Friday, 30 October 2026 06:09

ከ19 ዓመታት የባህል ምግብ ልምድ ወደ ዘመናዊው "ቡል ኤንድ ቡሽ" አገልግሎት

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
በአገራችን እየተስፋፋ የመጣውን የቱሪዝም ዘርፍ ዝመና እና የባሕል ምግብ አዳራሽ አገልግሎት የበለጠ ለማጎልበት ያለመ፣ በዓይነቱ ለየት ያለ ዘመናዊ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጥ "ቡል ኤንድ ቡሽ" (Bull & Bush) የተሰኘ ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ፡፡
ሬስቶራንቱ በሁለት ሺሕ ሐበሻ ባሕላዊ የምግብ አዳራሽ የ19 ዓመታት የስራ ልምድና አስተዋጽዖ ላይ ተመስርቶ የተከፈተ ሲሆን፣ በዋናነት በመሃል ቦሌ አትላስ አካባቢ ከአዳራሹ በስተጀርባ ይገኛል።
የሬስቶራንቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የሁለት ሺሕ ሐበሻ ባሕላዊ የምግብ አዳራሽ ባለቤት አቶ ነጋሲ ገብረማርያም እንደገለጹት፣ ተቋሙ በኢትዮጵያ ያለውን የአመጋገብ ባሕልና የዘመናዊ ምግብ ፍላጎት ያቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በአገራችን አብዛኛው የጥሬ ስጋ ቤት አገልግሎት ባሕላዊ በሆነ መልኩ ለወንዶች ብቻ የተወሰነ ይመስል የነበረ ቢሆንም፣ "ቡል ኤንድ ቡሽ" ቤተሰብን ያማከለ አሰራር መዘርጋቱን አቶ ነጋሲ ገልጸዋል። አባቶች ጥሬ ስጋ በሚመገቡበት ወቅት፣ እናቶችና ሕጻናት እንደፒዛ፣ ሻዋርማ፣ የተጠበሰ ዶሮ (Chicken Points)፣ አሮስቶ እና የቁርስ ምግቦችን በስፋት ማግኘት የሚችሉበት ሰፊ የምግብ ዝርዝር (Menu) መዘጋጀቱንም አንስተዋል።
ሬስቶራንቱ በውስጡ ከአራት ዓይነት በላይ ቤት ውስጥ የተጠመቁ ቢራዎችን (House-made Beer) የሚያመርት ሲሆን፣ አሰራሩም 98.6 በመቶ ከስኳር ነጻ (Sugar-Free) በሆነ መንገድ በቦታው ላይ ተጠምቆ ለደንበኞች የሚቀርብ መሆኑን አቶ ነጋሲ አያይዘው አስረድተዋል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ወደፊት የሰራተኞቹን ቁጥር እስከ 200 ለማድረስ አቅዷል። በተጨማሪም ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ የውጭ አገር ቱሪስቶችና ዲፕሎማቶች የአገሪቱን ባሕላዊና ዘመናዊ የምግብ አቀራረብ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተነግሯል።
ሬስቶራንቱ በቂ የመኪና ማቆሚያና ጥበቃ ያለው እንዲሁም ለትራንስፖርት አመቺ በሆነ ቦታ ላይ እንደሚገኝና ደንበኞችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑ ተመልክቷል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 7111 times