Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 13:04

ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን አጥቻለሁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2003 ዓ.ም ዲሞክራሲያዊ ስርአትን አጥቻለሁ፡፡ በነፃነት ተደራጅቶ የመንቀሳቀስ መብት ተገድቦ፣ ስልጣን ላይ ያለው አካል ከቀረነው ጋር መነጋገር አለመፈለጉ ይሄ ትልቅ ያጣነው ነገር ነው፡፡ ለዚህ አገር መፍትሄ ሊሆን ይችላል የምለው ውይይት እና መደራደር ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ ለዚህ ፍቃደኛ አለመሆኑ ትልቁ ያጣነው ነገር YmSl¾L””በ2003 ዓ.ም የማልረሳው ክስተት ይሄ የሚሌኒየሙን ግድብ የመስራትን ነገር ነው፡፡ ከሚገባው በላይ ማስጮሁ፤ ህዝቡን በስሜታዊነት አጥሮ በቂ መረጃ ሳይሰጥና ያሉትን አማራጮች ሳያሳይ፣ የምስኪኑን ህዝብ ልቦና ማዋለሉ ለምን እንደሆነ አይገባኝም፡፡

በ2004 ዓ.ም ገዢው ፓርቲ ከተቀረው የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ተወያይቶ፣ ቀጣዩ ምርጫ ሁሉም በሰላማዊ መንገድ የሚወዳደርበትን አማራጮች የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር እመኛለሁ፡፡እንግዲህ የዲሞክራሲያዊ ስርአቱ የቀጨጨ የፖለቲካ እንቅስቃሴና ተሳትፎ ባለበት ሁኔታ ላይ ነን ያለነው፡፡ ሁሉንም ጨቁኜ ልግዛ ማለቱ ነው አሁን ያለንበትን ሁኔታ ያመጣው፡፡ በቀጣይ የሚመጣውን መተንበይ ይከብዳል፡፡ ማማውን የያዘው አካል ሲገለባበጥ ነው እያየን ያለነው ይሄ፡፡
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
(የመድረክ ምክትል ሰብሳቢ እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

Read 4650 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:06