ሁለተኛውና ሦስተኛው የምዕራፍ ክፍሎች የኢሬቻን አመጣጥ፣ አራት የተለያዩ ትርጉሞች፣ እንዲሁም በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ዘመነ ጽጌ ድረስ የሚከበርባቸውን የመንጻት፣ የስርየት እና የመታደስ ምዕራፎች ከአፍሪካ ፍልስፍና እና ከክርስትና ነገረ መለኮት ጋር በማቀናጀት ያቀርባል።
በተጨማሪም አራተኛውና አምስተኛው ምዕራፎች ስለ ውኃ (የወላቡ፣ የሆራ፣ የወንዝ) እና ስለ ተራራ (ኢሬቻ ቱሉ) ያላቸውን መንፈሳዊና ባህላዊ ትርጉም ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከአፍሪካ አረዳድ አንጻር በሰፊው ያነጻጽራሉ። በመጨረሻም ስድስተኛው ምዕራፍ ኢሬቻን ከአውሮፓ የሳተርናሊያ በዓል፣ ከኢትዮጵያ የእሸት በዓላት፣ እንዲሁም ከክርስትና እምነት እንደ ጥምቀት፣ ትንሣኤ እና የጸደይ/የአበባ በዓላት ጋር በማወዳደር ይመረምራል። መጽሐፉ ሲጠቃለል "ምንተ ንግበር?" በሚል ጥያቄ መደረግ ያለባቸውን 14 ተግባሮች ይዘረዝራል።
መጽሐፉን:
1. ከጃፋር መጻሕፍት መደብር፣
2. አአዩ አራት ኪሎ ካምፓስ ፊለፊት በሚገኘው የገበያ ማዕከል ውስጥ ባለ የኦሮሞ ምርምር ማኀበር ሱቅ እና
3.በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፊለፊት በሚገኘው የመጻሕፍት መደብር እና
4. ከቢርቢርሰ ጎሮ ጊዮርጊስ ወደ ደጃች ውቤ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ በሚገኘው ኢሉ መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 7236 times