Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 13:11

..ዲሞክራሲ የአንድና የሁለት ቀን ሥራ አይደለም..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው ነገር የለም፡፡ የማልረሳቸው ክስተቶች ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው ኢዴፓ ለህዝብ ቃል በገባው መሰረት የአመራር ለውጥ አድርጐ ከተለመደው የፖለቲካ አሠራር እራሱን የተለየ ፓርቲ መሆኑን ያረጋገጠበት ነው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደን የቀድሞውን አመራር በአዲስ ተክተናል፡፡ ሁለተኛው በአባይ ግድብ ዙሪያ ያደረኩት ጉብኝት ነው፡፡ የዚህ ታሪክ አካል መሆኔ የማልረሳው ሲሆን ሦስተኛው በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ነው፡፡

ከረጅም ጊዜ በኋላ በጣም አሳሳቢ ነው የተባለውን ድርቅ ማየታችን የማልረሳው አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የምመኘው አዲሱ ዓመት ተስፋ ፈንጣቂ እንዲሆንልን ነው፤ ነገር ግን ተስፋዎች ወደ ተግባር ሲለወጡ አይታዩም፤ ባህሉም የለም እና ይሄ አመት የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ ከማድረግ ወጥቶ በተግባርና በውጤት የሚለካ ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
የኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ፖለቲካ ሂደት አሁንም ኋላቀር ነው፤ መሰረታዊ ነገሩ መንግስት ዲሞክራሲን ለማምጣት መስራት የሚገባውን እየሰራ ባለመገኘቱ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቅም የፈቀደውን ያህል ትግሉን አለመግፋታችን ለውጥ እንዳይመጣ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዲሞክራሲ የአንድና የሁለት ቀን ሥራ አይደለም፤ ስለዚህ በሚቀጥለው አመት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በዚህ ደረጃ ያድጋል ብሎ መናገር ይከብዳል፡፡
አሁንም የተጀመሩ ጭላንጭል ነገሮችን ለመቀጠል ኢህአዴግ ጥረት የሚያደርግ ከሆነ፣ ዲሞክራሲን ኢትዮጵያ ውሰጥ ለማስፈን አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ ይቻላል፡፡ ይሄንን ግን ገዢው ፓርቲ መፈፀም ካልቻለ ሌሎች አምባገነን መሪዎች የሚደርስባቸው እጣ ፈንታ ይደርሰዋል፡፡ ማህበረሰቡ ጥቅምና ጉዳቱን ለማረጋገጥ ሁኔታዎች እስካልተመቻቹለት ድረስ መንግሥታት አምላኮች ስላልሆኑ መለወጣቸው የግድ ነው፡፡
2004 ዓ.ም መልካም የስራና የብልግና ዘመን እንዲሆንእመኛለሁ፡፡ በአገሪቱ ለውጥ ለማምጣት በጋራ ውጤታማ ስራዎችን የምንሰራበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
አቶ ሙሼ ሰሙ
(የኢዴፓ ሊቀመንበር)

 

Read 3322 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:24