Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 05 November 2012 07:36

ሪታ ማርሌ ለህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ ታሰባስባለች

Written by 
Rate this item
(9 votes)

የዝነኛው የሬጌ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ ባለቤት ማርሌ ለሁለት ሳምንት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ተገለፀ፡፡ የጉብኝቷ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት በሚገነባው የህዳሴ ግድብ አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠርና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው ተብሏል፡፡
የቦብ እና ሪታ ማርሌ ፋውንዴሽን ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ ቦብ ኔስታ ማርሌይ በመላው ህይወቱ ስለኢትዮጵያ ብዙ ሃሳብ እንደነበረው ጠቅሶ፤ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ምድሬ ወደ የሚላት አገር መጥቶ የህይወቱን የመጨረሻ ዘመናት ለመኖር ባይታደልም ራእዩ ከኢትዮጵያውያን ጋር ዝንተዓለም ይኖራል ብሏል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቦብ ማርሌ እጅግ የሚያደንቁት አርቲስት መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልፁ እንደነበር የጠቀሰው መግለጫ የቦብ እና የሪታ ማርሌይ ፋውንዴሽን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገቢ ይሆናል ብሏል፡፡ ወይዘሮ ሪታ ማርሌይ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማትን ሃዘን እንደገለፀችም ታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ከድህነት አዘቅት ለማውጣት በነበራቸው ራእይ ከፍተኛ አድናቆት እንዳላት ሪታ ማርሌይ ገልፃለች፡፡በኢትዮጵያ የቦብ እና ሪታ ማርሌይ ፋውንዴሽን ተወካይ ወይዘሮ ደስታ ሜጎሁ ስለህዳሴ ግድብ ለወይዘሮ ሪታ ሲነግሯት፤ “እኛ ከኢትዮጵያ ጋር አብረን መስራት አለብን፡፡ ለኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካ ስንል፤ ይህ የአፍሪካ አንድነት መገለጫ ነው” በማለት ምላሽ እንደተሰጠች ታውቋል፡፡ በጋና የምትገኘው ሪታ ማርሌ በባህርማዶ ያሉ ኢትዮጵያውያን በመደገፍ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጐት እንዳላት ትናገራለች፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በሚያመነጨው ሃይል በኢትዮጵያ እና በጐረቤት አገራት ያሉ በሚሊዮን የሚገመቱ ህዝቦች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በጉጉት እንጠብቃለን ብላለች - ወይዘሮ ሪታ ማርሌ፡፡ 
ቦብ “አፍሪካ ዩናይት” በሚል ያቀነቀነውን ዜማ ስንኞች “How good and how pleasant it will be, before God and man, to see the unification of all Africans…” በመጥቀስ ወደ ሌላ አገሯ ኢትዮጵያ ለመምጣት የመጨረሻ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ገልፃለች፡፡ “ኢትዮጵያ የአፍሪካን ህዳሴ እውን በማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖራታል፡፡ እኛም በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ አብረን መሆን እንፈልጋለን” ብላለች ሪታ ማርሌ፡፡

Read 4135 times Last modified on Monday, 05 November 2012 07:48