Saturday, 10 November 2012 14:12

ፍቅርና የፍቅር አልጋ!

Written by  ደረጀ በላይነህ
Rate this item
(322 votes)

ሌላው ፍቅር የምንሰራበት ስፍራ ጥሩና ደህንነት ያለው መሆን አለበት፤ይህ በተለይ ለሴቶች ወሳኝ ነው ይላሉ፡፡ ግድግዳው ድምጽ የሚያስተላልፍ ከሆነ፣በሩ ካልተዘጋ፣አልጋው ጠባብ ወይም አጭር ፣የሚጮህ ከሆነ፣ሴትዋ ምቾት ላይሰማት ይችላል፡፡ልብስን ሙሉ በሙሉ ያለማውለቅን በተመለከተ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ምርጫ አላቸው፡፡ አንዳንድ ሚስቶች ልብሳቸው በባሎቻቸው ሲወልቅላቸው ደስ ይላቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ባልየው በጥንቃቄና ተራ በተራ ሊያወልቅላት ይገባል፤ እንደ ሁለቱ ምርጫ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል፡፡ አንዳንድ ወንዶች ሚስታቸው ስስ ፒጃማ (ጋዋን) እንድትለብስ ይፈልጋሉ፡፡ ወንዶችም በተመሳሳይ ራሳቸው ሊያወልቁ ወይም ሚስታቸው ልታወልቅላቸው ትችላለች፡፡

ሁለቱ ጥንዶች ልብሳቸውን ካወለቁ በኋላ በምንም ነገር ሊቋረጡ አይገባም፤ያለበለዚያ ከፍተኛ ስነ ልቡናዊ ረብሻ ይፈጥርባቸዋል፡፡ከዚህ ቀጥሎ ግን የሰውነት ክፍሎችን በመነካካትና በመተሻሸት የሚፈጠረውን የስሜት ከፍታ በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ባል የሚስቱን የጡት ጫፍ መቀስቀስ አለበት፡፡ ከንፈርና ምላስም እንደዚሁ፡፡ ሌላው አስፈላጊና ወሳኝ ምርጫ የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚደረግበት ጊዜ ያለው አተኛኝ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የተለመደው ሚስት ከታች ባል ከላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን መቀየር ይቻላል፡፡ ሚስት ከላይ ባል ከስር ሲሆኑ ለሁለቱም የተሻለ እርካታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ምክንያቱም የኮሌጅ ተማሪዎች ስለ ፅዳት አጠባበቅ ይማራሉና! አንዳንድ ባልና ሚስትም ከግብረ ስጋ በፊት አብረው የመታጠብ ልማድ አላቸው፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ሽቶ መጠቀም ጥሩ የስሜት መነሳሳት ሊፈጥር ይችላል፡፡ ሌላው ለአፋችን ጠረን ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ ነው፡፡ ብዙ ሴቶች የሲጋራ፣ የመጠጥ የሽንኩርትና የሌሎች ተመሳሳይ ጠረን ያላቸውን ነገሮች መታገስ አይችሉም፡፡ከዚህ በተጨማሪ በጽዳትና ጥሩ ጠረን በመፍጠር መዘጋጀት የሚኖረው ድርሻ ቀላል አይደለም፡፡ ምናልባት ባሌ የኮሌጅ ተማሪዎችን ጭራ ይከተላል ያለችው ሴት ችግር ራስ የመጠበቅ (የጽዳት ችግር) ሊሆን ይችላል፡፡ይህ የሆነው በፈቃደኝነት፣በስምምነት የሚሰጣጡት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ ወንዶች ሚስቶቻቸውን ቀደም ብለው በፍቅር የማግባባት ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ታዲያ ይላሉ አማካሪው፤ ባልና ሚስቱ አብረው ሽርሽር ቢወጡ ወክ፣ ሙዚቃ ቢያዳምጡ፣የፍቅር ቃላት ቢለዋወጡ፣ስራ ቢተጋገዙ የተሻለ ያዘጋጃቸዋል፡፡ የፍቅር ጉዳይ ያለ ሁለቱ ወገኖች የማይሆን ስለሆነ ጉዳዩን በመነጋገር ለመፍታት መሞከር የተሻለ ነው፡፡ እንደ እንስሳት የሴትዋ ብልት ከውጪ ያለመቀመጡ፤በሁለት እግሮች መሃል መሆኑ ዝም ብሎ አይደለም፤እግር ደግሞ የሰውነት ጠንካራ ክፍል ነው፡፡ቀን ሙሉ ትኩረት ያልሰጣትን ሚስቱን በአልጋ ሰዓት ቢያቅፋት ስሜትዋ ላይዘጋጅና የፍቅር ስሜት ላይኖራት ይችላል፡፡ሰዉየው እንደሚሉት፤ ባልና ሚስት ወደ ግብረ ስጋ ግንኙነት ከመሄዳቸው በፊት ስነ ልቡናዊ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው፡፡ ቀደም ሲል ቅራኔና ያልተፈታ ችግር ካለ፣ አንደኛውን ወገን ሊያሳዝኑትና ደስታ ሊከለክሉት ይችላሉ፡፡  ሌላም አፍሪካዊ ጸሃፊ በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ፤ጣሪያ ላይ ምስማር እንደሚመታ አናጺ ወጥቶ የልቡን ለመፈጸም ባል መሆን የለበትም፡፡ በግብረ ስጋ ጊዜ ሶስት ደረጃዎች አሉ ይላሉ፡- ለግብረ ስጋ ወይም ለፍቅር ጨዋታ መዘጋጀት፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ፣ከግብረ ስጋ በኋላ ዘና የማለት ጊዜ፡፡ዶክተር ቴዎዶር የተባሉ የጋብቻ አማካሪን ጠቅሰው ሲናገሩ “ባል ማለት ለሚስቱ እንደ ጠራራ ጸሃይ መጠለያ ኮት ነው፤ቀን ከሃሩር ሊከልላት ይገባል፤ሊያስጠልላት ያስፈልጋል፡፡ ሁልጊዜ ደህንነትና ፍቅር ከተሰማት ሁለመናዋን ለመስጠት አይቸግራትም፡፡ጂን ባንዮላክ፤ የግብረ ስጋ ግንኙነት አካላዊ ብቻ ሳይሆን ስነ ልቡናዊ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ውጫዊ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊም ነው፡፡ የነፍስ፣ የስጋ፣ የመንፈስም ህብረት ነው፡፡      ስለዚህ ደናግል ወደዱህ፡፡      ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤      ዘይትህ፣መልካም መዓዛ አለው፤      ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና፡፡      በአፉ መሳም ይሳመኝ፣አድናቆትና   ፍቅር ሲፈስስ፡ይልቅስ ብልግናው መፍትሄ እያለ ጎጆን ማፍረስና ልጆችን መበተን ነው-ይላሉ፡፡ በተለይ ቅዱሳን መጻህፍትን ያየን እንደሆነ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ፍቅር የሰጠውን ትኩረት እንመለከታለን፤ ለዚህ ደግሞ መሃልየ መሃልይን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዳንዶች ግን ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት መነጋገርን እንደ ነውር ያዩታል፡፡ የስነ ጋብቻ ምሁራን ይህንን አምርረው ይኮንኑታል፡፡ -አብሬው የምኖረውን ባሌን ከማግባቴ በፊት ወንድ የሚባል ነገር አላውቅም፤ይሁን እንጂ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብረ-ስጋ ግንኙነት ስናደርግ ምንም ደም አልፈሰሰኝም፤ስለዚህ ባለቤቴ ድንግል አይደለሽም፤ ያለ ሁሌ ይነዘንዘኛል፤ ይህንን በምን መንገድ ላሳምነው እችላለሁ፡-እነዚህ ሁሉ ችግሮቻቸውን በግልጽ የተናገሩ ናቸው፡፡ ባለቤቴ የግብረ-ስጋ ግንኙነት አድርገን እርካታ ላይ ከደረስን በኋላ እኔ አፍጥጨ እያለ እርሱ ለመተኛት ይጣደፋል፤ወዲያው ጀርባውን አዙሮ ማንኮራፋት ይጀምራል፤ይህ የኔን የእርካታ ስሜትና ደስታ መልሶ ያጠፋዋል፡፡የዚህችኛዋ ጥያቄ ትንሽ ለየት ይላል፤ ባለቤቴ ሁልጊዜ ምሽት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ይጠይቀኛል፤አብዝተኸዋል ስለው ደግሞ ሌላ ሚስት እንደሚያገባ ይነግረኛል፤ለመሆኑ ባልና ሚስት በየስንት ጊዜው የግብረ-ስጋ ግንኙነት ቢያደርጉ ጤናማ ነው እኔም እንግዲያው ከኮሌጅ ወንድ ተማሪዎች የአልጋ ጥበብ እማራለሁ ስለው ለዱላ ይነሳል፤ሮጨ ካላመለጥኩ አይምረኝም፡፡ ስለዚህ ምን ይሻለኛል?ባለቤቴ የኮሌጅ ተማሪዎችን ያሳድዳል፤ ለምን እንደዚያ እንደሚያደርግ ስጠይቀው የኮሌጅ ተማሪዎች ስለ አልጋ ጥበብ የተማሩ ናቸው ይለኛል፡፡ ሌላኛው ጠያቂ ደግሞ እንዲህ ይላል፡- ባለቤቴ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በምናደርግበት ጊዜ ከኔ እኩል ወደ እርካታ አትደርስም፤የእኔ ዕድሜ 38 ሲሆን የርሷ ደግሞ 24 ነው፤ ስለዚህ ከኔ ጋር የማትረካው የዕድሜ እኩዮችዋ ጋ እየሄደች እንደሆነ ተናግሬያታለሁ፡፡ ይህ ጉዳይ በጣም ረብሾኛል፤ስለዚህ ሌላ ሚስት ባገባ ይሻል ይሆን? ባለቤቴ በግብረ ስጋ ሰዓት መብራት ታጠፋለች፤ ይህ ነገር ጤናማ ነው ይሄ ደግሞ በአንድ  ግራ ተጋቢ ባለትዳር የተጠየቀ ነው፡፡ እስቲ ደግሞ ወደ ሴቶቹ ድምጽ እንምጣ፡-ለአልጋ ፍቅር ጋበዛኝ አታውቅም፤እኔም ስጋብዛት ደስተኛ አትሆንም፤ፊትዋ ጭጋግ ይለብሳል፡፡አንዳንዴ እንዲያውም በንዴት ትበግናለች፤በር ለመዝጋት የምትልከውም እኔን ነው፤ከዚያም በኋላ ከወገብ በታች ልብስዋን ታወልቃለች፤ግብረ-ስጋ ስናደርግም ፊትዋን ታዞራለች፡፡…በማለት  ግራ መጋባቱን ይናገራል፡፡አንዳንዴ እንዲያውም ብቻችንን እንድንሆን በር ለመዝጋት ትጣደፍ ነበር፤ከአልጋ መልስ ሁለታችንም በጣም ደስተኞች ነበርን፡፡ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡ከአንዱ ምክር ጠያቂ እንጀምር፡-ከሚስቴ ጋር ከተጋባን ሁለት ዓመት ሆኖናል፤ይሁን እንጂ ሚስቴ የግብረ-ስጋ ፍላጎትዋን አጥታለች፤…መጀመሪያ ላይ በጣም ጥሩ የአልጋ እርካታ ነበረን፤ሌላው ቀርቶ ሚስቴ ራስዋ ፍቅር እንስራ ብላ ትጋብዘኝ ነበር፡፡መቸም ቢሆን የግብረ-ስጋ ጥያቄዬን አሻፈረኝ ብላ አታውቅም፡፡ሰውየው የተነሱት ከአፍሪካ ተጽፎልኛል ካሉዋቸው ደብዳቤዎች ነው፡፡ ደብዳቤዎቹ ደግሞ አንጀት የሚበሉ ናቸው፡፡የጻፉት ወንዶችና ሴቶች በየራሳቸው ወጥመድ ተይዘዋል፡፡ ደብዳቤዎቻቸው በጥይት ተመትቶ ጦር ሜዳ የወደቀን ሰው ያህል ሆድ የሚያባቡና ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የዘርፉ ምሁር የሆኑት ጄን ባንዮላክ ብዙ ነገር ይነግሩናል፡፡ ሰው ምንም ያህል ቢዋደድ፣ሞትኩልሽ-ሞትኩልህ ቢባባል የስሜት ውጥረቱን መተንፈሻው አልጋ ሊሆን ግድ ሆኗል፡፡ ታዲያ ይህ የአልጋ ጉዳይ መከራው ቀላል ስላልሆነ፣ በዚህ ችግር ብዙ ሰዎች ያለቅሳሉ፡፡ ብዙ ትዳሮች ይፈርሳሉ፡፡ ዛሬም የኔ ጥረት ምናልባት እንባ የተሞሉ፣ሳቅ የወደቀባቸውን  ቤቶች ባነበብኩት መጽሃፍ ሃሳብ መርዳት ከቻልኩ ልሞክር የሚል ነው፤ማነህ አንተ የምትሉም ካላችሁ ይዤ የመጣሁት ራሴን አይደለም-ብዙ ልምድ ያላቸውን አዋቂ እንጂ!!እልፍ አእላፍ ቅኔ የዘነበለት ፍቅር ሮጦ -ሮጦ መድረሻው አንድ ነው፡፡ አይኖችዋ ክዋክብት ይመስላሉ ያልናት፤ስትስቅ ሰማይ ይነደላል ብለን ዘይቤ የረጨንላት፣እርሷን ካላገኘሁ ቤቴ መቃብር ይሁን ብለን የተወራረድንላት ቆንጆ፣ከንፈር ደርሰን፣ገላ ዳብሰን እንዳንቆም ተፈጥሮ የማሰችው ጉድጓድ ይጠራናልና ሳንደርስ አንመለስም፤ እንሮጣለን - ጥሪ ነዋ!! ፍርጃ ነው እንበል ወይስ ድንቅ ዕድል? ለቀናው ዕድል ነው፤ለተበላሸበት ደግሞ ፈተና!!ልክ አንድ ሯጭ ሮጦ-ሮጦ ክር ጋ መድረስ እንዳለበት ሁሉ የተፋቃሪዎች መጨረሻ ደግሞ አልጋ ላይ መውደቅ ነው፡፡

 

Read 152637 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 17:10