Wednesday, 21 October 2026 07:03

ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ "ደከመኝ ኩርፊያው" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ሊለቅ ነው

Written by 
Rate this item
(2 votes)
ተወዳጁ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን በጉጉት ሲያስጠብቅ የቆየበትን "ደከመኝ ኩርፊያው" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ይዞ ብቅ ሊል ነው። ድምፃዊው ይህንን አዲስ የሙዚቃ ስራውን በመጪው አርብ ለአድማጮቹ እንደሚያበረክት አስታውቋል።
የጎሳዬን ተወዳጅ የድምፅ ቃና ዳግም ወደ አድማጭ ጆሮ በሚያመጣው በዚህ አዲስ ስራ ላይ፤ የግጥም ድርሰቱን ሀብታሙ ቦጋለ ሲያበረክት፣ የዜማውን ድርሰት ደግሞ ራሱ ድምፃዊው ጎሳዬ ተስፋዬ በሚገባ ሰርቶታል።
አርቲስቱ እንዳረጋገጠው፤ በጉጉት እየተጠበቀ የሚገኘው ይህ አዲስ ነጠላ ዜማ በመጪው አርብ 12:00 ሰዓት አመሻሹን በራሱ ይፋዊ የዩቱብ ገጽ በኩል በቀጥታ ለህዝብ ክፍት ይደረጋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 8334 times