Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:09

.ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል..   ማርክ ትዌይን
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው የታመመ ጓደኛውን ሊጠይቅ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ ጓደኛው የመጨረሻው የሞት አፋፍ ላይ ነበር ይባላል፡፡ ኦክሲጂን በላስቲክ ቱቦ ተገጥሞለት ነው የሚተነፍሰው፡፡
ጠያቂው ወደሚያጣጥረው ጓደኛው ቀረብ ብሎ ሲያየው ታማሚው በጣም ባሰበትና እየተወራጨ በሚያቃስት
..እባክህ የምጽፍበት ወረቀትና እርሳስ አቀብለኝ.. አለ፡፡
ጠያቂው በፍጥነት ወረቀትና እርሳስ እያቀበለው፤
..አይዞህ የፈለግኸውን ጻፍ፡፡ በርታ.. አለው፡፡

ህመምተኛው የሞት ሞቱን እያማጠ ባለ በሌለ አቅሙ አንድ ማስታወሻ ለመጻፍ ሞከረ፡፡
ማስታወሻውን ጽፎ ሲያበቃ በሽተኛው ህይወቱ አለፈች፡፡ ጓደኝየው በሀዘን ስሜት እንደተዋጠ ሟቹ የጻፈውን ማስታወሻም እንኳን ለማንበብ ለራሱ ጊዜ ሳይሰጥ ኪሱ ከተተው፡፡
ሟቹ ከተቀበረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጓደኝየው ወደ ሟቹ ቤተሰብ ይሄዳል፡፡ ከዚያም፤
..እንግዲህ ሰው ሆኖ ከሞት የሚቀር የለም፡፡ ልጃችሁ ያጋጠመው ህልፈት ነገ ሁላችንንም የሚያጋጥመን ህልፈት ነው፡፡ ስለዚህ ሀዘኑን አለማጥበቅ ነው፡፡.. ይላል፤
እናት፤
..እውነትክን ነው፡፡ ከሞትማ ማን ይቀራል?.. አሉ፡፡
አባትም፤
..የተናገርከው እርግጥ ነው፡፡ እንደው ድንገት ማጋጠሙ ነው እንጂ ከሞትማ ልቅርስ ቢባል እንዴት ይቻላል?.. ይላሉ፡፡
ሌሎቹም የቅርብ ዘመዶች፤
..እንዲህ ያለ አሳዛኝ፣ አሳቢ ጓደኛ ከወዴት ይገኛል?.. እያሉ የየበኩላቸውን ሀሳብ ይሰጣሉ፡፡
..በዛሬ ጊዜ የጓደኛው መቃብር ሲቆፈር ምነው አቀረባችሁት ጉድጓዱን አርቃችሁ ቆፍሩት እንጂ?´ የሚል ሰው ነው ያለው፡፡
ወይም ደግሞ፤
..እንደምንም ያለውን ሀብት እንዳይዝረከረክ እናሰባስብለት በሚል እንዴት እጄ ላስገባው? ይላል እንጂ እንዲህ ከልቡ የሚቆረቆር sW'÷ አይገኝም.. ሲሉ የየግል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡
በዚህ መካከል ጓደኝየው፤ ሟቹ የፃፈው ማስታወሻ ኪሱ ውስጥ እንደነበረ ትዝ አለው፡፡
ከዚያም ለቤተሰቡ ሟቹ የፃፈውን ማስታወሻ ቢያነብብላቸው የሚሰማቸውን እፎይታ በማሰብ፤
..ሟቹ ጓደኛዬ የመጨረሻ እስትንፋሱን ሳያጣ በፊት፤ የፃፈው ማስታወሻ አለ፡፡ ልክ ነብሱ ከሥጋው ስትለይ እጄ ላይ አስቀምጦት ነው ያለፈው..
..ምነው እስካሁን አቆየህብን.. አሉ አባት፡፡
..ምን አደረግንህ እስካሁን ሳታነብልን መቆየትህ?.. አሉ እናት፡፡
ሌሎቹም ዘመዶች ሁሉ ..ምነው ምን አደረግንህ?.. ሲሉ ወቀሱት፡፡
ጓደኝየውም፤ ..በሀዘኑም በሌላም ምክንያት ስሯሯጥ በመዘንጋቴ ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ እርግጥ ልጃችሁ የልብ ወዳጄ፤ ያለጥርጥር የሚፍልን ስለነገ ራዕይ የምንሰንቅበትና የሚያነሳሳን ድንቅ ነገር እንደሚሆን እምነቴ ነው!.. አለ፡፡
በመጨረሻም የተጣጠፈውን ወረቀት ዘረጋጋና ጮክ ብሎ እንደሚከተለው
..ወዳጄ፤ የኦክሲጂን ቱቦዬ ላይ ነውኮ የቆምከው
***
ደግ የሚያደርጉልን መስለው፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ፤ የኦክሲጂን ቱቦዎቻችን ላይ ከሚቆሙ ሰዎች ይሰውረን፡፡ እኛ ደጉን ስንጠብቅ የእንጀራ - ገመዳችንን ከሚበጥሱ ተንኮለኛና ክፉ ሰዎች ይሰውረን፡፡ ዛሬ ከጉዳይ ሁሉ ቀዳሚው በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፤ በማህበራዊም መልኩ በራስ መተማመን ነው፡፡ በራስ ለመተማመን ቢያንስ በሌሎች መፈራት ሳይሆን መወደድ፣ መጠርጠር ሳይሆን መከበር፤ ይቆይብኛል ብሎ መስጋት ሳይሆን ይሄድብኛል ብሎ መጨነቅ የሚፈጥር መሪ መሆንን ይጠይቃል፡፡ በራስ ለመተማመን ለሁሉም የሀገራችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መፍጨርጨር ሳይሆን ሌሎች የሚሰጧቸውን አማራጮች ለማዳመጥ
ኧርል ግሬይ (እ)ስቲቨንስ እንዲህ YlÂL:-
..በራስ መተማመን፤ ልክ እንደጥበብ፤ ለሁሉም ጥያቄ መልስ ከማግኘት የሚመጣ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለሁሉም መልሶች ልብን ክፍት ከማድረግ የሚመነጭ ነው..
ለመጠፋፋት ጊዜ የማይፈጅብን፤ ለመፋቀር ረዥም ዘመን የማይበቃን አያሌ ነን፡፡ ቀድሞም ሆነ ዛሬ እርስ በርስ፣ በፖለቲካ ድርጅትና ድርጅት ውስጥ ያለውን መናቆር፤ ትላንት ገዢዎች ያደርጉ ከነበረው ፍትጊያ ተነስቶ ማየት ቀላል ነው፡፡ ለዚህ አይነተኛ አስረጅ የሚሆነን በአስፋወሰንና በሞራት ገዢ በጥዱ ማህል የነበረው ጠብ በየፊናቸው ከገጠሙት ግጥም ይታይ ነበር፡፡ ጥዱ እንዲህ አሉ -
..አስፋወሰን ይፋት ጠንክረው ይረሱ
ሞራት ጥዱ-አል ብለው ከመመላለሱ..
አስፋወሰን እንዲህ መለሱየቆምከው
..ለሞፈር ለቀንበር የሚሆነኝን
ሳልቆርጠው አልቀርም ዘንድሮ ጥዱን!..
እንደራደር፣ እንነጋገር፣ እንቻቻል፣ እንግባባ ማለት ማንን ገደለ?
ከፖለቲካው ቀውስ የሚብሰው የኢኮኖሚው ቀውስ ነው፡፡ ይሄ በእኛ አገር ላይ ብቻ የተከሰተ አባዜ አይደለም፡፡ በመላው ዓለም በኃያላኑ ላይ ጭምር ፍንትው ብሎ የታየ የኢኮኖሚ መቃወስ ዛሬ ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ የሚገርመው ማጣፊያው ያጠረውም ያው እንደኛው ነው!
ፒተር ጊል የተባለ ፀሀፊ ጋዜጠኛ፤
..ምዕራባውያን የፖለቲካ መሪዎች ነገን ለመጋተር ሲያስቡ፤ ምን ይሄ ኢኮኖሚኮ ነው የማይረባ ያሰኛቸዋል፡፡ ለኢትዮጵያዊ የፖለቲካ መሪ ደግሞ ምን የድህነት ኢኮኖሚኮ ጣጠኛ ነው! ያሰኘዋል ይለናል፡፡.. (It is the economy እና It is the economics of poverty እንደማለት ነው)
የሚገርመው ኃያላኑ ምዕራቦችም እኛም እኩል በኢኮኖሚ ላይ ማማረራችን ነው፡፡
ይህንን አስመልክተው፤
የሚሌኒየም ቪለጅ ፕሮጀክት መሥራች ፕሮፌሰር ሳች ..በአሁኑ ጊዜ ሀብታሞቹ የሚሰቃዩት ፍትሕ እያነሰ በሚሄድበትና የበለጠ ወዳለመረጋጋት ወደሚሄድ ዓለም እየሰመጡ ስለሚሄዱ ነው.. ብለው ይደመድማሉ፡፡ ..ይህን ለመግለ የሚቸግረኝ ሰው አይደለሁም.. ብለው ይቀጥሉና ..ዋናው የሞራላዊ ምናብ፣ የአመራርና የግንዛቤ አጥረት ነው!.. ይላሉ፡፡
ይሄ ነገር እኛም አገር በይፋና በሰፊው የሚታይ በመሆኑ፤ ..እፍኝ ቆሎ ይዘህ ከአሻሮ ተጠጋ.. በሚለው ተረት ከተጠቀምንም፤ አንድ ነገር ነው! ሁሉንም ችግሮቻችንን በአንድ በትር እንምታ ማለት የመሪዎቻችን ሁሉ ፈሊጥ ነው፡፡ በእርጋታ፣ በትዕግሥትና በመቻቻል የሚፈቱ አያሌ ጉዳዮች ሁሉም ላይ ባንዴ ካልዘመትን ብለን ያመከናቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ማርክ ትዌይን በሹፈት መልኩ ..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚሥማር ይመስለዋል.. የሚለን ይሄንን ነው! ከዚህም ይሰውረን፡፡

 

Read 3666 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:17