Tuesday, 01 November 2011 14:13

ቺኑዋ አቼቤ - ሥራቸው

Written by  ቀዳማዊ ሰሎሞ
Rate this item
(0 votes)

ቀጥሎ ከአቼቤ ልሂቅ ጥበባዊ ድርሳኖች መሀከል በሦስቱ ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ፡፡ እግረ - መንገዳችንንም የጠቢቡን የዘይቤ አጠቃቀም ሊቅነት፣ ንጥር አፍሪቃዊነትና ኪነ ጥበባዊ ኪሂሎት እንመዝን ዘንድ በቅንጭብ እንመልከት፡፡ 
ከ - አንትሒልስ ኦፍ ዚ ሳቫና
“… በመኸር ወቅት ሰማይና ምድር ከጣብቂያቸው ሳይላቀቁ፣ ጥዑም የሆነው የማለዳ እንቅልፍ ጫና ሲደብት፣ እንደመርግ በከበደው ሌሊት፣ የንጋት ወፍ ስትጮህ ገበሬውን ለማንቃት - በዚያ ቁርና ዳፍንት፡፡ ለመሆኑ ገበሬው እንቅልፍ እንደተጫነው ብትት ብሎ ነቅቶ ወደማሳው ይገሰግሳል ወይንስ በንጋት ወፋዋ ላይ መልሶ ይጮህባታል፣ “አፍሽን ዝጊ እባክሽ…

መንጋቱን ማን አባሽ ነው የነገረሽ? አንቺ ራስሽ አንድ ፍሬ በቆሎ ዘርተሽ፣ አረሙንስ አርመሽ ለመሆኑ ታውቂያለሽ - ምን አዝምረሻል በሕይወትሽ?” ብሎ ያበሻቅጣት ይሆን? ፈጽሞ! በእርግጥም አፈር መስሎ በመሥራት፣ ጉንጩን ሞልቶ ለመብላት የሚጥር ታታሪ ገበሬ፤ ከሌሊት ወፍዋ ጋር እንካ ሰላንቲያ አይገጥምም፡፡ ጩኸቷን መና አያስረቀውም፡፡ ይነቃል - ይነሳል - ትዕዛዟንም ይፈጽማል፡፡
“ለመሆኑ በእስከዛሬው ሕይወታችሁ ይህን ጉዳይ አስባችሁበት ታውቃላችሁ? እኔ ግን እውነቱን ልንገራችሁ፣ ምንተስኖት የሆነው አምላክ ዓለማችንን በዚህ መልክ ነው ከፋፍሎ የፈጠራት፡፡ ሁሉም የየራሱንና የግሉን፤ የንጋት ወፍዋም ጩኸቷን፣ ገበሬውም እርሻውን፡፡
“ሰማያዊው ጌታ ለአንዳንዶቹ፣ የመንቂያው ሰዓት የመድረሱን ትንቢት የመናገር ስጦታ ይሰጣቸዋል፡፡ ለሌሎቹ ደግሞ የጥሪውን ደወል ሰምተው የመንቃቱን ብርታት፣ በሚንተገተግ የደም ዑደት የመነሳት፣ ባጋተ ወኔ ወደ ትግሉ አውድማ የመዝመት፣ ከጠላት ጋር ጉርቦ ለጉርቦ ተናንቆ የመሟሟት…ተልእኮ ያድላቸዋል፡፡ ከእነዚህ የተለዩ ደግሞ አሉ - አንገታቸውን ደፍተው፣ ጦርነቱ እስኪያልቅ ድረስ አድብተው፣ ብዕር ከወረቀት አዋደው፣ ታሪክ ቀርፀው ለማስቀረት የታደሉ፡፡
“የውጊያውን መጀመር የሚያበስረው የእምቢልታ ድምጽ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለው፤ የመተረኩም ጉዳይ እንደዚያው …ሁሉም በየፈርጁ የየራሱ ረቤታ አለው፡፡ ከእነዚህ በቅደም ተከተል ከተንሰላሰሉ ድርጊቶች መሀል አንዱን ብናጣ ታሪካችን ሰንካላ ይሆናል፡፡ ነገር ግን “ከእነዚህ ክስተቶች ውስጥ የትኛው ሚዛን ይደፋል?” ብላችሁ ብትጠይቁኝ መልሴን በልበ ሙሉነት እሰጣችኋለሁ፡፡ ታሪክ ነው ከምንም ነገር በላይ የሚልቀው - ታሪክ ነው የሚያኮራው - ይሄው ነው፡፡ በአፍላ የወጣትነት ዘመኔ ይህን መሳዩን ጥያቄ አንስታችሁልኝ ቢሆን ኖሮ፣ ውጊያውን ለመምረጥ ቅንጣት አላቅማማም ነበር፡፡ ዳሩ ግን ዕድሜ ደጉ በቀኝ እጁ አንዳች አዲስ ባህርይ ሲለግሰን …በግራ እጁ ደግሞ ንቡር ማንነታችንን ሲነጥቀን እነሆ እስከዛሬ አለነው፡፡
በኮበሌነት ዘመን እንደሚሆነው ሳይሆን አረጋውያን ደመ - በራድ ናቸው፡፡ እናም ተስፋው ነጥፎ፣ ወኔው ተገፎ፣ ድኩም ጉልበቱን አቅፎ፣ ቀሪ የዕድሜ ዘመኑን ለመግፋት ይገደዳል - አዛውንቱ፡፡ ታድያ አቅሙ ቢከዳውም በእግረ - ሕሊናው ይኳትናል፤ በዓይነ - ልቦናው ይጓዛል፣ አስተውሎቱ ይመጥቃል፣ የዕይታው አድማስ ይሰፋል፣ ከጽንፍ - ጽንፍ ያማትራል…
“…የእኛ ሰዎች ለሴት ልጆቻቸው ስም ሲያወጡ “ኒኮሊኮ” ብለው መሰየማቸው ይህን በማወቃቸው ይመስላል - “ማስተዋል ደጉ” እንደማለት፡፡ ለምን - ? ምክንያቱም ከትግሉም ሆነ ከታጋዩ ዕድሜ አንጻር ሲሰላ የታሪክ እድሜ የትየለሌ ነው፡፡ ልጆቻችን ተጨፍነው በየሰው ደጅ ለምጽዋት እየዞሩ “በእንተስማለማርያም” የሚሉ የእኔ ብጤዎች ከመሆን የሚያድናቸው እኛ አባቶቻቸው የምናቆይላቸው አኩሪ ታሪክ ነው - ታሪክ ብቻ ነው የሚታደጋቸው፡፡ ታሪክ ነው ዋቢያቸው …አዳኛቸው…ጠባቂያቸው፡፡ ታሪክ የሌለው ዜጋ ዓይነ - ሥውር ነው - ልበ ሥውርም ጭምር፡፡ ልበ - ሥውራን የታሪክን ክቡርነት የት ያውቁታል? እኛስ ብንሆን ታሪክን መች ጨበጥነው፡፡ ይሁን እንጂ ታሪክ ነው የሚመራን፣ ማንነታችንን የሚያሳየን፣ ሰብዕናችንን የሚቀርፀን፡፡ ይኸው ቀዳማዊ ማንነታችን ነው ከእንስሳት የሚለየን፡፡
ከ-“ቲንግስ ፎል አፓርት”
“የንጉሥን አፍ የሚያስተውል ሰው” አሉ አንድ አረጋዊ “የእናቱን ጡት የጠባ አይመስለውም፡፡” አዛውንቱ ይህን ያሉት ትፈሳ ዶሮ ሳይኖረው ከትቢያ ተነስቶ በሀብት ስለናጠጠውና በወገኖቹ አናት ላይ ቂብ ስላለው ስለአኮንክዎ ለመናገር ፈልገው ነው፡፡ ሰውዬው የአኮንክዎን ክፉ የሚመኙ ሰው ሆነው አይደለም፡፡ እንዲያውም ጥሮ ግሮ ሕይወቱን ለማሻሻል ባደረገው ትጋትና በጨበጠው ስኬት የሚያከብሩት ሰው ናቸው፡፡ ሆኖም በኑሮ ከእሱ ለሚያንሱ ሰዎች በሚያሳየው ንቀት ይንቁታል ይበሽቁበታል፡፡
“ከአንድ ሣምንት በፊት በተካሄደ የቤተ ዘመድ ስብሰባ ላይ ሲወያዩ ነበር ከአንዱ ተሰብሳቢ ጋር አኮንክዎ የተጋጨው፡፡ አጅሬ አኮንክዎ ሆዬ፣ የሰውዬውን ፊት እንኳን በቅጡ ሳያየው ይህ ስብሰባ የተፈቀደው ለወንዶች ነው፡፡” በሚል የንቀት ቃል ነበር በአግቦ የተናገረው፡፡ ይሄኔ ሰውዬው የሚናገረው ጠፋው፡፡ በኦኮንክዎ ቤት አጠይሞ ሰውዬውን እንደሴት በመቁጠር በነገር መውጋቱ ነበር፡፡ መቼም የሰው ልጆችን መንፈስ እያኮሰመኑ የመግደልን ጥበብ አኮንክዎ ተክኖታል፡፡
“በቤተ ዘመድ ስብሰባው ላይ የነበሩት ተሰብሳቢዎች ሁሉ በአንድነት “ሴት” ተብሎ የተሰደበውን ሰው ወገኑ፡፡ ከዕድሜው ዝቅ አድርጐ የሰጣቸው አዛውንት ግን፣ በጐ አሳቢ ወገኖች ሁሉ በተለመደው ግዙፍ ትዕግስታቸው እንዲፀኑ ገዘቱ፡፡ በመጨረሻም አኮንክዎ በፀያፍ አንደበቱ ለፈፀመው በደል ይቅርታ ጠየቀና የስብሰባው ሥነ - ስርዓት ቀጠለ፡፡
“እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የእጁን ጭብጥ ዘርግቶ ለአኮንክዎ በፀጋ ያስረከበው ማንም ሰው አልነበረም፡፡ ራሱ ኦኮንክዎ ነው ድርሻውን አስረግፎ የወሰደው፡፡ የድህነትን ሰንሰለት በእልህ አስጨራሽ ጥረታቸው በጣጥሰው በአሸናፊነት የተወጡ ሰዎች በዕድል ድህነትን አመለጡ ሊባሉ አይገባም፡፡ በአጋጣሚ መክበር አይቻልም፡፡ የድካሙን ፍሬ ጐንጩን ሞልቶ ለመብላት የበቃ ሰው ቢኖር ኦኮንክዎ ነው - ድህነትን ድል ያደረገ ብርቱ ሰው፡፡
“ልጅ ሳለ ከጫፉ የሚደርስ ተፎካካሪ የሌለው የነፃ ትግል አሸናፊ ነበር፡፡ ያ በዕድል አልነበረም፡፡ ከራማው ወይም ፈጣሪው እየደገፈው ነው ሊባል ይችል ይሆናል፡ነገር ግን በኢቦ ጐሣ ተወላጆች ዘንድ “አንድ ብርቱ ሰው ለሽንፈት አልበገርም የሚል ቆፍጣና መንፈስ ካለው፣ ከራማው አይበገሬነቱን ያፀድቅለታል” የሚል የዘልማድ አባባል ነው፡፡ አክንክዎ በፍርጥምታ ሽንፈትን “እምቢኝ” አለ፤ ከራማውም ይህንኑ ጽናቱን አጸደቀለት፡፡ ከዚያ በኋላማ ከራማው ብቻ ሳይሆን ሀገሬውም ጭምር የሰው ልጅ ከጣረ የድካሙን ፍሬ እንደሚበላ አመነ፡፡ አመርቂ ውጤት የሥራ ፍሬ መሆኑም የሕዝቡ እምነት ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ አንዲት የኢቦ ሴት በሰው እጅ በመገደሏ ሳቢያ የገዳዩ ወገኖች አንድ ኮበሌና አንዲት ኮረዳ ጉማ እንዲከፍሉ አለበለዚያ ግን ምድሪቱ በጦርነት እሳት እንደምትጋይ በዘጠኝ መንደር ነዋሪዎች የጸደቀው፡፡ የክተት አዋጁን ጦማር እንዲያደርስ ደግሞ ጀግናው አኮንክዎ ነበር የተመጠረው፡፡”
ከ-ሞርኒንግ የትኦን ክሪኤሽን ዴይ
“በተዋበ ቋንቋ የሚቀርብና በጣፋጭ የአተራረክ ዘይቤ የሚንኳለል ተረት ማድመጥ የልጅነት ቀልቤን ያማልለው ነበር፡፡ በልጅነቴ የትውልድ መንደሬ አረጋውያን በኩል በኢግቦ ቋንቋ ያቀርቡልኝ የነበረውን የተረት ጅረት እየሰማሁ አድጌአለሁ፣ ኋላም ስምንት ዓመት ከሞላኝ በኋላ በእንግሊዞች ቋንቋ የሰማሁት ተረት እስከዘላለሙ ይታወሰኛል፡ሆኖም ምክንያቱን በውል አይቼ ባላውቀውም ከእንግሊዘኛው ይልቅ አያሌ የኢግቦ ቃላትን በሰለጠነ አንደበት መናገር እችላለሁ - በጽሑፍ ከሆነ ግን እንግሊዘኛው እንደሚቀናኝ አውቃለሁ፡፡ በዚህ የተነሳ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ለመሆኑ በቃሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በኢግቦ ቋንቋ የመፃፍ ችሎታዬም የተዋጣ እንደሆነ ሀሳባቸውን ለግሰውኛል፡፡ አንዳንዴም ወደ ግል ሕይወቴ በመግባት በየትኛው ቋንቋ ሕልም እንደማልም ጭምር ይጠይቁኛል፡፡ በሁለቱም ቋንቋዎች እኩል እንደማልም ስነግራቸው ግን አያምኑኝም - በፍፁም፡፡”
ስለ ቺኑዋ አቼቤ ስራዎች ጥቂት ብለን ጽሁፋችንን ብንቋጭ ወደድን፡፡
ምንም እንኳን በርዕሱ ላይ ጭጋጋማ ድባብ ቢያጠላም “ኢንትሂልስ ኦፍ ዚ ሳቫና” የኢግቦዎችን ብሂል ይዘክራል - በበረሃማው የሳር ምድር ላይ የተዛመተው ሰደድ እሳት አልፎ አልፎ የሚታዩትን ጉብታዎት መጧቸው አልፏል - ይኸም የሰደዱን አጎዳ ያስታውሳል - በእግረ ትዝታ ያስኳትናል - ያለፈውን እያስቃኘ መጪውን ያመላክታል...
“አንትሂልስ ኦፍ ዚ ሳቫና” ጠሊቅ ሂሳዊ ንባብ የሚሻ ኪነ-ጥበባዊ ውጤት ነው፡፡ አንድ ምዕራብ አፍሪቃዊ የመጽሐፍ ቅኝት አድራጊ፤ ስለመድበሉ ሲገልጡ “. . . የታለመለትን ግብ በሚያመረቃ ደረጃ የመታ የኪነጥበብ እሴት” በማለት በውዳሴ ጠበል አራጥበውታል፡፡ ይኸው መጽሐፍ ሦስት ተራኪዎች ሲኖሩት ብዕረኛው የተጠቀሙበት ቋንቋ ደግሞ፤ ከከፍተኛው መደብ የእንግሊዞች ልሣን አንስቶ፣ ጉራማይሌ ተናጋሪዎችን አካቶ፣ አቼቤ በልጅነት የዕድሜ ዘመናቸው እስከቀሰሟቸው የቤተክህነት ጥቅሶች ድረስ ያሉትን የአነጋገር ፊሊጦች ያካተተ ነው፡፡ በማህበራዊውና በፖለቲካው መስክ የተደረጉት ፍተሻዎችም ቢሆኑ እንደፈርጥ በሚንተገተጉና በምፀታዊ ሕብር በቀለሙ ውብ ቃላት ተከሽነዋል፡፡
“ቲንግስ ፎል አፓርት” የተሰኘው የአቼቤ የበኩር ሥራ ጭብጥ በደራሲው ምንዥላቶች ሕይወት ዙሪያ የተጠነጠነ ሲሆን በ18ኛው ምዕተ-ዓመት መካተቻ ግድም በግፉአን ጥቁር የሀገሬው ተወላጆች ላይ ሚስዮናዊያንና ቅኝ ገዢዎች የጫኑባቸዉን አሰቃቂ የግፍ ቀንበር በጥልቀት ይዳስሳል፤ ተገቢውን የክብር ሸማ ለወንዝ ልጆች ያላብሳል፡፡ እንደራሳቸዉ እንደፈጣሪው አባባል ከሆነ ይህ ሥራቸዉ “ያለፈውን እኔነት አንጥሮ የሚያወጣ፣ ማጋጣውን ወጣት በሥርዓት አርቆ ወደ ጤናማው ማህበረሰባዊ ሕይወት የሚያመጣ ልብወለድ ነው”
መቼቱ በነፃነት ዋዜማ ግድም ሌጐስ ከተማ ውስጥ ከተዋቀረውና “ኖ ሎንገር አት ኢዝ” ከተባለው መጽሐፋቸው ቀጥሎ በ1920 ዓ.ም ወደነበረው የኢግቦ መንደር እንደገና በመመለስ የማህበረሰባቸዉን መንፈሳዊና ፖለቲካዊ ድቀት የቃኙበትን “የእግዜር ቀስት” የተባለውን ድረሳናቸውን አበረከቱ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ በንቅዘት ተበሻቅጦ በወታደራዊ መኮንኖች አመጽ ስለተፈነገለው መንግስት ያወሱበትን መድበላቸውን ከብሩህ አዕምሮአቸው አንቅተው የፈጠሩት፡፡ ይህንኑ ከቅድመ አርነት አፍሪቃ ጋር መልሶ በማቆራኘት ሰምና ፈትል ያደረጋቸውን የብዕራቸውን ውጤት “ኤ ማን ኦፍ ዚ ፒፕል” ብለው በመሰየም ለተደራሲያን አቀረቡት፡፡ ስለዚሁ መጽሐፍ ከተሰነዘሩት አስተያየቶች መሀል አንድ ሁለቱን እንመልከት፤
“አንዳንድ ሸፍጥን ሥራዬ ብለው የተነሱ ፖለቲከኞች በሕዝብ ስም የሚፈጽሙት ገደብ የለሽ ደባ በተዋጣለት ሽሙጥና ሽንቆጣ ይፋ ወጥቶ ተዝረጥርጧል፡፡ . . . ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገሀዳዊው ዓለም ሕይወት እጅግም ሳያፈነግጡ የተሳሉ አስቂኝ ገፀ-ባህሪይ ናቸው፡፡ አጭበርባሪ፣ ወስላታ፣ ምላሰኛ፣ ፌዘኛ የሆኑ ሰው፡፡ ከእርሳቸው በተቃርኖ የቆመውና በአንደኛ መደብ ትረካ ራሱን የሚያስተዋውቀው ወጣቱ ኦዲሊ ደግሞ ምንም እንኳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰው ቢሆንም ቁርጠኛ፣ ሀቀኛና ብርቱ ተፋላሚያቸው ሆኖ ተስሏል፡፡ የኦዲሊ ቅን ልቦና፣ የቁርጥ ቀን ልጅነት፣ ልበ-ሙሉነትና ሳንካአልባነት ለጥበባዊው ሥራ ምጡቅነት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ሆኖም ራሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመሆን ምኞቱ በታሪኩ አመሻሽ ላይ መክኖበታል፡፡”
(አንገስ ዊልሰን - በ”ኦብዘርቨር” ላይ ከሰነዘሩት አስተያየት የተቀዳ፡፡)
“ይህ የአቼቤ ልቦለድ በአፍሪቃ ውስጥ የሚገኝ አንድ የመንግስት ሹመኛ ይፈጽመው የነበረው ቅሌትና ክፋት በምሬት የተኮነነበት የፈጠራ ሥራ ነው . . . ያለፈውን ማህበረሰባዊ ወግና ልማድ ከሚያወድሱት ቀደምት ድርሳኖቻቸው እኩል የዜጐችን ሁለንተናዊ ሕይወት እንደመስተዋት በሚያሳይ ጥዑም ገለጻ የተከሸነ ሸንቋጭ ልቦለድ ነው፡፡”
(ዲ.ኤን.ኤን ጆንስ በኒው ስቴትስማን ላይ ካሰፈሩት ግምገማ የተቀነጨበ፡፡)
(የዘመን አቆጣጠሮቹ በሙሉ እ.ኤ.አ ነው)ቀጥሎ ከአቼቤ ልሂቅ ጥበባዊ ድርሳኖች መሀከል በሦስቱ ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ፡፡ እግረ - መንገዳችንንም የጠቢቡን የዘይቤ አጠቃቀም ሊቅነት፣ ንጥር አፍሪቃዊነትና ኪነ ጥበባዊ ኪሂሎት እንመዝን ዘንድ በቅንጭብ እንመልከት፡፡
ከ - አንትሒልስ ኦፍ ዚ ሳቫና
“… በመኸር ወቅት ሰማይና ምድር ከጣብቂያቸው ሳይላቀቁ፣ ጥዑም የሆነው የማለዳ እንቅልፍ ጫና ሲደብት፣ እንደመርግ በከበደው ሌሊት፣ የንጋት ወፍ ስትጮህ ገበሬውን ለማንቃት - በዚያ ቁርና ዳፍንት፡፡ ለመሆኑ ገበሬው እንቅልፍ እንደተጫነው ብትት ብሎ ነቅቶ ወደማሳው ይገሰግሳል ወይንስ በንጋት ወፋዋ ላይ መልሶ ይጮህባታል፣ “አፍሽን ዝጊ እባክሽ… መንጋቱን ማን አባሽ ነው የነገረሽ? አንቺ ራስሽ አንድ ፍሬ በቆሎ ዘርተሽ፣ አረሙንስ አርመሽ ለመሆኑ ታውቂያለሽ - ምን አዝምረሻል በሕይወትሽ?” ብሎ ያበሻቅጣት ይሆን? ፈጽሞ! በእርግጥም አፈር መስሎ በመሥራት፣ ጉንጩን ሞልቶ ለመብላት የሚጥር ታታሪ ገበሬ፤ ከሌሊት ወፍዋ ጋር እንካ ሰላንቲያ አይገጥምም፡፡ ጩኸቷን መና አያስረቀውም፡፡ ይነቃል - ይነሳል - ትዕዛዟንም ይፈጽማል፡፡

(የዘመን አቆጣጠሮቹ በሙሉ እ.ኤ.አ ነው)

Read 1699 times Last modified on Tuesday, 01 November 2011 14:20