የጥበብ ቅርሶች ስርቆት ዓለም አቀፍ ፈተና በሆነበት በአሁኑ ወቅት የጣሊያን ፖሊስ «Swoads» የተሰኘ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሰረቁ ውድ ቅርሶችን በብቃት ማግኘት ጀምሯል። ይህ አዲስ ሥርዓት እ.ኤ.አ በ2004 ተሰርቆ መልኩ ከተቀየረ በኋላ ተደብቆ የነበረውን የ«Saint Agnese» ሥዕል ጨምሮ ከ300 በላይ ትልልቅ ሥዕሎችን እና ከ165 ሺህ በላይ ታሪካዊ ቅርሶች ማስመለስ ያስቻለ ሲሆን፣ የተመለሱት ቅርሶች አጠቃላይ ዋጋም 226 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል።
ቴክኖሎጂው ሥዕሎች ቢለወጡ፣ ቢቆረጡ ወይም የቀደመ ጥራታቸው ቢቀንስ የሕብር እና የቅርጽ ተመሳሳይነትን በመተንተን በቅጽበት የመለየት አስደናቂ አቅም አለው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መረጃዎችን ቀንና ሌሊት በማጣራት የፖሊስን ሥራ በእጅጉ እያቀላጠፈው ሲሆን፤ እንደ ጣሊያን፣ ቱርክ እና ኢንተርፖል ያሉ ሀገራትና ተቋማት ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ታሪካዊና ባህላዊ እሴት ያላቸውን በርካታ ቅርሶች ለባለቤቶቻቸው የመመለስ ስኬታማ ተግባር ማከናወናቸውን ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
EAII-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና

