Wednesday, 28 October 2026 06:34

መሬትም ባንክም ታንክም የያዘ አካል ውንብድናን ማሸነፍ ማክሸፍ ሊያቅተው አይችልም

Written by 
Rate this item
(35 votes)
ውስብሰብ ያለ ነገር ግን እጅግ ጠንካራ አደረጃጀት የነበረው አንድ የማፊያ ቡድን ነበር አሉ አዲስ አበባ ውስጥ። መዋቅሩ እስከ መንግሥት ኃላፊዎች የተዘረጋና ለብዙ ዓመታት ፈርጥሞ የቆየ እንደነበር ነው የተገለጸው።
ለራሱም ሆነ ለሌሎች ተቀጥሮ የፈለገውን የውንብድና ሥራ ይሰራ የነበረ 'የሚፍፈራ ተቋም' እንደነበር ይነገራል። እናም በአንዱ ቀን በድንገት አንድም የዚህ 'ተቋም' አባል የት እንደገባ ማወቅ ሳይቻል ቀረ። ሁሉም ብን ብለው ጠፉ። ሰንሰለቱ ተበጣጠሰ ሳይሆን ተነነ።
በኋላ እንደተሰማው በመንግሥት በኩል ጉዳዩ በሚመለከተው ክፍል ዘለግ ላለ ጊዜ ስውር ክትትል ተደርጎ በአንድ ምሽት ሁሉም ልቅም ተደርገው ተወስደው ኖሯል። የት እንደተወሰዱ የወቅቱ operation ባለቤት ነው የሚያውቀው። ይህን ከሰማን አንድ 20 ዓመት ጠግቶታል።
እና ምን ማለት ነው? መሬትም ባንክም ታንክም የያዘ አካል ውንብድናን ማሸነፍ /ማክሸፍ ሊያቅተው አይችልም። የአርሲ እና የወለጋ ወገኖቻችን ተደጋጋሚ ግ^ድያ ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ በፍጹም ሊሆን አይችልም።
የፈለገውን operation ተጠቅሞ መከላከልም መቆጣጠርም ይችላል። 'አቅም የለኝም' ካለ 'የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልኝ' ማለት ይችላል። ይሄ ህገ-መንግሥቱ ላይ የተቀመጠ ነገር ነው። እኔ አይደለሁም ያልኩት።
አንድ ግብር እየሰበሰበ ነገር ግን ሥራውን ያልሰራ የመንግሥት አካል ተቀምጦ እያለ በሃይማኖት ሥም ጥ'ቃት እየደረሰ እንደሆነ ለማስመሰል እየተሞከረ ያለው ነገር ደስ አይልም።
7ዳይ በሃይማኖት ሥም ሊደበቅ አይችልም። የሚሳካ ባይሆንም ለፖለቲካዊ ትርፍ ሲባል በሙስሊሞችና ክርስትያኖች መካከል ቅራኔ ለመፍጠር የሚተጋ ከሁሉም ሃይማኖቶች በኩል 'ወመኔ' ስለማይጠፋ በአስተውሎት መጓዝ ይጠቅማል። ሥራውን ቸል ያለ አካል አለ! አራት ነጥብ!
© ሐዉለት አሕመድ (ፒኤችዲ)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 9430 times