ኢሉሚ ማዳ (ዲጄ ኢሉ) በ6 ዓመት ከ99 ቀን ዕድሜዋ የዓለም ትንሿ ሴት ዲጄ በመሆን የጊነስ የዓለም ሪከርድ አስመዝገበች። ሪከርዱን ለመስበር በጃፓን ዮኮሃማ ከተማ በሚገኝ ክለብ ውስጥ ከአንድ ሰዓት በላይ ሙዚቃ አቅርባለች።
ሙዚቃ ሰዎችን ከሐዘን መልሶ የማስደሰት ኃይል እንዳለው የምታምነው ዲጄ ኢሉ፤ በከባድ ጊዜያት ሰዎችን በሙዚቃዋ መርዳት ትፈልጋለች።
ለወደፊት በዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ ማቅረብ፣ አዳዲስ ሪከርዶችን መስበር እና የዲጄ ሙዚቃ የሚለቀቅበት የራሷን አይስክሬም ሱቅ መክፈት ግቦቿ መሆናቸውን ተናግራለች።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና

