Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 15:51

ኤልተን የምርጥ ነጠላ ዜማ ሽያጭን ይመራል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሰር ኤልተን ጆን ባለፉት 60 ዓመታት በብሪታኒያ የሙዚቃ ገበያ ውስጥ በነጠላ ዜማ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ የአንደኝነት ደረጃ አገኘ፡፡ በእንግሊዝ ከሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ለመሸጥ የቻሉ 123 ነጠላ ዜማዎች በማወዳደር በወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ፣ ሰር ኤልተን “ሰምቲንግ አባውት ዘ ዌይ ዩ ሉክ ቱናይት” በተሰኘ ዘፈኑ የአንደኝነት ደረጃን ተቆጣጥሯል፡፡ ለዌልሷ ልእልት ዲያና መታሰቢያነት በ1997 እ.ኤ.አ የተሰራው ይሄው ነጠላ ዜማ ለአምስት ሳምንት ገበያውን በመምራት 4.9 ሚሊዮን ቅጂዎች ተቸብችቧል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ያገኘው ነጠላ ዜማ በ1984 እ.ኤ.አ በባንድ ኤይድ የተሰራው “ዱ ዘይ ኖው ኢትስ ክሪስማስ” የተሰኘ ዜማ ሲሆን 3.6 ሚሊዮን ቅጂዎች ተሸጧል፡፡ በ1975 እ.ኤ.አ የተለቀቀው የኩዊንስ “ቦሄምያን ራህፕሶዲ” 2.36 ሚሊዮን ቅጂዎች ተሸጦ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ ቢትልሶች 6 ነጠላ ዜማዎቻቸውን በሽያጭ ደረጃ ውስጥ በማካተት ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ጆንትራ ቮልታ፣ ኦሊቪያ ኒውተን ጆን፣ ቦኒ ኤም፣ ሴሌንዲዮንና ስፓስይ ገርልስ ሁለት ሁለት ዜማዎችን ማስመዝገብ ከቻሉት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

የብሪትሽ የሙዚቃ ገበያን በመከታተል የከፍተኛ ሽያጭ ደረጃን የሚያጠናቅረው ኩባንያ፤ ባለፉት 60 ዓመታት በነጠላ ዜማ ዘርፍ በሽያጭ የተሳካላቸውን 123 ዜማዎች በአልበሞች ከፋፍሎ ለገበያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡ ከእንግሊዝ ሙዚቀኞች በስኬታማነቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው ሰር ኤልተን ጆን፤ በሙያው  በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ250 ሚሊዮን በላይ የዓልበሞቹን ቅጂዎች በመላው አለም ሸጧል፡፡ በዚህም 355 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ሃብት እንዳፈራ “ሰንደይ ታይምስ” ያወጣው የእንግሊዛውያን ሃብታም ዝነኞች የደረጃ ሰንጠረዥ ይጠቁማል፡፡

 

Read 2841 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 16:07