Saturday, 10 September 2011 11:45

ብርቅና ድንቅ ሰው... የሚሊኒየሙ ገጠመኝ...

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

የሚሊኒየሙ ገጠመኝ የአደይ ሽመልስ ነው፡፡ ታሪኩን ለአንባቢ ስንል ሌሎች ተመሳሳይ ገጠመኞችም እንደሚኖሩ በመተማመን ነው፡፡
---------------------------///--------------------------
..እኔ የታሪኩ ባለቤት አይዳ ሽመልስ የተወለድኩትም የአደግሁትም ናዝሬት ወደ ሶደሬ መንገድ ላይ ባለው መንደር ነው፡፡ ጉዋደኞቼ፣ ዘመዶቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ እንደሚመሰክሩት ቆንጆ ነኝ፡፡ ቁመናዬ አንድ ሜትር ከ75 ሴ.ንቲ ሜትር ሲሆን አፍንጫዬ ሰልካካ፣ አይኔ ጎላያለ ፣ጸጉሬም ቢሆን ጠንከር ያለ ይሁን እንጂ በዛ እና ረዘም ያለ በተለይም ሲተኮስ ልዩ የሆነ ውበት ያለው ነው፡፡ የሽንጥና የዳሌ ነገር አይወራራም... ግሩም ነው፡፡ እናስ ምን ሆንሽ በሉኝ... አዎን ...እኔ የምፈልገው እሱን ነው፡፡

..እኔ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ ግጥም መጻፍ በጣም እወድ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የስነጽሁፍ የድራራማ ወይንም የዘፈን ነገር እጅግ ይስበኛል፡፡ ታዲያ ጉዋደኞቼ የግጥም ደብተሬን ለማንበብ ተውሰው ሲቀባበሉ በአንድ ወቅት የት እንደደረሰ ይጠፋል፡፡ መልሱልኝ ብልም ግራራ ስለተጋቡ መልስ አጣሁ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ ግን ደብተሬን ከአንድ ተማሪ እጅ አገኘሁት፡፡ ደብተሩ የኔ በመሆኑ እንዲመልስልኝ ስጠይቀው ትሽ ናንገራራገረ በሁዋላ መለሰልኝ ፡፡ ልጁም በበኩሉ ይጽፍ ኖሮ ደብተራራችንን እየተቀባበልን በማንበብ ተግባባን፡፡   አስተሳሰቡ፣ ደግነቱ ፣ቅንነቱ ግን እጅግ ጥሩ ነበር፡፡ እስከአሁን ድረስ ፍቅር የሚባለው ነገር ጭርሱንም በአጠገቤ እልፍ አላለም፡፡ በእርሱ በኩል ግን መውደዱ እየታወቀ ወደድኩሽ ብሎ ለመናገር የሚፈራራ ነበር፡፡ እሱ የሚወደኝ እኔ ግን ብዙም ትኩረት ያልሰጠሁት ልጅ ለካስ ቀደም ሲል አንዲት ጉዋደኛ ነበረችው ፡፡ ልጁ ብዙም ስለማይዳፈር እቤቱ ከነጉዋደኞቼ ሄደን መዝናናትን እናዘወትር የነበረ ሲሆን አንድ ቀን እንደለመድኩት ከቤቱ ስሄድ ልጅትዋን አገኘሁዋት፡፡ ከዚያም ይህች ልጅ ምንድናት ብዬ ጠየቅሁት፡፡ አ ...አ ..ይ ምንም አይደለም... የሰፈራራችን ልጅ ስለሆነች ነው... አለኝ፡፡ እኔም ማመን አቃተኝ፡፡ ተበጠበጥኩ ትምህርን መማር አቃተኝ ... ልብ በሉ ያለነው ለአስራራ ሁለተኛ ክፍል  ፈተና በምንዘጋጅበት ወቅት ነው፡፡ ጉዋደኞቼ ወደቤተመጻህፍት ሲሄዱ እኔ ይህን ልጅ የማገኝበትን መንገድ ማውጠንጠን ብቻ ሆነ ስራራዬ ፡፡ ደብተሬን ከቤ ይዤ እወጣና ለጉዋደኞቼ ሰጥቼ እኔ ወደእሱ ቤት ነው የምሄደው፡፡ እሱ ደግሞ ከቤቱ ነው ¾T>ÁÖ“¨<፡፡ እኔ ስሄድ ግን ለማጥናት በሚለው ሰበብም ይህችን ልጅ ከዚያ አገኛታለሁ፡፡ በቃ... እራራሴን መቆጣጠር እስኪሳነኝ ደረስኩ፡፡ምን ልሁን...ጉዋደኞቼም በኔ ጉዳይ ተቸገሩ፡፡ አንድ ቀን እነሱም እስቲ እንየው በማለት አብረን ሆነን ከቤቱ ሄድን፡፡ ያው እንደተለመደው ልጅቷ አለች፡፡ በሁዋላ ትንሽ ቆይተው ከመሀከላችን ጠፉ፡፡ ተነስቼ ወደጉዋዳ ስሄድ ቀጥሎ ያለውን ክፍል በር ገርበብ አድርገው በበርጩማ አስደግፈውታል ፡፡ ቀ...ስ ብዬ አልፌ ወደውስጥ ስመለከት ይሳሳማሉ፡፡ አበድኩ...ጉዋደኞቼ እስኪጨነቁ ድረስ ጮህኩ... ከዚያም ደጋግፈወ ወደቤ ወሰዱኝ፡፡ ሶስት ቀን ሙሉ አሞኛል ብዬ ከቤ ተኛሁ፡፡ ፈተናው አንድ ወር ከአስራራ አምስት ቀን ብቻ ነው የቀረው፡፡
እኔ ቀደም ሲል አንድ ሌላ ልጅ ተዋውቄ ነበር፡፡  ነገር ግን ይህንን ልጅ ልክ እንደወንድም የምቀርበው ብዙ ነገር የሚያማክረኝ መንገድ የሚመራራኝ ነበር፡፡ እናም የፍቅር ነገር ሲያነሳብኝ አ... አ... ይ ብዬ ነበር መልስ የሰጠሁት፡፡ ምክንያቱም ለብዙ ነገር ደራራሼ ስለሆነ በሱ እግር ማንን እተካለሁ የሚል ስጋት ስለነበረኝ ነው፡፡ እናም ይህ የወደድኩት ልጅ ያደረገኝን የሆንኩትን ነገር በሙሉ አማክረዋለሁ፡፡እንዲያውም እንደዚህ አድርጊ እንደዚህ በይ እንደዚህ አትሁኚ እያለ ነገሮችን የምቋቋምበትን መንገድ ሁሉ    የሚያሳይኝ እሱ ነበር፡፡
ጉዋደኞቼ በሙሉ ለብሔራራዊው ፈተና ያላቸውን የጥናት ዝግጅት አጠናቀው መዝናናት ጀምረዋል፡፡ እኔ ገን ከአርእስት በስተቀር ምንም የማውቀው ነገር የለም፡፡ በሁወላ ለአንዲት የሳይኮሎጂ ባለሙያ አማከርኩዋት፡፡
...ልጁን እወደዋለሁ...እሱ ግን ሌላ ሴት አፍቅሮአል...ስለዚህ ልጅቷን ላናግራራት ወይንስ ምን ላድርግ ? አልኩዋት፡፡
ሳይኮሎጂስቷም... ጥሩ አስበሻል፡፡ ልጅቷ ምናልባት በእልህ ተነሳስታ ያደረገችው ከሆነ እንድትተወው እሱዋን ለመቅረብ ሞክሪ፡፡ልጅቱዋ ጉዋደኛ ልታረግሽ ካልፈለገች ደግሞ እሱ ለአንቺ ያለውን ስሜት ለማወቅ ተረጂ፡፡ በሁለቱም በኩል የምታገኚው መልስ የማያጠግብሽ ከሆነ እና የእነሱ ፍቅር የሚቀጥል መስሎ ከተሰማሽ ስለራራስሽ አስቢ... አስተሳሰብሽን አስተካክይ የሚል መልስ ሰጠችኝ፡፡
በመቀጠል ያነጋገረኝ ያ እንደወንድም እንደአማካሪ የምሳሳለት... በእድሜ ከእኔ ትንሽ ከፍ የሚለው ጉዋደኛዬ ነው፡፡ ለእሱም የሰጠሁት መልስ ...ልጁን እወደው እንደነበር ...ነገር ግን እሱ ቀድሞ ሲወደኝ ንቄ ትቼ የነበረና አሁን ከሌላ ሴት ጋር ሳገኘው ፍቅሩ በእኔ ጠንቶ መቋቋም እንዳቃተኝ... ፈተናዬንም መፈተን እንደማልችልና በቤተሰብ ደረጃም ችግር ሊገጥመኝ እንደሚችል እያለቀስኩ ነገርኩት፡፡ እሱም አይዞሽ ብሎ በሚችለው መንገድ ሁሉ እንደሚረዳኝና እንደማይለየኝ ተነጋግረን ተለያየን፡፡
ከዚያ ቀጥዬ የሄድኩት ወደእምነት ቤ ነበር፡፡ እዛም ሄጄ ልጁን አፍቅሬዋለሁና ለእኔ እንዲያደርገው ፈተናዬንም በወጉ እንድፈተንና ከጉዋደኞቼ በታች እንዳልሆን ነበር ልመና ያቀረብኩት፡፡ ነገር ግን አልሆነም፡፡ ልጁን ማሰብ ጨርሶ እንደማይገባኝ ተረዳሁ፡፡ ምክንያቱም ከሴት ጉዋደኛው ጋር የነበራራቸው ግንኙነት ጭራራሹንም እየተጠናከረ መጣ፡፡
እንደወንድም የምቀርበው ሰው በዚህ ጊዜ ያገኘሁት ብርቅና ድንቅ ሰው ሆነ፡፡ ቀደም ሲል የነበረንን ትውውቅ ሁሉ ሰርዤ እንደአዲስ የጀመርኩት ግንኙነት ነው የመሰለኝ፡፡ ምክንያቱም ፈተናው እጅግ እየተቃረበ በመጣበት ወቅት ያለማሰለስ እየተከታተለ ቤተመጽሀፍት እንድሄድ ያደርገኝ ነበር፡፡ እሱ ተመርቆ ስራራ ይዞ ስለነበር እንዳልቸገር ፣ጥናት እንዳይሰለቸኝ ...ገንዘብ ፣ ቸኮላት ፣መስቲካ የመሳሰለውን ሁሉ ያቀርብልኝ ነበር፡፡ ጉዋደኞቼ ሁሉ የሚወዱት እኔ ግን ከወንድምነት ውጭ ጭርሱንም ልቤን ልሰጠው ያልቻልኩት የነበረው ሰው ... ምናልባት ተኝቼ ሳላጠና እንዳልውል ጭምር ስልክ እየደወለ ሲቀሰቅሰኝ ቤተሰቤም ያደንቀው ነበር፡፡ እንዲያውም አባ..ይህ ሰው ማነው ? አስተማሪሽ ነው ? እያለ ይጠይቀኝ ነበር፡፡
Ñ<ªÅ™ቼ ጥናት ጨርሰው እየዞሩ ሲዝናኑ እኔ ግን ገና ሀ ያልኩትን ጥናት የትም ሳላደርሰው ፈተናው መጥቶ ቁጭ አለ፡፡ በቃ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያን ሄጄ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ በተለይም የእና ልፋት በጣም አሳዘነኝ፡፡ እና .....ተምራራ እራራስዋን ያልቻለች ሴት ልጅ ሕይወቷ የተበላሸ ነው የሚሆነው.. ትለኝ ነበር፡ እሱ ሁሉ ነው እየመጣ ከፊ ድቅን ይል የነበረው፡፡ Kእግዚአብሔር ሳለቅስ ይሄ ሁሉ ይመጣብኝ ስለነበር አምርሬ ነበር የነገርኩት፡፡ .. ብቻ ፈተናውን አሳልፈኝ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በሁዋላ እኔ አውቃለሁ፡፡ .. እያልኩ ነው የለመንኩት፡፡ ...እ...አልቀረም...ፈተናውን ተፈተንኩት፡፡
ውጤቱ ምን ሆነ...? ሁላችሁም የምትጠብቁት ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ እኔ ሳልሰራራው እግዚአብሔር እራራሱ ሰርቶት ፈተናውን አለፍኩ...፡፡ ምናልባት ለዚህኛው ጥያቄ መልሱ ምን ነበር የሚል ጥያቄ ቢቀርብልኝ ኖሮ እንኩዋንስ መልሱን ጥያቄውን እራራሱን እንደማላስታውሰው ነበር የምናገረው፡፡ ያ ሁሉ የፍቅር ምስቅልቅል አልፎ  ፈተና አለፍኩ ብዬ ጨፈርኩ..........እንዲያውም ቤተሰቤን አስፈቅጄ ፓርቲ ደገስኩ፡፡ ቤተሰቤም ታሪኬን ስለማያውቅ የኛ ልጅ ጀግና ነች አለ......፡፡ ፈተናውን ማነው የሰራራው......መልሱ አላውቅም ነው፡፡
2000ዓ/ም መግቢያ ላይ ቁጭ ብዬ ስለሚቀጥለው ሕይወ የማስብበት ጊዜ ሆነ፡፡ ይህ ከችግሬ እንድወጣ ፣ጥናን እንዳጠናና ፈተናዬን እንዳልፍ የረዳኝ ጉዋደኛዬ ቁመናው ጥሩ ፣አስተሳሰቡ የተባረከ ፣ለእኔ ብዙ እንክብካቤና ክትትል የሚያደርግልኝ ስለሆነ ለምን የፍቅር ጥያቄውን እሺ ብዬ አልቀበልም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ልክ ወቅቱ የዘመን መለወጫ ያውም ሁለትሺህ ነበር... በደስታ አብረን ዘመኑን ተቀበልነው...... አከበርነው፡፡ እኔም ብሔራራዊ ፈተናውን እንደሰራራ ሰው ተሸፋፍኜ ወደ}መደብኩበት ዩኒቨርሲቲ ሄድኩ፡፡ ቤተሰቤም በጥሩ ሁኔታ ሸኘኝ፡፡ አዲሱን ጉዋደኛዬንም በድፍረት ከእና እና ከእህቶቼ ጋር ›e}ª¨ቅሁት፡፡
ከተመደብኩበት ዩኒቨርሲቲ ለእረፍት ስመጣ ያገኘሁት ወሬ እጅግ የሚገርም ነበር፡፡ ያ ቀደም ሲል ያበድኩለትን ፍቅረኛዬን ያስጣለችኝ ልጅ ለካስ ልክ እኔ ትቼው አርፌ ቁጭ ስል ነበር እሱዋም ትታው ወደ ሌላ፡፡ እኔ ለእረፍት መምጣን ሲያውቅ እንደምንም አግኝቶ ነበር የነገረኝ ፡፡ አኔም ሁለተኛ አጠገቤ እንዳይደረስ አድርጌ ነበር የመለስኩት፡፡ በእርግጥ መልሴ አይነቱ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እሱን ሳይ የሚታየኝ ፈተናው ፣በፍቅሩ ምክንያት ልሆን የነበረው፣ ይሉኝታ ያጠሁ መሆኔ.. የመሳሰለው ስለሆነ አሁንም ሳስበው ይዘገንነኛል፡፡
ለማንኛውም በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2000ዓ/ም ለእኔ እጥፍ ድርብ የሚሊኒየም ዘመን ነው፡፡ በጣም እወደዋለሁ፡፡ ከዚህ ከተባረከው ጉዋደኛዬ ጋር በስምምነት ተፋቅረን እስከአሁን አለን፡፡ ከፍቅር ባሻገር እንደታላቅ ወንድም ወይንም እንደአባት የምቆጥረውን የምንሰፈሰፍለትን ሰው ስላገኘሁ አዲስ ዘመን ለእኔ ሁልጊዜም በተለየ ሁኔታ የማሳልፈው ነው፡፡
እኔ ያገኘሁትን የሰከነ የፍቅር ሕይወት... ፍቅር ላጡ ሁሉ እመኝላቸዋለሁ፡፡ እንኩዋን ከዘመን ዘመን በሰላም አሸጋገራራችሁ
አደይ ሽመልስ ከናዝሬት

 

Read 5756 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 11:50