Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 16 July 2011 12:14

ረሃብ የለም ብሎ መናገር ችግሩን ያድበሰብሰዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አቶ ተመስገን ዘውዴ፤ የአንድነት የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
ዜጎች ለረሃብ የሚጋለጡት፣ በአጋጣሚና በአንድ ሌሊት በተፈጠረ ችግር ሰበብ አይደለም፡፡ ባለፈው ዓመት የተከሰተው ርሃብ ከዘንድሮው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ የሚገባው ነገር ነው፡፡ ድርቅን ለመቋቋምና ወገኖቻችን በረሃብ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ለማድረግ መንግስት ዘላቂ መፍትሔ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡ ያለፈው ዓመት ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንደ¸ÃSfLgW ተነግሮ ነበር፡፡ ዘንድሮ ቁጥሩ ጨምሯል፤ ወደ 4.5 ሚሊዮን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 8 ሚሊዮን ህዝብ በሴፍቲ ኔት እርዳታ እየታቀፈ እንደሆነ ተነግሮናል፡፡ ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል፡፡

የአለማቀፍ ማህበረሰብ ችግር እንደሆነ የማድረግ ሁኔታ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ነገር ግን ይህ ችግር፣ የእኛ ችግር ነው እንጂ የሌሎች አይደለም፡፡ መፍታት ያለብን ራሳችን ነን፡፡ በረሃብ እየተሰቃዩ ያሉት የራሳችን ወገኖች ናቸው፡፡ ችግሩን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት መንግስት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይገባዋል፤ ረሃብ የለም ብሎ መናገር ችግሩን ያድበሰብሰዋል”” የምግብ እጥረት ተፈጠረ እንጂ ረሃብ አይደለም ማለት መፍትሄ አያመጣም፡፡
የምግብ እርዳታ እህል መስጠት ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ፤ በዘላቂ ችግሩን አይፈታም፡፡ ባለፉት ዓመታትም ችግሩን ለመፍታት በጊዜያዊ መንገድ መጠቀሙ ነው ዛሬ ይህን ጦስ ይዞ የመጣው፡፡ ለዚህም ነው ችግሮች ደጋግመው እየተከሰቱ ያሉት፡፡ ሰፋ ያለ ውይይት፣ አመለካከት፣ እቅድ የሚያስፈልገው ስለሆነ የሚመለከታቸውን አካላት በሙሉ ስለዘላቂ መፍትሄ ማወያየት ይገባል፡፡ ችግር በተፈጠረ ቁጥር የድረሱልኝ ጩኸት ማሰማት መፍትሔ አይደለም፡፡ ፖሊሲ ተቀርጾ እቅድና እስትራቴጂ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁኔታ ሊፈታ ይችል ነበር፡፡ ለዚህ ሁኔታ የመንግሥት ፖሊሲ ግልጽም አይደለም፡፡
በመንግሥት የተገለፀው የ4.5 ሚሊዮን ሰዎች ጉዳይ እንዳለ ሆኖ፤ በከተሞች በምናየው የኑሮ ውድነት ምክንያት በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ያሉ ብዙ ናቸው፡፡ ከህብረተሰቡ ራቅ ብለው የሚኖሩ ሰዎች ይህንን ላይገነዘቡት ይችላሉ፡፡ እኛ ግን በየቀኑ የምናየው ክስተት ነው፡፡ ማለዳ ላይ ወጣ ብሎ የአዲስ አበባን ጎዳናዎች ማየት ይቻላል፡፡ ምን ያህል ህዝብ ወድቆ፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ እንዳለ እናያለን፡፡
መንግሥት ኢኮኖሚውን አስተካክሎ የመምራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው፡፡ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው በጽሑፍም በቃልም ደጋግመን ተናግረናል፡፡ የዋጋ ግሽበቱ ህዝቡን ከፍተኛ ንቀት ውስጥ እየከተተው ነው፡፡
ዘላቂ መፍትሔ ምንድን ነው ይላሉ?
በኢኮኖሚው ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት መኖሩ፤ ለዋጋ ግሽበት መፍትሔ እንደሆነ በመንግስት ሲነገር ሰምተናል - ከወራት በፊት በተደረገ የፓርላማ ስብሰባ ላይ፡፡ በከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት ሳቢያ የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት፤ በተጨማሪ የገንዘብ ፍሰት ለመፍታት የተሞከረበት ሌላ አገር እናውቅም፡፡ በተቃራኒው፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ ብሔራዊ ባንክ ኖሮ በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ፍሰት በነጻነት ሊቆጣጠር የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡ አሁን ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት በኢኮኖሚ ውስጥ አለ፡፡ ምርቱ ግን በጣም ትንሽ ነው፡፡ ስለዚህ ለዋጋ ግሽበቱ መባባስ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ወደ ኢኮኖሚው እያፈሰሰ ነው፡፡ መንግስት በራሱ በበጀቱ መተዳደር አልቻለም፡፡ ልክ እንደ ግለሰብ መንግሥትም በገቢው መጠን በበጀቱ መተዳደር ካልቻለና ወጪው ከበዛ ችግር ይፈጠራል፡፡ መንግስት  ወጪዎቹን መቀነስ ይኖርበታል፡፡  የግድ መደረግ የሚኖርበት የኢኮኖሚ እውነታ ነው፡፡
በርካታ መንግሥታትም ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት በሚኖርበትና የዋጋ ግሽበት በሚፈጠርበት ጊዜ፤ መንግስት ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ኢኮኖሚው የሚያፈስበት ሁኔታ መኖር የለበትም፤ የዋጋ ግሽበቱ እስከሚረጋጋ ድረስ፡፡ መንግትስ ግን ተቃራኒውን መንገድ ሲከተል ታይቷል፡፡ የዋጋ ቁጥጥር እንዳልሠራ አይተነዋል፡፡ በፊትም ቢሆን እንደማይሠራ ተናግረን ነበር፡፡ በሞነተሪና በፊሲካል ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ዘዴዎች አማካኝነት የገንዘብ ፍሰቱን መስመር በማስያዝ የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ አልተተገበረም፡፡ ነገር ግን የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት ካልቻለ እድገትንና ትራንስፎርሜሽንን አመጣለሁ ማለት አይቻልም፡፡

Read 3185 times

Latest from