ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ የምትታወቀው ድምፃዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ፣ አራተኛውን አዲስ አልበም ልታወጣ መሆኑ ተነገረ። ቀደም ሲል "እወደሀለሁ"፣ "አታላይ" እና "ብር ብር" የመሳሰሉ ተወዳጅ ዘፈኖችን ለአድናቂዎቿ ያደረሰችው አርቲስቷ፣ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ታላላቅ ሽልማቶችን በማግኘት ቀዳሚ መሆኗ ይታወሳል።
መስከረም 16 ቀን 2019 የሚወጣው አዲሱ አልበም 10 ውብ ሙዚቃዎችን የያዘ ሲሆን፣ ከአልበሙ ውስጥ አንድ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮም እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና

