Tuesday, 29 September 2026 08:24

አሜሪካ ለመካከለኛው ምስራቅ ያወጣችው ገንዘብ አፍሪካን ከአንድ ዓመት ረሃብ መታደግ ይችል ነበር

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስፑትኒክ የተባለው የዜና ተቋም ባወጣው ትንተና መሠረት፤ አሜሪካ ለመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ያወጣችው ግዙፍ ገንዘብ በአፍሪካ ለአንድ ሙሉ ዓመት የሚሆን የረሃብ አደጋን መታገል የሚያስችል ነበር። የአሜሪካ ኮንግረስ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ አሜሪካ እስከ ሐምሌ 25 ድረስ ብቻ 38 ቢሊዮን ዶላር ያወጣች ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ባሉት ወራትም በየወሩ ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወጪ አድርጋለች።

በሌላ በኩል የተመድ የእርሻና ምግብ ድርጅት የሩሲያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ኦሌግ ኮቢያኮቭ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፣ በአፍሪካ ረሃብን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እስከ 2030 ድረስ በየዓመቱ ከ39 እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ረሃብን በድጋሚ ለማጥፋት በየዓመቱ 267 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ትልቁ የድጋፍ ድርሻ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ይገባል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 2022 times