ወደ ትወና ከገባች በኋላም በሆሊዉድ በአንድ ፊልም እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ከሚከፈላቸው ተዋናዮች አንዷ ለመሆን የበቃች ስኬታማ ተዋናይት ናት፡፡ ሄሊ ቤሪ በ2001 እ.ኤ.አ በሰራችው “ሞንስተርስ ቦል” የተሰኘ ፊልም በምርጥ ተዋናይነት ኦስካር ተሸልማለች፡፡ዘንድሮ ከአዲስ ፍቅረኛዋ ከፈረንሳዊው ኦሊቨር ማርቲኔዝ ጋር ቀለበት ያሰረችው ሄሊ ቤሪ፤ በዚሁ ዓመት ከዚሁ ፍቅረኛዋ ጋር ትዳር ለመመስረት የነበራት እቅድ ከሽፎባታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከሦስተኛ ባሏ ገብሬል አውብሪ ጋር የጀመረችውን የፍርድ ቤት ክርክር ባለማጠናቀቋ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በ40ዎቹ እድሜ መጀመሪያ ላይ የልጅ እናት መሆኗን የወደደችው ሄሊ ቤሪ፤ ሌላ ልጅ የመውለድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ሰሞኑን ተናግራለች፡፡ “ከአራት ዓመት ልጄ ከናሃላ ጋር ማታ ማታ ሌላ ልጅ እንዲሰጠኝ አምላክን በፀሎት እንማፀናለን” ብላለች - ለ”ፒፕል” መፅሄት በሰጠችው ቃለ ምልልስ፡፡