Tuesday, 01 November 2011 14:20

ኩበት በሌለበት ጭስ ከየት ይመጣል

Written by  በፍቃዱ አባይ
Rate this item
(0 votes)

ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍ መንስኤ የሆነኝ ባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃው የአዲስ አድማስ ዕትም ነው፡፡ በጥበብ አምድ ላይ ተጋባዥ የነበረችው ተዋናይት ሮማን በፍቃዱ ስለፊልምና የፊልም ገቢ እንዲሁም የፊልም ሰሪዎች በተመልካች መቀደምንና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠችውን ቃለ-ምልልስ አነበብኩት፡፡ ከዚያም ከዚህ ቀደም ሳስባቸው የነበሩ የፊልሞቻችንና የፊልም ስራዎቻችንን የዓመታት ትዝብቶቼን ደፍሬ እከትባቸው ዘንድም መነሻ ሆነኝ፡፡ በግሌ በቅርብ ግዜያት ተሰርተው ለተመልካች ከቀረቡ ሐገርኛ ፊልሞች መሐከል በጣም ከወደድኳቸው ጥቂት ፊልሞች አንደኛው የሆነውን “ባለታክሲው”ን ፊልም የሰራችውና የተወነችው ሮማን በፍቃዱ በዚህ አምድ በመጋበዟ መደሰቴን መደበቅ አልሻም፡፡ ሮማንና ባለቤቷ ሚኪያስ መሐመድ በጋራ የተወኑበት ባለታክሲው የተሰኘው ፊልም በኔ ብቻም ሳይሆን በቅርብ ወዳጆቼም ዘንድ ስምምነት የደረስንበት ቆንጆ ፊልም በመሆኑ ልናመሰግናቸው ግድ ይለናል፡ የተበላሸውን ለመጠገን፤ የደከመውን ለማበርታት መልካም የሰሩትን ማመስገን የተሻለ ዘዴ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ጥቂት አስደሳች ፊልሞችን ለሰሩልን ባለሙያዎች እጅ መንሳት እሻለሁ፡፡ ነገር ግን በዚህ ቃለ-ምልልስ መሀል የተሰነዘረችውን የተመልካች ከፊልም ሰሪዎች መቅደም ጉዳይንም በደንብ ልንነጋገርበት የሚገባ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ለዚህም የፊልም ትውውቃችንንና አሁን የደረስንባቸውን ኩነቶች በማያያዝ ጥቂት የፊልማችንን ዕድገት የገቱ የችግር ሰበዞችን እየመዘዝን እንጨዋወታለን፡፡

የፊልም ኢንዱስትሪ 
በርካታ ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ስለ ፊልም ሲናገሩ በንግግራቸው ጣልቃ “የፊልም ኢንዱስትሪያችን . . .” ሲሉ አደምጣለሁ፡፡ ይህ አነጋገር በራሱ ስለ ኢትዮጵያ ፊልም ስንነጋገር ማንሳት የሚገባን ቀዳሚ ህጸጽ ይመስለኛል፡፡ አሁን ባለንበት የፊልም ደረጃ ኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪውን የሚያስጠራ ተሳትፎ ውስጥ ስለመገኘቷ ሲበዛ እጠራጠራለሁ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (Secretary of state) የሚል መጠሪያ ያገኘውን ሆሊውድንና ህንዶች ማንነታቸውንና፤ ባህላቸውና፤ የተሳሳተ ስዕላቸውን ለመለወጥ የቻሉበትን ትልቁን ቦሊውድ (Bollywood) ትተን፣ ወደ አፍሪካ ብንመጣ እንኳን በኢንዱስትሪው ሰፊ ድርሻ እንዳላት ከሚነገርላት ናይጄሪያ አንጻር ብዙ ርቀት ወደኋላ መቅረታችንን የዘነጋን ይመስለኛል፡፡ የፊልም ኢንዱስትሪያቸውን Nollywood የሚል መጠሪያ የሰጡት ናይጄሪያውያን፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሶስተኛው እርከን ላይ ተቀምጠው እንኳ ስለፊልም ኢንዱስትሪያቸው ብዙ ችግሮችን ይነቅሳሉ፡፡ በአማካይ 10 ፊልሞችን በቀን ለገበያ እያቀረቡ በዓመት 1.2 ቢልዮን የናይጄሪያ ኒያራ እያንቀሳቀሱ፤ በሰሜን አሜሪካ፤ በእንግሊዝ፤ በአውሮፓና እስያ ከፍ ያለ ገበያ እያላቸው እንኳን ስለፊልም ኢንዱስትሪዎቻቸው አፋቸውን ሞልተው ለመናገር ገና ስለመሆናቸው ይሞግታሉ፡፡ ታድያ በጅማሮው መስመር ላይ የሚገኘው ፊልማችን ከመቼውና እንዴት ወደ ኢንዱስትሪው ማማ እንደዘለቀ ቢያንስ ለኔ ግልጽ አይደለም፡፡ ይህ ተያይዞ ገደል የመግባት ፋሽን መሰል አነጋገር በሰፊው መለመዱም ስለ ፊልም ኢንዱስትሪ ካለማወቃችን ወይስ የተለመደ ድፍረታችን ውጤት ይሆን?
አንድ ዓላማና ግብ አስቀምጦ የኢትዮጵያ ፊልም ለተመልካቹ ምን ሊያበረክት ይገባል? የሚሉ ጥያቄዎች ባልተመለሱበትና ለሐገር መልካም ምስል መከሰትና የኢኮኖሚ ድርሻ የበኩሉን ለመወጣት ባልተሰራበት፤ እንዲሁም ግልጽ አካሔዶችን በማናይበት ሁኔታ ስለፊልም ኢንዱስትሪያችን ስናወራ ልንጠነቀቅ የሚገባን ይመስለኛል፡፡ ይህ በጅምር ላለው ፊልማችን የዕድገት ማነቆ መብዛት አንዱ ምክንያት ይመስለኛል፡ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ መጠሪያው ማን ይሰኛል? ስም አልባው ኢንዱስትሪ ወይስ . . .
ትርፋማ ቢዝነስ ተደርጎ መወሰዱ
ፊልማችን በተፈለገው መጠን እንዳይጓዝና ተመልካቹ ይቀድመው ዘንድ እንደ አንድ ችግር ያገኘሁት ፊልምን አዋጪ ቢዝነስ አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ ፊልምን ከመስራታቸው በፊት ስለፊልም አሰራር ጥቂት እንኳን ዕውቀትም ሆነ ልምድ የሌላቸው ደፋሮች በሰፊው ሲሳተፉበት አስተውላለሁ፡፡ ፊልምን ለመስራት በቂ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ከገንዘቡ በላይ የሆነው የፊልም ዕውቀት መሰረት፤ ተሰጥኦና ችሎታ ወሳኝነት እንደሚኖራቸው አምናለሁ፡፡ ፊልምን አስተምረው ብቁ የሚያደርጉ ተቋማት ያለመኖራቸው አንድ ችግር መሆኑን አውቃለሁ፡፡ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የትምህርት ተቋማት በዚህ በኩል ብዙ ቢጠበቅባቸውም ምንም እገዛ ያለማድረጋቸው የሚያሳስብ ስለመሆኑም እስማማለሁ፡፡ ያም ቢሆን ግን ስለምንፈልገው ሙያ ዕውቀትን የምንገበይባቸው መንገዶች በዘመነ መረጃ (info-tech-era) ሰፊ እንደሆኑ እገምታለሁ፡፡
በዚህ ረገድ ስለሙያው እየኖሩ ያሉና ስራዎቻቸው ባህር መሻገር የቻሉላቸው ጥቂት ወጣትና አንጋፋ ባለሙያዎችን ለማየት በመቻላችን ለእነዚህ አርአያዎቻችን አክብሮቴን እገልጻለሁ፡፡
ከዚህ በተለየ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት የማነጋግራቸው የፊልም ሰሪዎች ፊልም አዋጪ ቢዝነስ ስለመሆኑ ያወጉኛል፡፡ ህልማቸውም ግባቸውም ትርፍን ያማከለ ብቻ ስለመሆኑ ሲነግሩኝ ይገርመኛል፡፡ ማንም በስራው መጠቀሙና ማትረፉ የተለመደና የሚጠበቅ ቢሆንም የአንድ ወቅት ገቢ ማግኛ ብቻ ሲሆን ማየት ግን ለፊልማችን ችግርን እንጂ ትርፍን አያመጣልንም፡፡ እነዚህ ገንዘብን ብቻ ማዕከል አድርገው የተደባለቁት በመስኩ ያላቸው እምነት ጎደሎ መሆኑን ከምረዳባቸው መለኪያዎች ተጠቃሹ፣ በስራው ላይ ከአንድ ቢበዛ ከሁለት ጊዜ በላይ ሲሳተፉ ያለማየቴ ነው፡፡ ግለሰቦቹ መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው ትርፍ በመሆኑ ወደ መሰል አትራፊ ጎራ በአስገራሚ ፍጥነት ይሸጋገራሉ፡፡ በአንድ ወቅት ለፊልም ስራ ዕድገት እንሞታለን እንዳላሉ በመሰል አትራፊ ሌላ ስራ ገብተው የሙያው ኤክስፐርት መስለው ይታያሉ፡፡ ይህ መሰሉ በሁሉም የሙያ ዘርፎች ጥልቅ የማለት አባዜ ደግሞ በምናከብራቸው ባለሙያዎቻችንም ላይ መታየቱ ይበልጥ ያሳስበኛል፡፡ ዘፈን ሲወደድ ሲዲ የሚያሳትሙ፤ቴአትር ተመልካች ሲበዛ ወደቴአትር የሚዞሩ፤ ግጥም አድናቂው ሲበዛ ገጣሚ የሚሆኑት ሁሉ አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ዘመኑ የፊልም ወረት አዙረዋል፡፡ ምክንያቱም ቢዝነስ ነዋ፡፡
ተመልካች ወደፊት ፊልም ሰሪዎች ወደኋላ
ይህ ርዕስ ጥቂስ ስኬታማ ስራዎችን ለተመልካቹ ለማቅረብ የቻሉትን ባለሙያዎች አይመለከትም፡ ብዙዎቹን ፊልም ሰሪዎች ግን በግልጽ ይመለከታል፡ ብዙውን ጊዜ የምመለከታቸው ሐገርኛ ፊልሞች ከማዝናናት ይልቅ ማናደዳቸው ይብሳል፡፡ ከፊልሙ ታሪክ (Story)፤ መቼት (Setting)፤ ከጭብጥ (team)፤ ከገጸ - ባህሪያት ውክልናና (Characterization) መረጣ (audition)፤ ከአልባሳት (Costume)፤ ከሜክአፕ፤ ከድምጽና ምስል ጥራትና ከመሳሰሉት መሰረታዊ የፊልም አላባውያን (elements) አንጻር ጉድለቶች ይስተዋሉባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ፊልሞች ዘውጋቸው (genre) ኮሜዲ ተብሎ አስፈሪ ሆነው ይገኛሉ፡፡ አዝናኝ ተብለው አሸባሪ ይሆኑብናል፡፡ እስከአሁን ካየኋቸው ፊልሞች አብዛኞቹን የታሪኩ አጋማሽ ላይ ከመድረሴ በፊት መጨረሻቸውን አውቀዋለሁ፡፡ የታሪክ፤ የገጸ-ባህሪያትና የመቼት ትውቂያ፤ የታሪኩ ማደግ (rising) ጡዘትና (Climax) ፍጻሜ (resolution) በየስንት ደቂቃውና እንዴት መከወን እንዳለበት ያለማወቅ ችግሮችም በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም፡፡ በተጨማሪም የፊልምንና የቴአትርን ልዩነት ካለማወቅ በፊልም አተዋወን ላይ የሚታየው ህፀፅም ከመሰረታዊ ችግሮቻችን ውስጥ ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ችግሮች እኔ ብቻ ሳልሆን በበርካታ የፊልም ተመልካቾች ዘንድ ሰርክ እየተነሱ የሚጣሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ተመልካች ወደፊት ፊልም ሰሪው ወደ ኋላ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች መካከል በትውውቅ መስራት፤ ባለሙያን ያለማማከርና፤ ዕውቀት አልባ ድፍረት ይጠቀሳሉ፡፡
ስራን መጠቅለል (monopolize)
አሁን አሁን በተወሰነ መልኩ እየቀነሰ የመጣ የሚመስለው በሁሉን አዋቂነት ሥራን የመጠቅለል አባዜ ለፊልማችን እድገት አንደኛው ማነቆ ሆኖ ይታየኛል፡፡ በአንድ ፊልም ላይ ከስክሪፕት ጽሑፍ እስከ ማስታወቂያ ንባብ ድረስ የአንድ ግለሰብ መንገስ ከጥበቡ ልናገኝ የሚገባንን ትሩፋት እንድናጣ አድርጐናል፡፡
ፊልም በባህሪው የቡድን ስራ (team work) መሆኑ እየታወቀ ይህንን መሰረታዊ መርሕ በጣሰ መልኩ የአንድ ግለሰብ ሁሉን አዋቂ መምሰል በትክክልም ልንኮንነው የሚገባ ህጸጽ ነው፡ በአርአያነት የሚጠቀሱትን የሰለጠኑ ሀገራት የፊልም አሰራር ሂደትን በቀላሉ ብንመለከት እንኳን ፊልሞቻቸው ዓለም አቀፍ ዝናቸው ሊናኝና ተቀባይነታቸው ሊሰፋ የቻለው ለፊልም ስራ በጋራ የከፈሉት ሙያዊ አስተዋጽኦ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በትውውቅ፤ በዝምድና፤ ወጪን ለመቀነስ በሚል ሰበብና በሌሎች አጥጋቢ ባልሆኑ ምክንያቶች ስራን መጠቅለልና ለሌሎች ያለማካፈል አባዜ፣ ፊልማችን እንዲደርስ ለምንፈልግለት ደረጃ በፍጥነት ያለመድረስ ተጨማሪ ማነቆ ስለመሆኑ አምናለሁ፡፡
የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ህይወት ያለመዳሰሱ
በኢትዮጵያውያን ፊልም ሰሪዎች ዘንድ ከሚያሳዝኑኝና ከሚያስቆጩኝ ችግሮች መሐከል የአብዛኛዎቻችንን ህይወት የሚዳስሱ ፊልሞችን በብዛት አለማግኘቴ ነው፡፡ ታሪኮቻቸው የጋራ እሴቶች (common value) ቢይዙ እንኳን የመቼታቸው፤ የገፀ ባህሪያት ውክልናቸውና መሰል አላባውያን መሰረት የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ህይወት የሚወክሉ አይደሉም፡፡ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰባችን ክፍሎችን በሚያንፀባርቅ መልኩ የፊልሞቻችን ቀረጻዎች የተንደላቀቀ የህይወት ዘይቤ (Luxury life style) ላይ ያተኩራሉ፡፡ ስለፍቅር፤ ምቀኝነት፤ የወንጀል ድርጊት፤ በቤተሰብ መሐከል ስለሚፈጠሩ ያለመግባባቶች እና መሰል ማህበራዊ ስንክሳሮቻችን ላይ የሚያጠነጥኑት ፊልሞቻችን፤ ዝቅተኛውን የህብረተሰብ (majority) ክፍል ያለማማከላቸው እንደ አንድ ችግር ይታየኛል፡፡ ኢትዮጵያዊ ፊልም እኔን ሲያሳየኝ፤ ስሜቴን ሲኮረኩረኝ፤ ይህ የኔ ትክክለኛ ታሪክ ነው ሲያስብለኝ ነው ለማየት የምናፍቀውም፡፡ ግራውንድ ፕላስ መኖሪያ ቤት (G+1)፤ ዘመናዊ አውቶሞቢል ወዘተ ለፊልም ስራ ውበትን ከመጨመር ውጪ የአብዛኞቻችንን ህይወት እንደማይወክል እሙን ነው፡፡ ሁለት ብር ኪሳቸው ይዘው በፍቅር የሚኖሩ፤ ኑሮን ለማሸነፍ ላይ ታች የሚሉ፤ በማህበራዊ ህይወታቸው የጐለበቱ፣ በአንበሳ አውቶብስ አልያም በሚኒባስ (mini bus) የሚጓዙ ገፀ ባህሪያት እንዴት ናፍቀውኛል መሰላችሁ?
የመንግስት ስስ አመለካከት
ፊልምና የኢትዮጵያ መንግስታት ያላቸው ቁርኝት ያን ያህል ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ለ17 ዓመታት ሀገሪቷን ያስተዳደራት ደርግ ከሚከተለው ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ ዓለም (socialism ideology) አንጻር ፊልምን እንደ አንድ ግብዓት ለመጠቀም ፍላጐት የነበረው ቢመስልም ፍላጐቱ ከወረቀት ያልተሻገረ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከፊልም ይልቅ በተውኔትና በሙዚቃ ርዕዮተ ዓለሙን (ideology) በህዝብ ዘንድ ለማስረጽ ረጅም ጉዞ ተጉዟል ለማለት ይቻላል፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሳዊ አገዛዝም ስለፊልም የነበረው ግንዛቤ አነስተኛ ስለነበርና የቴክኖሎጂው እንደ ልብ አለመስፋፋት ተዳምረው ዘርፉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግም ቢሆን ፊልምን በአግባቡ በመጠቀም ረገድ የተከተለው አካሄድ ደካማ ነበር፡፡
አሁንም ድረስ ያው ነው ቢባልም ያስኬዳል ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ከስነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በቅርቡ አድርገውት በነበረው ውይይት ላይ ባለሙያዎቹ፤ መንግስት ዘርፉን በሚገባ ለመጠቀም ያለመቻሉንና የሀገሪቱን መልካም ስም ያጠለሸው ፊልም በመሆኑ ይህን የገጽታ ግንባታ (image building) ለማገዝ ፊልም ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ደጋግመው ቢገልፁም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡአቸው ምላሾች የመንግስትን የቀደሙ አካሄዶች የሚያሻሽሉ እንዳይደሉ ያመላከቱ ነበሩ፡፡
መንግስት የባህል ፖሊሲ ቢኖረውም ይህን ፖሊሲ ለማስፈፀም ፊልምን በግብአትነት ሲጠቀምበትም ሆነ በጀት ሲበጅትለት አላስተዋልኩም፡፡ በዚህ በኩል ተጠቃሽ ጥቅሞችን እንዳገኙ የሚነገርላቸው ናይጄሪያውያን በትምህርት፤ ህዝብን በማንቃትና በማንቀሳቀስ (public mobilization) ረገድ ጠቃሚ ውጤቶችን በፊልም ስራ ማግኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡
የባለሀብቶች ሚና ማነስ
በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ መስኮች ተሰልፈው ለልማት ስራ የሚታትሩቱ ባለሀብቶችም ስለፊልማችን ግድ የሰጣቸው አይመስልም፡፡ ጥቂት ባለሀብቶች ለተወሰኑ ባለሙያዎች መጠነኛ ድጋፎችን ከማድረጋቸው ውጪ የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው የፊልም ተሳትፎ አላደረጉም፡፡
ይህም ዘርፉ ስላለው አዋጪነትና በቀላሉ ስለሚኖረው ተደራሽነት በቂ ግንዛቤ ያለማግኘታቸው ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡ ለወደፊቱ ግን ይሄን መሰሉ እጥረት ሊቀረፍ የሚችልበት መልካም ዕድል ሊኖር እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ መቼስ የሰው ልጅ ያለተስፋ እንዴት ይኖራል?
በአጠቃላይ ከላይ በስህተት ሰበዝነት የመዘዝኳቸውንም ሆነ ሌሎቻችሁ የምትነጋገሩባቸው መሰል ችግሮቻችንን በግልጽ መነጋገራችን ይጠቅማል እላለሁ፡፡ እኔ ተራ የፊልም ተመልካች እንጂ ባለሙያ አይደለሁም፡፡ ቢሆንም ለፊልም ካለኝ ጥልቅ ፍቅር በመነሳት ብቻ ይህንን ሐሳብ ወረወርኩ፡፡ እንደ አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበርን የመሳሰሉ ማህበራት መበራከት ለተጠቀሱት ችግሮች መቃለል አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ የኢትዮጵያ ፊልም ባለሙያዎች ማህበርም ከፍ ያለ ሀላፊነት ይጠብቀዋል፡፡ፊልሞቻችን እያደጉ ነው ወይስ . . . ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ ጠንካራ ጥናቶችን በማስጠናትና አባሎቹ አጫጭር ስልጠናዎችን የሚያገኙበትን ዕድሎች እስከማመቻቸት የሚደርሱ የቤት ስራዎችን መወጣት ይኖርበታል፡፡ ፊልም ሰሪዎቻችንም ኩበት በሌለበት ጭስ እንደማይኖር ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡

Read 3382 times Last modified on Tuesday, 01 November 2011 14:28