Friday, 30 October 2026 06:10

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ ወሰነ

Written by 
Rate this item
(5 votes)
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በየሁለት ዓመቱ ወደሚካሄድበት ቀደምት አሰራሩ እንዲመለስ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
ውድድሩ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ቀደም ሲል ታስቦ የነበረውን አቅጣጫ በመቀየር የተላለፈው ይህ ውሳኔ፤ የአህጉሪቱን እግር ኳስ፣ የ54ቱን አባል ማህበራት እንዲሁም በውጭ ሀገራት ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾችን ጥቅም ለማስጠበቅና ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ማሻሻያ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት በአፍሪካ ዋንጫ ምትክ በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው አዲሱ "የአፍሪካ ኔሽንስ ሊግ" ውድድር፣ የአፍሪካ እግር ኳስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ራሱን የቻለ እንዲሆን የሚያስችለውን ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም ለማመንጨት በርካታ ዓመታት የሚፈጅበት መሆኑ በመረጋገጡ ነው።
የካፍ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓትሪስ ሞትሴፔ እንደገለጹት፤ ውሳኔው የአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት እንዳይስተጓጎል እና ጠንካራ የፋይናንስ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
Read 2680 times