Friday, 30 October 2026 06:17
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሀገራቸው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻሻልና ወደ ነበረበት እንዲመለስ ድጋፍ ለማድረግ ሙሉ ዝግጁነቷን አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ፍላጎት ካላቸው ሩሲያ ውይይትና ድርድር የሚያደርጉበትን መድረክ በማመቻቸት አዎንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኗን መግለጣቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ላቭሮቭ አክለውም "ዛሬም፣ ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ" መሪዎቹ ለመነጋገር ፍቃደኛ እስከሆኑ ድረስ ሞስኮ የሰላም ውይይቱን ለማስተናገድ በሯ ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል። ሆኖም እስከ አሁን ድረስ ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ በኩል በሩሲያ አሸማጋይነት ለመነጋገር የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ የለም።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና

