Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:30

ኮከብ ይወለዳል፤ ይከሰታል፤ ይፈጠራል ኢትዮጵያዊቷ ሃና እና አሜሪካዊቷ ጃኪ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጃኪ ኢቫንቾ
ጃኪ ኢቫንቾ የ11 አመት አሜሪካዊ ነች - በአስደናቂ የድምፅ ችሎታ አሜሪካዊያንን ያማለለች፡፡ አምና በ..ጎት ታለንት.. ውድድር ላይ ስትዘፍን፤ በድምጿ የተማረኩ አሜሪካዊያን ልብ ውስጥ ገባች፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ፤ በጣም ተወዳጅ የሆነችው በተራ ዘፈን አይደለም - በጣም ከባድ እንደሆነ በሚነገርለት የኦፔራ አዘፋፈን እንጂ፡፡ ምን ልታስቡ እንደምትችሉ ይገባኛል፡፡ ከኢትዮጵያን አይዶል ተወዳዳሪዋ ከሃና ግርማ ጋር ተመሳሳይነታቸው ይገርማል - በእድሜያቸው፣ በኦፔራ አዘፋፈናቸው፣ በአስደናቂ የድምፅ አቅማቸው፣ ከውድድር ባገኙት ተወዳጅነት...፡፡ አጀማመራቸውስ?

ሃና ግርማ፤ የኦፔራ አዘፋፈን መለማመድ የጀመረችው፤ የቶም ኤንድ ጄሪ ፊልሞች ውስጥ በሰማቻቸው ዘፈኖች አይደል? የጃኪ አጀማመርም ተመሳሳይ ነው፤ ፊልም ስታይ በሰማቻቸው ልዩ ዘፈኖች፡፡    
ጃኪ በ8 ዓመት እድሜዋ፤ ከአባቷና እናቷ ጋር ፊልም ቤት ያየችውን ፊልም አትረሳውም፡፡ ..ፋንተም ኦፍ ዘ ኦፔራ.. ይባላል ፊልሙ፡፡ በኦፔራ ድምፃዊያን የተዘፈኑ ጣፋጭ ዜማዎችን የያዘ ሙዚቃዊ ፊልም ነው፡፡ በፊልሙና በዜማዎቹ እጅግ የተማረከችው ጃኪ ከወላጆቿ ጋር ፊልሙን አይታ ወደ ቤት ስትመለስ፤ ሌላ ጨዋታ አላማራትም፡፡ ፊልሙ ላይ እንዳየችው፤ ዜማዎቹን በኦፔራ አዘፋፈን ለወላጆቿ ማዜም ጀመረች፡፡
በልጃቸው ድም የተማረኩት የጃኪ እናት፤ ለጊዜው ተደንቀው ዝም አላሉም፡፡ ..ፋንተም ኦፍ ዘ ኦፔራ.. በዲቪዲ ሲታተም፤ ገዝተው አመጡላት፡፡ በፍቅር ዘፈኖቹን መለማመድ ከጀመረችው ጃኪ የሚወጣው ጣፋጭ ድምና ዜማ፤ ቤታቸው ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አልሆነም፡፡ ከተማ ውስጥ በሚዘጋጅ ውድድር ብትገቢስ ብለው ፈቃደኝነቷን ጠየቋት - እናት፡፡ ጥሩ ድም እንዳላት ወላጆቿ ሙሉ ለሙሉ እንዲያረጋግጡ ስለፈለገች በደስታ እሺ አለች፡፡ አነስተኛ የከተማ ውድድር ቢሆንም፣ ፉክክሩና የጃኪ ብቃት አስደናቂ ነበር፡፡ ግን አላሸነፈችም፤ አንድ የ20 ዓመት ወጣት በአሸናፊነት ሲመረጥ፤ ጃኪ ሁለተኛ ወጣች፡፡ ቅር አላላትም፤ በኦፔራ አዘፋፈን እንደሚሳካላትና ጥሩ ድም እንዳላት ወላጆቿን እንዲያምኑ አድርጋለች፤ በዚያ ላይ ልምድ አግኝታለች፡፡
ከዚህ በኋላ የጃኪ ትኩረት የአሜሪካን ..ጎት ታለንት.. ውድድር ነበር፡፡ ውድድሩ ውስጥ መግባት ቀላል አይደለም፡፡ ማጣሪያውን ማለፍ ያስፈልጋል - ብቃትን የሚያሳይ ስራ ቀርፃ በኢንተርኔት በማሰራጨት፡፡ 20ሺ ሰው በተመዘገበበት በዚሁ ማጣሪያ፤ ጃኪ በዩቱብ ያቀረበችው የኦፔራ ዜማ የበርካታ አሜሪካውያንን ድጋፍ ስላገኘ ለተወዳዳሪነት አለፈች፤ በ2010 ለተደረገው 5ኛው የአሜሪካን ጎት ታለንት ውድድር፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ደስተኛ አልነበሩም፡፡ የኦፔራ ዜማው አስደናቂ ከመሆኑ የተነሳ፤ ..የራሷ ድም ሊሆን አይችልም፤ በሌላ ሰው ድም ነው እሷ ከንፈሯን የምታነቃንቀው.. በሚል ተችተዋታል፡፡
በዚህም ምክንያት፤ ለመጀመርያ ጊዜ ውድድሩ ላይ ስትቀርብ ማንም ከሷ ብዙ አልጠበቀም ነበር፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ ተሰጥዖዋን ለማሳየት ያቀረበችው የፑቺኒን ..አማድ ባቢሮ ካሮ.. የተባለ የኦፔራ ዜማ ነበር፡፡ በዚሁ ስራዋ የውድደሩ ዳኞችና መላው ተመልካች በከፍተኛ አድናቆት ፈዝዘው ከመቀመጫቸው ተነስተው አጨበጨቡላት፡፡ ከባዱ የኦፔራ ዜማን ስትጫወት በርካታ ባለሙያዎች ድምፁ ከ10 ዓመት ታዳጊ የሚወጣ ነው ብለው ለማመን ተቸግረው ነበር፡፡ የኦፔራ ዜማዋ ሁሉም በግል በሚመለከተው መድረክ ላይ በቀጥታ ስታቀርብ መታየቷ ሁሉንም በአድናቆት አፍዝዞ ያሳመነ ነበር፡፡ በዚሁ የመጀመርያ የኦፔራ ዜማዋ ላይ የውድድሩ ዳኞች ሲናገሩ.. በውድድራችን ላይ ያየሁት ከፍተኛው ችሎታ ሲል ያደነቃት ፒርስ ሞርጋን ነበረ፡፡ ..ከአንዲት ሚጢጢ ልጅ ይህን ያህል የበሰለ ድም ሲወጣ ያስገርማል.. ያለችው ደግሞ የመሃል ዳኛዋ ሻሮን ኦስቦርን ነበረች፡፡ ..አጀብ ነው፤ መልዓክ ነች.. ሲል አድናቆቱን የገለፀው ደግሞ ሶስተኛው ዳኛ ሃዊ ማንዴል ሆነ፡፡
ታላላቅ የሙዚቃ ባለሙያዎች የጃኪ ኢቫንቾ ማራኪ ድም ከሳንባዋ ወይም ከቅላፄዋ ሳይሆን በአዕምሮዋ ከምትፈጥረው ቅንብር የሚወጣ ነው ሲሉ ምስክርነታቸው በከፍተኛ አድናቆት ገለፁ፡፡ ጃኪ ስለአሜሪካ ጎት ታለንት ውድድር ተሳትፎዋ ስትጠየቅ የምትሰጠው ምላሽ የውድድር መድረኩ በድምጽ ያላትን ተሰጥዖ ለማሳየትና ሙዚቃን ስትጫወት ምን ያህል እንደሚያዝናናትና እንደምትደሰትበት በመግለ ነበር፡፡ በመድረክ ላይ ስትጫወት ሙዚቃ ሁለመናዋን እንደሚጠናወታትና ልትገልፀው በሚያዳግት መመሰጥ ውስጥ እንደሚከታትም ትናገራለች፡፡ አምና በተካሄደው 5ኛው የአሜሪካን ጎት ታለንት ውድድር ላይ ጃኪ በ10 ዓመቷ  ነበር የተሳተፈችው፡፡ የውድድሩን ዳኞችና ተመልካቾች በአድናቆት እንዳፈዘዘች ለፍፃሜው ደረሰች፡፡ በየመድረኩ ላይ የታላላቆቹን የኦፔራ ዘፋኞች የሉቺያኖ ፓቫሮቲ፤ የፑቺኒንና የአንድሬ ቦካሊን ዜማዎች በከፍተኛ ብቃት ስትጫወት ሁሌም ተመልካቾቹንና ዳኞችን ከመቀመጫቸው እያስነሳች ለማስጨብጨብ የቻለች ነበረች፡፡ ከጃኪ ኢቫንቾ ለፍፃሜ የደረሰው በአገረሰብ ሙዚቃ አቀንቃኝነት ሲወዳደር የቆየው የ26 ዓመቱ ጃክ ሚረር ነበር፡፡ የአሸናፊነቱን ግምት ያለማመንታት ለእሷ አድርጎ ስለነበር የሽንፈት NGG„ን በማዘጋጀት መድረኩ ላይ ቀረበ፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ ግን ጃክ ሚረር አሸናፊ ሆኖ የአሜሪካን ጎት ታለንት የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማትን ወሰደ፡፡ ይሄው ወጣት በወቅቱ በመድረኩ ላይ በአሸናፊነቱ የተሰማውን ደስታ ሲገል በመጀመርያ ዘሎ ያቀፈው እሷኑ ነበር፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ በ5ኛው የአሜሪካ ጎት ታለንት በ2ኛ ደረጃ ስትጨርስ አልተከፋችም፡፡ ምክንያቱም እጅግ ተስፋ የምታደርግ ልጅ ስለነበረች ነው፡፡ዘንድሮ 11ኛ ዓመቷን የያዘችው ጃኪ፤ በፒትስበርግ ፔንሲልቫኒያ ነው የተወለደችው፡፡ በ8 ዓመቷ የድምፃዊነት መለስተኛ ትምህርት ተከታትላ በሙዚቃው ከ2009 እ.ኤ.አ ጀምሮ ሰርታለች፡፡ በ2010 እኤአ በተደረገው የአሜሪካን ጎት ታለንት ውድድር በከፍተኛ ዝና ተተኮሰች፡፡ ዘንድሮ 6ኛ ዓመት የውድድር ዘመኑን የያዘው የአሜሪካን ጎት ታለንት ፕሮግራም በኤንቢሲ ቻናል የሚዘጋጅ ነው፡፡ በየሳምንቱ ለ120 ደቂቃዎች የሚቀርበው ዝግጅት በአማካይ እስከ 12 ሚሊዮን ተመልካች ይታደሙታል፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ በዚሁ ታላቅ የተሰጥኦ ውድድር 2ኛ ደረጃ ይዛ ስትጨርስ ፕሮግራሙ ከቀረበባቸው 25 ከተሞች በ10 ያህሉ መድረክ ላይ ቀርባ ተሰጥኦዋን በማሳየት እጅግ ዝነኛ ለመሆን በቅታለች፡፡ ከዚሁ የአሜሪካ ጎት ታለንት ስኬታማ ተሳትፎዋ ጎን ለጎንም የመጀመርያ አልበሟን ..ኦ ሆሊ ናይት.. በሚል ስያሜ ለገበያ አበቃች፡፡ አልበሙ የታላላቅ ድምፃዊያንና የኦፔራ አርቲስቶች ታዋቂ ዜማዎችን የተጫተችበት ሲሆን፤ የአንደሬ ቦካሊ ..ኮንቴ ፖሪትዮ..፤ የጆሽ ግሮባን ..ዘ ፕሬየር.. እና ሌሎችም ምርጥ ስራዎች ተካተውበታል፡፡ ይሄው አልበም ለገበያ በበቃበት የመጀመርያ ቀን በአማዞን የአልበሞች ሽያጭ የደረጃ ሰንጠረዥ 1ኛ ደረጃ ከመያዙም በላይ ሙሉውን አመት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ከፍተኛ ስኬት ተቀዳጅቷል፡፡ ..ኦ ሆሊ ናይት.. ከታላላቆቹ ሌዲ UUÂ አዴሌ አልበሞች ጋር በገበያው ፉክክር ውስጥ የገባ ሲሆን በወጣበት የመጀመርያ ሳምንቱ እስከ 240ሺ ኮፒ ለመቸብቸብ በቅቷል፡፡ በዚህ የአልበም ስራዋ በፕሮዱዩሰርነት አብሯት የሰራው ከ16 በላይ የግራሚ ሽልማቶችን የሰበሰበው ዴቪድ ፎስተር ነበር፡፡ ይህ የሙዚቃ ፕሮዱዩሰር ያላትን ተሰጥዖ ተመልክቶ በሙያው ሊያግዛት በመፍቀድ መንቀሳቀስ የጀመረው በትውልድ ከተማዋ ባደረገችው የመጀመርያው የተሰጥዖ ውድድር ላይ ተመልክቷት ነበር፡፡ የሙዚቃ ፕሮዲውሰሩ ዴቪድ ፎስተር፤ ጃኪ ፒያኖ እንድትማር ከመገፋፋቱም በላይ ቫዮሊንም እንድትጫወት መክሯታል፡፡ በዚህም በሁለቱም የሙዚቃ መሳርያዎች ብቁ ችሎታ አግኝታለች፡፡
ጃኪ የአሜሪካ ጎት ታለንት ተሳትፏዋን ባጠናቀቀችበት ማግስት ከዴቪድ ፎስተር ጋር በመሆን ..ድሪም ዊዝ ሚ.. የተሰኘውን ሁለተኛ አልበሟን ሰራች፡፡ በዚሁ አልበም ከተካተቱ የሙዚቃዎች ስብስብ ከብሪቴን ጎት ታለንት አሸናፊዋ ሱዛን ቦይል ጋር ..ኤ ማዘርስ ፕሬየር.. በሚል በጋራ የተጫወቱት ዜማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወደደላት፡፡ አልበሙ ከ1 ሚሊዮን በላይ ቅጂ የተሸጠላት ሲሆን፤ በሽያጩ የፕላቲኒዬም ደረጃን በመጎናፀፍ ታዳጊዋን ለዚህ ደረጃ የበቃች የመጀመርያዋ ታዳጊ አርቲስት አድርጓታል፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ በሁለቱ አልበሞቿ በዓለም ዙሪያ እስከ ቅርብ ጊዜ ያገኘችው ሽያጭ 1 ሚሊዮን 320ሺ  በመድረሱም በአሜሪካ ጎት ታለንት የ5 ዓመታት ቆይታ ከፍተኛውን የአልበም ሽያጭ በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ አስገኝቶላታል፡፡
l11 ›ma ጃኪ ኢቫንቾ ..ሱፐር ሂውማን ነኝ ብለሽ ታስቢያለሽ?.. የሚል ጥያቄ ቀርቦላት ነበር፡፡ ..በጣም ይደንቃል፤ እኔ ስዘፍን የሚሰማኝ የ11 ዓመት ልጅ ድም ነው.. ብላ መለሰች፡፡ የሌዲ ጋጋን ዘፈኖች አዘውትራ እንደምትሰማና በተለይ ..ፖከር ፌስ.. የተባለ ዘፈኗን እንደምትወድ ከኤንቢሲ ቻናል ጋር ባደረገችው ቃለምምልስ ስትናገርም ዝነኛነት እምብዛም እንዳላስቸገራት ገልፃ ከቤቷ አልጋ ይልቅ የአውሮፕላን መቀመጫ ማዘውተሯን በፀጋ እንደተቀበለችው ተናግራለች፡፡ ትምህርቷን በኢንተርኔት እየተከታተለች መሆኗን አምርራ እንደምትጣላ የምትገልፀው ጃኪ፤ ጓደኞቿ በድምፃዊነቷ እያገኘች ባለችው ስኬት ብዙም ግድ እንደሌላቸው ማወቋ እንደተመቻትና ታዋቂ መሆን የሚፈጥረውን ትኩረት እንደማትወደው ተናግራለች፡፡ ድምፃዊነት ባይሳካላት ምን መሆን እንደምትፈልግ የተጠየቀችው ጃኪ ስትመልስ.. ሙዚቃ ባይሆንልኝ፤ ብፍ ደስ ይለኛል፡፡ የሙዚቃ ግጥም ወይም መጽሐፍ መፃፍ እፈልጋለሁ .. ብላለች፡፡
ጃኪ በአሜሪካ ጎት ታለንት ላይ ኦፔራዋን ስትጫወት በአማካይ እስከ 10.5 ሚሊዮን ተመልካች ይታደማት ነበር፡፡ በ10 ዓመቷ ባቀረበችው የኦፔራ ዘፈንም የዓለም ሪኮርድን ያስመዘገበች ሲሆን፤ ቀድሞ የነበረው ክብረወሰን ኤርያ ቴሶሊን የተባለች ታዳጊ በ12 ዓመቷ ያስመዘገበችው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአልበሙ ላይ የሰራቻቸውን ዘፈኖች የመረጡላት ቤተሰቦቿና የአሳታሚው ፕሮዱዩሰር ናቸው፡፡ ሆኖም የሷ ፍላጎትና አስተያየት ቅድሚያ እንደተሰጠው ትናገራለች፡፡ ጃኪ በሁለተኛ አልበሟ የሰራቻቸውን ዘፈኖች ልቧን እንደሚነኩ ትናገራለች፡፡ ..ኤንጅል.. የሚለው ዘፈኔ ራስን ስለማጥፋት የሚተርክ መሆኑ ስለሚያሳዝነኝ ስጫወተው በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ገብቼ ነው የምትለው ጃኪ፤ የግጥም ይዘቱ ለመስማት የሚከብድና የሚያሳዝን ነው ብላለች፡፡ታዋቂው የአሜሪካን አይዶል ፕሮግራም ዘንድሮ ለ11ኛ ዓመት የሚደረግ ሲሆን በውድድሩ ላይ የሚያሸንፉት አዳዲስ ኮከቦችና በልዩ ችሎታቸው ከፍተኛ ዝና የሚያገኙት በአልበም ሽያጩና በገቢ ስኬታማ ሲሆኑ ታይቷል፡፡ ከአይዶል አሸናፊዎቹ መካከል በውድድሩ 4ኛ ዓመት ላይ ያሸነፈችው ኬሪ አንደርውድ፤ በአልበም 12.3 ሚሊዮን፣ በዲጅታል ትራክ 18.5 ሚሊዮን ያሰራጨች ሲሆን የኮንሰርት ገቢዋ እስከ 67 ሚሊዮን ዶላር ተመዝግቦ አንደኛ ደረጃ አሰጥቷታል፡፡ በብሪቴን ጎት ታለንት ውድድር ከ2 ዓመት በፊት ባታሸንፍም ሁለተኛ ደረጃ አግኝታ የነበረችው የ49 ዓመቷ ሱዛን ቦይል ስኬትም የሚደንቅ ነው፡፡ ከሁለት ወራት በኋላ ሶስተኛ አልበሟን ለገበያ የምታበቃው ሱዛን ቦይል፤ አስቀድማ በሰራቻቸው ..አይ ድሪምድ ኤ ድሪም.. እና ..ዘ ጊፍት.. የተባሉ ሁለት አልበሟቿ በዓለም ዙሪያ በ30 አገራት ተደማጭ ከመሆናቸውም በላይ በ14 ወራት ውስጥ ከ14 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ተሸጠውላታል፡፡ኢትዮጵያዊቷ ሃና እና አሜሪካዊቷ ጃኪ
በኢትዮጵያ አይዶል እየተወዳደረች ያለችው ሃና ግርማና በአሜሪካ ጎት ታለንት ከፍተኛ ዝና በማግኘት ስኬት የተቀዳጀችው ጃኪ ኢቫንቾን በንር በማስቀመጥ ይህ ጽሁፍ ይጠቃለል፡፡ ሃናና ጃኪ 11 ዓመታቸው ነው፡፡ ሃና 7ኛ ክፍል በመደበኛ፤ ጃኪ 6ኛ ክፍል በሳይበር ይማራሉ፡፡ ሃና የጠፈር ተመራማሪ፤ ጃኪ ደራሲ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ሃና በ..ቶም ኤንድ ጄሪ..፤ ጃኪ በ..ፓንተም ኦፍ ዘ ኦፔራ.. ከኦፔራ ተዋውቀዋል፡፡ ሃና የሙዚቃ አሳታሚ ሆነ ማናጀር የላትም፤ ጃኪ ሁለት አሳታሚዎች፤ 16 ግራሚ የተሸለመ ፕሮዱዩሰር፤ ማናጀርና ሌሎችም በዙሪያዋ ተሰባስበዋል፡፡ ሃና ችሎታዋ ድም ብቻ፤ ጃኪ ግን ከድም ሌላ ፒያኖና ቫዮሊን ትጫወታለች፡፡ ጃኪ 2 አልበም ሰርታ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሸጣለች፤ የሃና ገና አልታወቀም፡፡

 

Read 2506 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:32