Tuesday, 29 September 2026 08:26

በእሬቻ ዋዜማ የሚጠበቀው ታሪካዊ የቦክስ ውድድር

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በእሬቻ በዓል ዋዜማ የኢትዮጵያን የቦክስ ስፖርት ለማሳደግ ታላቅ ውድድር ሊካሄድ ነው። አፍሮኮ ትሬዲንግና ኤች ኬ ኢንተርቴመንት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ፣ ከፌዴራልና ከኦሮሚያ ክለቦች የተውጣጡ 16 ቦክሰኞች በሰባት የወንዶች እና በአንድ የሴቶች ጨዋታዎች ይፋለማሉ።
ይህ ውድድር ዐርብ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ የሚጀምር ሲሆን እስከ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል። በዕለቱ ከሚደረጉት ጠንካራ ፍልሚያዎች መካከል በ80 ኪሎ እና በ57 ኪሎ ግራም የሚካሄዱት ጨዋታዎች ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው ሲሆን፣ አሸናፊዎችም ቀበቶ እንደሚሸለሙ ተገልጿል፤ ተመልካቾችም ቲኬቶቻቸውን በአዋሽ ባንክ በኩል ማግኘት ይችላሉ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 3636 times