Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 08 August 2011 09:44

..የደረቀ ቅጠል እሳት ጭረው አትንደድ ቢሉት.......

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አለም በህገወጥ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ምን ያህል ሴቶችን አጥታለች ለሚለው ለጊዜው በእርግጠኝነት ይህን ያህል ማለት ባይቻልም ብዙዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ግን እውን ነው፡፡ እንደ World Health Organization, the Alan Guttmacher Institute, and Family Health International, እማኝነት ከሆነ በአለም Ÿ70,000 - 200,000 የሚሆኑ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

ይህ ቁጥር ወደ ህክምና ተቋም ለሕክምና እርደታ የሄዱትን ወይንም በጥናቱ ወቅት ትክክለኛው መረጃ ከተገኘባቸው ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ለእማኝነት ያልቀረቡ የእናቶች ሞቶች እንደሚኖሩ እሙን ነው፡፡ ለዚህ እትም በኢትዮጵያ ስላለው ጽንስን የማቋረጥ ህጋዊ አሰራራር የሚያብራራሩት ወ/ሮ ኦሪጅናል ወልደጊዮርጊስ ይባላሉ፡፡ ወ/ሮ ኦሪጅናል በአይፓስ ኢትዮጵያ የህግ አማካሪ ናቸው፡፡ ወ/ሮ ኦሪጅናል በሴቶችና በህጻናት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደዋል፡፡
***
ኢሶግ/     በኢትጵያ ህግ አተረጎዋጎም ጽንስ ማቋረጥ ማለት ምን ማለት ነው?
ኦሪጅናል/ ጽንስ ማቋረጥ ምን ማለት አንደሆነ በኢትዮጵያ ህግ ስያሜ ›M}cÖ¨ወለድበት እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ በሁለት መንገድ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ አንደኛው በተፈጥሮ ማለትም በህመም ወይንም በአደጋ በመሳሰለው የሚቋረጠው ሲሆን በሌላ በኩል ግን ጽንሱን የያዘችው ሴት በተለያየ ምክንያት እንዲቋረጥ ስትፈልግ የምታቋርጠው ነው፡፡ ያረገዘችው ሴት ልጁ ቢወለድ ማሳደግ የማትችልበት ሁኔታ ሲፈጠር የሴትየዋን መብት እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል ለሚለው የኢትዮጵያ ህግ መስፈርቶችን አስቀምጦአል፡፡ የኢትዮጵያ ህግ ይህንን የሚመለከት ድንጋጌ ያወጣው ከ1949 ዓ/ም ጀምሮ ነው ፡፡የ1949 ዓ/ም የቀድሞው የወንጀል ህግ በ1996 ዓ/ም ተሸሽሎ ሲወጣ ጽንስን ማቋረጥን ያካተተ ሆኖአል፡፡ ይህ ህግ በተወካዮች ምክር ቤት በ1996 መጨረሻ ከጸደቀ በሁዋላ አዋጁን ለማውጣት ሙሉ አመት ፈጅቶአል፡፡ ከዚያም የፌደራራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር በተሰጠው ስልጣን መሰረት መመሪያ አውጥቶ ስራራውን ለመጀመር አንድ አመት በመፍጀት ሰኔ 19/1998 መመሪያው ወጥቶ በስራራ ላይ ውሎአል፡፡
ኢሶግ/ በ1949 ዓ/ም የወጣው ህግ ጽንስን በማቋረጥ ረገድ ምን አተረጎዋጎም ነበረው?
ኦሪጅናል/    የ1949 ዓ/ም ጽንስን የማቋረጥ ህግ በኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራራዊ ካልሆኑ ህጎች መካከል የሚቆጠር ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ህጉ ጽንስን በማቋረጥ ሁኔታ ላይ በክልከላ ጀምሮ በክልከላ የሚጨርስ ነበር፡፡ ህጉ እንደT>ገልጸው አንዲት ሴት በማናቸውም ጊዜ በየትም ቦት በሚል የእርግዝናው ጊዜ ምንም ያህል ቢሆን እና በሐኪም ቤትም ማለት ነው... በማናቸውም ዘዴ ሲል በህክምናም ይሁን በባህላዊ ዘዴ ጽንስ ማቋረጥ አትችልም ብሎ ነው ¾T>ËU[¨<፡፡ ማንኛዋም ሴት ልጅ መውለድ ትፈልጋለች፡፡ በየትኛውም መንገድ ጽንስ ማቋረጥም አይበረታታም፡፡ ይሁን እንጂ ምንጊዜም ጽንስ ማቋረጥ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራራል፡፡ ለምሳሌ... አንዲት ሴት ...አንቺ ታመሻልና ያረገዝሽውን ልጅ ልትወልጂው አትችይም...  ብትባል አይ... እኔ ሞቼ ...ልጁ ይወለድ የምትል አትገኝም፡፡ ስለዚህ በተለያዩ አስገዳጅ ሁኔታዎች ጽንስን ማቋረጥ በ1949 ዓ/ም ሕግም ሆነ በየትኛውም አለም ሊከለከል የማይችል ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲል በነበረው አሰራራር አንዲት ሴት ከችግር ውስጥ በመውደቋ ምክንያት ጽንስን ማቋረጥ ብትሞክር ያስቀጣታል፡፡ ሐኪሞችም በህጉ ከተፈቀደው ውጭ ጽንስ ቢያቋርጡ የስራራ ፈቃዳቸውን ይነጠቁ ነበር፡፡ በ1949ዓ/ም በወጣው ህግ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቀደው ለእናትየውና ለጽንሱ ሕይወት ችግር የሚፈጥር ሲሆን ብቻ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ጽንስን ለማቋረጥ የጤና ሁኔታ እንኩዋን አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ አፈጻጸሙ እጅግ አስቸጋሪ የነበረ ነው፡ ለምሳሌ አንዲት ሴት የልብ ሕመም ቢኖርባትና ጽንስ እንዲቋረጥ ቢያስፈልግ የጽንስ ሐኪሙ ለጤና ጥበቃ ሚኒስር የልብ ሐኪም እንዲመደብለት ደብዳቤ ጽፎ ከዚያም የልብና የጽንስና ማህጽን ሐኪሞቹ በጋራራ ተቀምጠው ውሳኔውን የሚሰጡበት የተቀላጠፈ አሰራራር ያልነበረበረት አሰራራር ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለምሳሌ... አንዲት ወጣት እኔ ያረገዝኩት ጽንስ እንዲወርድልኝ እፈልጋለሁ ብላ ሐኪሙን ብታማክረው አይሆንም ብሎ የሚመልሳት ሲሆን በራራስዋ መንገድ ጽንሱን ነካክታ እየደማች ብትመጣ ግን ያው አይሆንም ብሎ የመለሳት ሐኪም አልጋ ሰጥቶ አስተኝቶ ሕክምና ማድረጉን ÃkØLM፡፡ቀደም ሲል የነበረው ህግ ያስከተለው ችግር  ያረገዙት ሴቶች አቅማቸውንና ጉዳታቸውን የሚመለከትL†¨< ፣ፈቃዳቸውን የሚፈጽምላቸው ባለመኖሩ በመሰላቸው መንገድ አካላቸውን ሲነካኩ ከአካል ጤንነት እጦት ባሻገር ልጅ ለመውለድ ካለመቻል እስከ ሕይወት ማጣት የደረሱ በርካቶች ናቸው፡፡ በኢትዮያ የ1949 ዓ/ም የወንጀል ሕግ ጽንስና ማቋረጥ የሚቻልበትን እድል እጅግ አጥብቦ አይቻልም እስከማለት በሚያስችል ሁኔታ ቢቀመጥም እንኩዋን አቅም ለሌላቸው ሴቶች መንገድ ከመዝጋቱ ውጪ እድሉ ያላቸው ሴቶች ግን ጽንስን ካልፈለጉ እንዲያቋርጡ የሚፈቅዱ የህክምና ተቋማት እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ በዚህ ምክንያት የ1949 ዓ/ ም ህጉ የተጠበቀበት መንገድ እምብዛም ነበር ፡፡ የጽንስ ማቋረጥ እንደማንኛውም የስነተዋልዶ ጤና መብት መብት መሆን አለበት፡፡ ሴቶች እንዲዋሹና ንጽህናው ባልተጠበቀ መንገድ የሐኪሞ ችሎታ ፣የሚፈጸምበት ቦታ እና መሳሪያው ጽንስ ማቋረጥን እንዲፈጽሙ ማበረታታት አይገባም የሚሉ ብዙ የጥናት ውጤቶች አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በጅማ ፣ጎንደር እና አዲስ አበባ በተደረገው ጥናትም ሆነ እንደውጭው አቆጣጠር በ2000ዓ/ም አካባቢ ኢትዮጵያ  ከወሊድ ጋር በተያያዘ የእናቶች ሞት በአለም አንደኛ እንደነበረች አይዘነጋም፡፡ ይህ የሚያሳየወ ህጉ ቢከለክልም ሴቶቹ ግን በእራራሳቸው መንገድ ስለሚጠቀሙ መሞታቸውን ነው፡፡ እናቶች ሲባል ስላረገዙና ስለወለዱ እንጂ የሚሞቱት ሴት ሕጻናቱም ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመለወጥ ህጉን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በ1996 ዓ/ም ህጉ እንዲሻሻል ተደርጎአል፡፡
ኢሶግ/ በ1996 ዓ/ም የወጣው የወንጀል ህግ ጽንስ ማቋረጥን በምን መንገድ አሻሻለው?
ኦሪጅናል/ በ1949ዓ/ም የወጣው ህግ ምን ያህል ለአሰራራር አስቸጋሪ እንደነበር ለሚያውቅ ሰው የ1996ዓ/ም ህግ መውጣቱን ጥሩ መሻሻል ነው ሊለው ይችላል፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግስት ጽንስን ማቋረጥን ሙሉ ለሙሉ ከመከልከል ይልቅ የተወሰኑ ሊፈቀድ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ግልጽ አድርጎ በህጉ በማስፈሩ የሰጠው ጥቅም ከፈተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎ ለምን ሙሉ ለሙሉ መብት ሆኖ አይቀመጥም በሚል ቢሻሻልም ህጉ የሚቀረው ነገር አለ የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ ነገር ግን የ1949 ዓ/ም ህግ በክልከላ ጀምሮ በክልከላ የሚጨርስ ሲሆን የ1996 ዓ/ም ህግ ግን በህክምና ተቋም በተፈቀደ የጊዜ ገደብ እንዲሁም ያረገዘችውን ሴት ማህበራራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በጤናና በተለያዩ ምክንያቶች ጽንስን በይፋ ማቋረጥ የሚቻልባቸው” ነጥቦች በአራራት ከፋፍሎ አስቀምጦ›†ªM፡፡  
ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ጽንስና ማቋረጥ የሚቻልባቸው ምክንያቶች፡-
1/ በመደፈርና በዘመድ መካከል በተደረገ የግብረስጋ ግንኙነት የተጸነሰ ከሆነ፣
2/ እርግዝናው መቀጠል በእናቲቱም ሆነ በጽንሱ ሕይወት ወይንም በእናቲቱ ጤንነት ላይ አደጋ የሚያስከትል ሲሆን፣ የልጁ መወለድ በእናቲቱ ጤንነት እና በህይወትዋ ላይ ችግር የሚያመጣ ሲሆን ፣
3/ ጽንሱ ሊድን የማይችል ከባድ የአካል ጉድለት ያለው ሲሆን ፣
4/ አንዲት እርጉዝ ሴት ሀ/ የአካል ወይንም የአእምሮ ጉድለት ያለባት በመሆኑ ልጁን ወልዳ ለማሳደግ የህሊናም ሆነ የአካል ብቃት ባይኖራራት  ለ/ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ሆና ልጁን ወልዶ ለማሳደግ በአእምሮና በአካል ዝግጁ ያልሆነችና  የማትችል ከሆነ ጽንሱን ማቋረጥ እንደሚቻል ህጉ ይፈቅዳል፡፡  
ኢሶግ/ አስገድዶ መደፈርና ከዘመድ ጋር ባለው ግንኙነት ከተጸነሰ ማቋረጥ ይቻላል ሲባል መመዘኛው ምንድነው?
ኦሪጅናል/ በእርግጥ ይህ ጥያቄ ብዙውን ጊዜ አነጋጋሪ ሆኖ ይነሳል፡፡ ነገር ግን አንዲት ሴት ተገዳ ለመደፈርዋ ወይንም በአንዱ ዘመድዋ በተደረገ ግንኙነት ማርገዝዋን በሚመለከት ምስክርዋ እራራስዋ ነች፡፡ ከዚህ ውጭ ለፖሊስ አመልክተሻል ወይንስ ክስ መስርተሻል ወይ የሚል ጥያቄ አይነሳም፡፡ የዝምድናውን ደረጃና ማንነቱን የመግለጽ ግዴታም የለባትም፡፡ ጤና ጥበቃ ባወጣው የአሰራራር መርህ መሰረት የምክር አገልግሎት ከተሰጣት በሁዋላ ጽንስ ማቋረጡ ይፈቀድላታል፡፡
ኢሶግ/ ጽንስን ማቋረጥ የሚችለው ባለሙያ በምን ደረጃ ያለ ነው?
ኦሪጅናል/ ቀደም ባለው ጊዜ የጽንስ ሐኪም ብቻ ጽንስ ማቋረጥ እንደሚችል መመሪያው ይገልጽ ነበር፡፡ አሁን ግን ስልጠና እስከተሰጠ ድረስ እንደጊዜ ገደቡ ሙያው ከሐኪም ዝቅ ባለ ደረጃ ያለ የጤና ባለሙያም ሊሰራራው እንደሚችል በመመሪያው ተቀምጦአል፡፡ የእርግዝናውን ጊዜ በሚመለከት እስከ ሶስት ወር በማን እንደሚሰራራ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ...ወዘተ በሚል የተከፋፈለ ሲሆን ሁሉም የጽንስ ማቋረጥ ሂደቶች ግን ንጽህናውንና ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ እንዲካሄዱ ተደንግጎአል ፡፡ የጽንስ ማቋረጡ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ የጤና ተቋማት ማለትም ጤና ጣቢያ በመሳሰሉት ቦታዎች ሊካሄድ የማይችል ከሆነ ወደከፍተኛ የህክምና ተቋም በማስተላለፍ መሰራራት እንደT>Ñv¨<ም ይገልጻል፡፡
ኢሶግ/ ወደ ጽንስ ማቋረጥ ከመደረሱ በፊት አስቀድሞውኑ ያልተፈለገ እርግዝናውን ለመከላከል ምን ቢደረግ ጥሩ ይሆናል?
ኦሪጅናል/ የደረቀ ቅጠል ላይ እሳት ጭሮ አትንደድ አትንደድ ቢሉት መንደዱን አይ}¨<ም፡፡¨×~” ሳያስተምሩ ከችግር እንዴት እንደሚወጡ ሳያሳዩ ያልተፈለገ እርግዝና ትክክል አይደለም፣ ጽንስ ማቋረጥ አያስፈልግም ቢባል ምንም ውጤት የለውም፡፡  አሁንም ጽንስ ማቋረጥ አይገባም ሲባል ህብረተሰቡ ፣የሀይማኖት ተቋማት፣ ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ ምን አድርገዋል የሚለውን መመልከት ይገባል፡፡ጽንስ ማቋረጥን በህግ በመፍቀድና በመከልል ብቻ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ያስቸግራራል፡፡

Read 4669 times