Tuesday, 13 October 2026 06:33

የፖለቲካ ዝርፊያ በትግራይ (የግል ምልከታ እንደወረደ)

Written by 
Rate this item
(4 votes)
ትግራይ ላይ መንጠንቀቅ አለብን። እንደ አገር የኢትዮጵያ ራስ ነው። የፕሌቶን የሰው ~ መንግስት ሞዴል ከተከተልን (????) ትግራይ ለኢትዮጵያ አንገት ናት። ጉሮሮ ናት። ???? ትግራይ እጃችን ትከሻችን ክንዳችን ናት። ስለዚህ በብዙ መንገድ መጠንቀቅ አለብን። ግን የሚያሳስበን ነገር ደሞ አለ። በአሁኑ ሰአት አሳሳቢው ነገር በትግራይ የፖለቲካ ዝርፊያ እየተከናወነ ስለሆነ የተከበረው የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ።
በትግራይ ሁለት አይነት ዘረፋ እያየን ነው። የህዝብን ጥቅም የሚጎዳ፣ ለውጡን የሚቀለብስ የለየለት ዘረፋ ነው። አንደኛው የኤኮኖሚ ዘረፋ ነው። ጦርነቱን ተክትሎ ጁንታው ሲሸሽ ሱቅ፣ የህዝብ ሀብት ወዘተ ሲዘረፍ ነው ያየነው። ይሄ የኤኮኖሚ ዘረፋ ነው። የፖለቲካ ዘረፋ ደግሞ አለ። በህዝብ ስም የህዝብ ስልጣን መንጠቅ፣ የስልጣን ዘረፋ ፣ በየወረዳው በየቀጠናው የሚታየው የስልጣን ቅርምት ሊባል የሚችለው የፖለቲካ ዝርፊያ ነው። ከዚህ ውጪ ስም ካለው እንነጋገር ፣ በተባለው ከተስማማን ደግሞ ችግሩን ለማስተካከል እንረባረብ።
Blilign Habtamu Ababu-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 7398 times