Monday, 05 October 2026 08:12

ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ድሮው የቃል ፈተና እየተመለሱ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
በርካታ ትምህርት ቤቶች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተጠቅመው የቤት ሥራ የሚሠሩ ተማሪዎችን ለመቆጣጠር አዲስ ዘዴ እየተጠቀሙ ነው። ኮሌጆች በአሁኑ ወቅት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚጻፉ ፍጹም የሚመስሉ ድርሰቶች መበራከታቸውን ይናገራሉ፤ ነገር ግን ብዙ ተማሪዎች የሠሩትን ሥራ በራሳቸው አብራርተው ለማቅረብ ይቸገራሉ።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች መልሶቻቸውን በአካል ቀርበው እንዲከላከሉ የሚያስገድዷቸውን የቃል ፈተናዎች (Oral Exams) እየመለሱ ይገኛሉ። ከጽሑፍ ሥራዎች በተለየ, እነዚህ ፈተናዎች በቦታው ላይ ሆነን ማሰብን ስለሚጠይቁ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ብቻ ጥገኛ መሆንን ፈጽሞ አዳጋች ያደርጉታል።
አስተማሪዎች እንደሚሉት የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማ ማጭበርበርን ማስቆም ብቻ ሳይሆን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ውስጥ ተማሪዎች የራሳቸውን የማሰብ ችሎታ፣ ፈጠራና የመግባቢያ ክህሎት እንዲያዳብሩ መርዳት ነው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 10394 times