Wednesday, 28 October 2026 06:31

አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ 7 የቀድሞ ዲፕሎማቶች ለማርኮ ሩቢዮ ደብዳቤ ጻፉ

Written by 
Rate this item
(2 votes)
"ተገንጣይ በሚል ፍረጃ የኢትዮጵያ ችግር አይፈታም"
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸውን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስንና አምባሳደር ፍስሃ አስገዶምን ጨምሮ ሰባት የቀድሞ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ በቅርቡ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ቡድኖች "ተገንጣይ" ሲሉ የሰጡትን መግለጫ በመተቸት ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደብዳቤ ልከዋል።
ዲፕሎማቶቹ በደብዳቤያቸው እንደገለጹት፤ ይህ የሩቢዮ ፍረጃ የሀገሪቱን ውስብስብ የፖለቲካና የጸጥታ እውነታ አቅልሎ የሚያቀርብና የችግሩን ሥረ-መሠረት የሚሸፍን በመሆኑ፣ አሜሪካ ጉዳዩን በጥልቀት ልትመረምረው ይገባል።
መንግሥትን መቃወምና የፖለቲካ ጥያቄ ማቅረብ ከተገንጣይነት ተለይቶ ካልታየ የግጭቱ ዋና ምክንያቶች ሊሸፋፈኑና ገንቢ ድርድር የማድረግ ዕድሎች ሊዘጉ እንደሚችሉ የጠቆሙት የቀድሞ ዲፕሎማቶቹ፣ ዋሽንግተን ሚዛናዊና መርህ ላይ የተመሠረተ አካሄድ እንድትከተል አሳስበዋል። በተጨማሪም አሜሪካ ለሲቪሎች ደኅንነትና ተጠያቂነት ወጥ የሆኑ መስፈርቶችን እንድትከተልና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለአካታች የፖለቲካ ውይይት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
Wazema-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 5115 times