Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 13:31

ከየትኛው ነን? ከአሜሪካ ወይስ ከቻይና?

Written by 
Rate this item
(8 votes)

ለምን ቢባል? ገዢው ፓርቲ ብቻ አይደለም ወደኋላ የሚንሸራተተው። ዜጎችም ይንሸራተታሉ። ኢህአዴግንስ ወቀስን። ግን፤ ምሁራንና ዜጎች ወይም ኢህአዴግን የሚቃወሙ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞችስ? በሂደት ነፃነት እንዲስፋፋና ወደ አሜሪካው አይነት የፖለቲካ ሁኔታ እንድንጓዝ ይመኛሉ? ወይስ በኢህአዴግ ቦታ ሁልጊዜ 99.9% የሚያሸንፍ ሌላ ገናና ፓርቲ ተተክቶ ማየት ነው የሚፈልጉት? ሁሉም ሰው ተቃውሞውንና ድጋፉን በነፃነት የሚገልፅበት ስርዓት እንዲስፋፋ ነው የሚያልሙት? ወይስ፤ ኢህአዴግን ተክተው የነሱ ሃሳብ ብቻ እየተስተጋባ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ እንዲታፈን ነው? በአጭሩ የትኛው ይማርካቸዋል - የአሜሪካ ወግ ወይስ የቻይና ወግ?የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲህ የኋሊት መንሸራተቱ አያሳዝንም? ከተጨባጩ ሁኔታ ይልቅ ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ግን፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ለወደፊት ያላቸው ምኞት ያን ያህልም ብሩህ ሳይሆን ሲቀር ነው።

ከአሜሪካና ከቻይና የፖለቲካ ድግሶች መካከል፤ የአሜሪካው ካላጓጓን፤ ከሁለቱ አገራት ወግ መካከል የአሜሪካው በጣሙን ካልማረከን፤ በእጅጉ ማዘን ይኖርብናል እላለሁ።  ከአስር አመት በፊትኮ፤ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአገሪቱ መልካም የፖለቲካ ባሕል ለመሆን እየተቃረበ ነበር። “ይሄውና ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነትና በሰላም የሚገልፁበት እድል እየተስፋፋ ነው” ብለን የምንሟገትለት መልካም ሂደት ዛሬ የለም። አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ካየን ሰባት አመት ልንደፍን አይደል! “ይሄውና የግል ጋዜጦች እየተበራከቱና እየተሻሻሉ ነው” ብለን የምንደግፈው የያኔው የፕሬስ ነፃነት ሂደትም፤ ዛሬ ዛሬ የኋሊት የሚጓዝ ሆኗል። የግል ጋዜጦች ቁጥር ተመናምኗል። ዜጎች የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሃሳባቸውን የሚገልፁበት ነፃነትም እየጠበበ መጥቷል። ዛሬ የመንግስትንና የገዢውን ፓርቲ መመሪያ ለማስፈፀም ነው፤ ዜጎች 1ለ5 ሲደራጁ የምናየው።ከአስር አመት በፊት ከነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ይልቅ የዛሬው የተሻለ መሆን አልነበረበትም? ግን አስተውሉ። ዛሬ ከያኔውም ብሶበት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ እየጠፋ መጥቷል። ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ብቻ ይዞ የነበረው ፓርላማ፤ በተከታዩ ምርጫ ተሻሽሎ 12 ያህል የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጮችን አስተናግዷል። ከዚያም የፖለቲካ ምርጫዎች ላይ የፓርቲዎች ፉክክር እየተሻሻለ፤ በፓርላማ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ቁጥር ከመቶ በላይ ሲሆን አይተናል። ይሄ ጥሩ ሂደት ነበር። “ይሄው ተመልከቱ፤ በርካታ ፓርቲዎች የሚፎካከሩበት የፖለቲካ ስርዓት እየተስፋፋ ነው” ብለን የምንሟገትለት ሂደት ነበር። ዛሬ ግን፣ “ሂደቱ” ወደ ኋላ ተመልሶ፤ የምርጫ ፉክክር ጠፍቷል። ገዢው ፓርቲ 99.9 በመቶ እያሸነፈ፤ ፓርላማውን ከሞላ ጎደል ተቆጣጥሮታል - ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በስተቀር።እውነትም፤ በግለሰብ ነፃነትና መብት ላይ የተመሰረተ የዲሞክራሲ ስርዓት ለማስፈን ጊዜና ጥረት ያስፈልጋል። ነገርዬው የሂደት ጉዳይ ነው። በሂደት ነው፤ የአገራችንን ፖለቲካ የሚሻሻለው። በሂደት ነው፤ ከቻይናው አይነት ፖለቲካ ወደ አሜሪካው አይነት ፖለቲካ መጓዝ ወይም መገስገስ የሚቻለው። አአሳሳቢው ነገር ምን መሰላችሁ? የአገራችን “ሂደት”... ቀስ በቀስ “ሂደትነቱ” እየጠፋ መምጣቱ ነው። ባለበት የሚረግጥ ከሆነ፤ “መሄድ”ን ረስቷል ማለት ነው። ጭራሽ... “ሂደቱ” የኋሊት ማፈግፈግና ተመልሶ ወደ ቻይና መጠጋት ሲጀምርስ? ባለፉት ሰባት አመታት ይህንን ወደ ኋላ የመመለስ አሳዛኝ “ሂደት” የተመለከትነው።“ሂደት”፣ መሄድ አቆመ
ታዲያ፤ ከተለያየ አቅጣጫ አይተን ስንመዝነው፤ የአገራችን ፖለቲካ ወደ ቻይና በእጅጉ የተጠጋ መሆኑ ያከራክራል?  ደግሞስ፤ ከ22 አመታት በፊትኮ፤ የኢትዮጰያ ፖለቲካ ከቻይና የባሰ አልነበር እንዴ! በደርግ የኮሙኒዝም አገዛዝ ወቅት፤ ከገዢው ፓርቲ ውጭ ሌላ ፓርቲ ማቋቋም ወንጀል ነበር። ተቃውሞና ትችት ማሰማት የተከለከለበት፤ የግል ሚዲያ የማይፈቀድበት ዘመን ነበር። ታዲያ፣ ዛሬም የአገራችን ፖለቲካ ከቻይና ጋር ተቀራራቢነት ቢኖረው ምኑ ያስገርማል? ኢህአዴግም ራሱ ከሞላ ጎደል የሚስማማበት ይመስለኛል። “የዲሞክራሲ ግንባታ በርካታ አመታትን የሚፈጅ ሂደት ነው” ይል የለ! አዎ፤ አገራችን ውስጥ ዜጎች በማህበር ሲደራጁና በምርጫ ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ሲንቀሳቀሱ ይታያል። ነገር ግን፤ እንደ አሜሪካ አይደለም። በአገራችን፣ ሁሉም ዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ እድላቸው ጠባብ ነው፤ ለእስርና ለወከባ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ያውቁታላ። ገዢውን ፓርቲ የሚደግፉ ከሆነ ነው ስጋት የማይኖርባቸው - እንደ ቻይና።አዎ፤ በአገራችን ነፃ አስተያየቶችና ዘገባዎች በግል ጋዜጦች ይታተማሉ። ግን ፍርሃትና ስጋት እንዳጠላባቸው ነው የሚታተሙት። መንግስት በማንኛውም ሰዓት የግል ጋዜጦችን ሊዘጋ፣ የግል ሬዲዮ ጣቢያዎችን ሊወርስ እንደሚችል ይታወቃልና። በዚያ ላይ፤ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ማቋቋም እስካሁን አልተፈቀደም። አገሪቱ ላይ የሚፈነጩት የመንግስት የሬድዮና የቲቪ ስርጭቶች ናቸው - እንደ ቻይና ማለት ነው። በአሜሪካ ግን፤ የመንግስት ጋዜጣ የለም። በሺ የሚቆጠሩ የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ባጥለቀለቋት አሜሪካ ውስጥ፤ መንግስት የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ የለውም (ከቪኦኤ ጣቢያ በስተቀር)። ለነገሩ፤ በመንግስት የሚተዳደረው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ ፕሮግራሞቹን አሜሪካ ውስጥ እንዲያሰራጭ አይፈቀድለትም። ለምን? መንግስት በአገሩ ውስጥ ፕሮፓጋንዳ የማሰራጨት ስልጣን እንዳይኖረው ለመከልከል ነው። አዎ፤ አገራችን ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማቋቋም ይፈቀዳል፤ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም አሉ። ነገር ግን፤ እንደ አሜሪካ አይደለም። ከገዢው ፓርቲና ከአጋሮቹ በስተቀር፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትን ለማበራከትና ዜጎችን መቀስቀስ በነፃነት የመንቀሳቀስ እድላቸው ጠባብ ነው። አንድ ገዢ ፓርቲ ነው የገነነው - እንደ ቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ። አዎ፤ አገራችን ውስጥ በየአምስት አመቱ በሚዘጋጁ ምርጫዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ። ግን፣ ጠንካራ ፉክክር የለም። ሁሌም ገዢው ፓርቲ ነው ስልጣን የሚይዘው - እንደ ቻይና። “የአገራችን ፖለቲካ፣ ከአሜሪካ ጋር ተቀራራቢ ሆኖ የሚታየን በህልም ነው ወይስ በእውን?” ... ብትሉ አይገርመኝም። በእርግጥ በህልምና በምኞት መቀራረብም ቀላል ነገር አይደለም። ነገር ግን፤ እያወራን ያለነው ስለወደፊቱ ምኞታችን ሳይሆን፤ አሁን በእውን ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ነው። በእውን ደግሞ፤ የአገራችን ፖለቲካ ከአሜሪካ ፖለቲካ ጋር በጣም ይራራቃል። ምናልባት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማቋቋም የሚፈቀድ መሆኑንና በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸውን በማሳየት፤ “ልክ እንደ አሜሪካ ነው” ብለው ሊያሳምኑን የሚሞክሩ መኖራቸው አይቀርም። በዚያ ላይ በየአምስት አመቱ የፖለቲካ ምርጫዎች እየተዘጋጁ ፓርቲዎች ሲሳተፉ ተመልክተናል። ምርጫ ሲቃረብ፤ ለተወሰኑ ሰዓታት የፓርቲዎች ክርክር በቲቪና በሬድዮ ሲሰራጭ አድምጠናል። በግል ጋዜጦች ነፃ አስተያየቶችና ዘገባዎች እየታተሙ አንብበናል። ዜጎች በማህበርም ሆነ በቡድን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ እንዲሁም በምርጫው እለት ድምፅ ሲሰጡም ታዝበናል። ይሄ ሁሉ ሲደማመር፤ የአገራችን ፖለቲካ፣ ከአሜሪካ የፖለቲካ ድግስ ጋር የሚቀራረብ ሆኖ ሊታየን አይችልም? አትስማሙም? ፓርቲዎች፣ ምርጫዎች፣ ጋዜጦች፣ ዜጎች“በሁለቱ አገራት ወግ መካከል የሆነ ቦታ ላይ ነው” የሚባለው የአገራችን ፖለቲካስ፤ ወደየትኛው ይጠጋል? ወደ ቻይና ወይስ ወደ አሜሪካ? በየትኛው አይነት የፖለቲካ ድግስ ወይም የፖለቲካ ድራማ ውስጥ ነን? የአሜሪካው ወይስ የቻይናው አይነት? ያን ያህልም ከባድ ጥያቄ እንዳልሆነ የምንስማማ ይመስለኛል። “ከሁለቱም ይለያል፤ ከሁለቱ መካከል የሆነ ቦታ ላይ ነን” ብሎ መልስ መስጠት ይቻላል። ግን ምን ዋጋ አለው! እንዲህ በደፈናው የሚቀርብ ምላሽ ብዙም አይጠቅምም። ውሃ የሚፈልግ ሰው፤ “ብርጭቆው ባዶ ነው ወይስ ሙሉ?” ብሎ ሲጠይቅ፤ “ብርጭቆው ባዶ ወይም ሙሉ አይደለም፤ የሆነ ያህል ውሃ ይዟል” ብሎ እንደመመለስ ነው። ምን ያህል ውሃ? ወደ ባዶ የተጠጋ? ወይስ ወደ ሙሉ የተጠጋ?... ለየት ያለ ሁለተኛ ጥያቄ ልጨምርላችሁ - “የሁለቱ አገራት ወግ ውስጥ፤ የኛ የዜጎች እንዲሁም የአገራችን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ቦታ የቱ ጋ ነው?” ... ይሄ የምኞትና የራዕይ ጉዳይ አይደለም። በእውን የኖርንበትና አሁን የምንኖርበት የፖለቲካ ሁኔታ ምን እንደሚመስል አይቶና መዝኖ የመፍረድ ጥያቄ ነው። ሁለቱ የፖለቲካ ድግሶች፣ በአንድ ፕላኔት በአንድ ሳምንት የተካሄዱ ቢሆኑም፣ ልዩነታቸው ግን የሰማይና የምድር ያህል ነው። በተለያዩ ፕላኔቶችና በተራራቁ የታሪክ ዘመኖች የተካሄዱ ይመስላሉ። ዋናው ጥያቄ፤ “ለመሆኑ ‘ከሁለቱ አገራት ወግ’ ውስጥ፤ የትኛው ይማርከናል?” የሚል ነው። አሜሪካን ወይም ቻይናን የመደገፍ ጉዳይ አይደለም። ነገርዬውን የኛ ጉዳይ እናድርገው። ለራሳችን ወይም ለአገራችን፣ የትኛውን አይነት የፖለቲካ ድግስ እንፈልጋለን? የትኛውን እንመኛለን?... ጥያቄው፣ የምኞትና የፍላጎት አልያም የራዕይና የአላማ ጥያቄ እንደሆነ ልብ በሉ።‘የሁለት አገራት ወግ’
ነገር ግን “መምረጥ አትችልም” ብለው አይተዉትም። እረፍት አይሰጡትም። ሁሉም ቻይናዊ የ”ምርጦቹ”ን ስብሰባና ዲስኩር በቴሌቪዥን የመከታተል ግዴታ አለበት። በትምህርት ቤቶችም ሆነ በሥራ ቦታዎች፤ ተማሪዎችም ሆኑ ሠራተኞች፤ አዳራሽ ውስጥም ሆነ ዛፍ ጥላ ስር፣ ወንበር ከተገኘ ቁጭ ብለው፣ ከሌለም ቆመው ቴሊቪዥን ማየት ግዴታቸው ነው።እነዚሁ ሁለት ሺ “ምርጦች”፤ አገሪቱን ለአስር አመታት የሚገዛ የፓርቲ መሪ ለመሰየም ሰሞኑን ስብሰባ ጀምረዋል። የንጉሥ ዘሮችና የመሳፍንት ቤተሰቦች አይመስሉም? በቃ! እነሱ ናቸው አድራጊ ፈጣሪዎች። በነሱ ስብሰባ ነው ፕሬዚዳንት የሚመረጠው። ከግማሽ ሚሊዮን ቻይናዊያን መካከል አንድ ሰው ብቻ ነው፤ የ”ምርጦቹ” ስብሰባ ውስጥ መግባትና ድምፅ መስጠት የሚችለው። 99.999% ያህሉ የቻይና ዜጋ ድምፅ የመስጠት መብት የለውም። ሁለተኛው የፖለቲካ ድግስ (ድራማ)፤ 1300 ሚሊዮን ህዝብ በያዘችው ቻይና ውስጥ የተሰናዳ ነው። ድግሱ ግን ጥቂቶች የሚታደሙበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። የአገሪቱን ፕሬዚዳንት የመምረጥና ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው የቻይና ዜጎች 2ሺ ብቻ ናቸው። የምርጫ ዘመቻና ፉክክር ብሎ ነገር የለም። አማራጭ ፓርቲዎችና የሃሳብ ክርክሮች በአገሪቱ ውስጥ ለምልክት ያህል እንኳ አይታዩም። መከራከርም ሆነ መተቸት፤ መቃወምም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲ መመስረት አይቻልም። አንድ ገዢ ፓርቲ የነገሰባት አገር ነች - ቻይና። በውርስ የሚተላለፍ “ሥርወ መንግስት” ይመስላል። የፓርቲው መሪዎች ብቻ ናቸው፤ አገሪቱን እየተፈራረቁ የሚገዟት። ሁለት ሺ የሚሆኑ የፓርቲው የበላይ ካድሬዎች (ምርጦች) ናቸው አገሪቱን የሚቆጣጠሯት። በምርጫው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ባራክ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት አሸንፈዋል፤ ተፎካካሪያቸው ሚት ሮምኒም በዚያው ምሽት ስልክ ደውለው “እንኳን ደስ ያለህ” ብለዋቸዋል። በምክር ቤት ምርጫ ግን አብዛኛውን የኮንግረስ ወንበር ያሸነፉት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ናቸው። ተፎካካሪዎች እለት በእለት በየመድረኩ የሚያቀርቡትን የእርስ በርስ ትችትና አማራጭ ሃሳብ መስማት ብቻ አይደለም - የዜጎች ድርሻ። ተፎካካሪዎች በየደቂቃው በተለያዩ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያስተላልፉት ክርክርና እልፍ ማስታወቂያ መከታተል ብቻ አይደለም - የዜጎች ፋንታ። ዜጎች ራሳቸው፤ ያሻቸውን ተፎካካሪ በመደገፍ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ። እንደየዝንባሌያቸውና እንደየፍላጎታቸው ማህበር እያቋቋሙ፣ ከተፎካካሪዎቹ ባልተናነሰ ሁኔታ ማስታወቂያዎችን ያሰራጫሉ። በመጨረሻም ይመርጣሉ። አንደኛው ድግስ፣ ባራክ ኦባማና ሚት ሮምኒ አንገት ለአንገት የተፎካከሩበት የአሜሪካ ምርጫ ነው። የተፎካካሪዎችን ፋታ የማይሰጥ ክርክርና የምርጫ ዘመቻ ሲከታተሉ የከረሙ ከመቶ ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን፤ ማክሰኞ እለት የምክር ቤት አባላትንና ፕሬዚዳንታቸውን መርጠዋል። ሕፃናትን ሳይጨምር ከአገሪቱ ዜጎች መካከል ቢያንስ 50% ያህሉ በምርጫ ዘመቻ ተዋናይነት ወይም በድምፅ ሰጪነት ተሳትፏል - ያሻውን እየደገፈና እያደነቀ፣ ያሰኘውን እየተቃወመና እየተቸ። አለማችን ዥንጉርጉር ነች። ሰሞኑን እጅግ የተለያዩ ሁለት አይነት የፖለቲካ ድግሶችን አስተናግዳለች።

Read 18938 times