Friday, 18 September 2026 09:44

የዓለማችን ቁጥር 1 ባለጸጋ ሴት - አሊስ ዋልተን

Written by 
Rate this item
(2 votes)

* ሃብቷ ከብዙ አገራት ዓመታዊ ገቢ ይልቃል !

አሊስ ዋልተን የተባለችው የዎልማርት መስራች ብቸኛ ሴት ልጅ፣ በ2026 ዓ.ም የሀብት መጠንዋ ወደ 118 ቢሊዮን ዶላር በመድረስ ከብዙ አገራት ዓመታዊ ገቢ በላይ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ፎርብስ እንዳረጋገጠው፣ አሊስ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚዋ የምድራችን ሀብታም ሴት ናት።

ሀብቷ ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ በመሻገርም ብቸኛዋ የአሜሪካ ሴት ሴንቲቢሊየነር ሆናለች። የዎልማርት አክሲዮኖች ከ10 በመቶ በላይ በማደጉ የሷም ሀብት በዚሁ ዓመት በፍጥነት
አሻቅቧል።

ዋልተን ከወንድሞቿ በተለየ መልኩ የጥበብ ሙዚየም የገነባች ሲሆን በአርካንሳስም የሕክምና ትምህርት ቤት መገንባት ጀምራለች። ይህም ግዙፍ ሀብት ባህልንና ትምህርትን እንዴት መለወጥ እንደሚችል ያሳያል ተብሏል።

Read 16351 times