Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 November 2012 12:05

ቶኒ ብራክስተን በእዳ ተዘፍቃ ንብረቷን እያሸጣት ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ቶኒ ብራክስትን የተዘፈቀችበት የ50 ሚሊዮን ብር እዳ ንብረቷን እያሸጠባት መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ፡፡ ከ1989 ጀምሮ በሙዚቃ ሙያዋ ያሳለፈችው ሙዚቀኛዋ ፤ በዘፈን ደራሲነት፣ በፕሮዱዩሰርነትና በተዋናይነት ከፍተኛ ስኬት እና ክብር ያገኘች ስትሆን 6 የግራሚ፤ 7 የአሜሪካን ሚዩዚክ አዋርድ እና 5 የቢልቦርድ ሽልማቶችን ሰብስባለች፡፡

ቶኒ ብራክስተን በተለያዩ እዳዎቿ ተዘፍቃ ለኪሳራ መዳረጓን በይፋ ስታሳውቅ ከ2010 እ.ኤ.አ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ አርቲስቷ ለፍ/ቤት ባቀረበችው ማመልከቻ በኪሳራ ላይ መሆኗን ጠቁማ እዳዋን ለመክፈል በቂ ጊዜ እንዲሰጣት ብትጠይቅም፤ ሰሞኑን በጆርጂያ የሚገኝ መኖርያ ቤቷ አንዱን እዳዋን ለመሸፈን በ1.1 ሚሊዮን ዶላር እንዲሸጥ ተወስኖባታል፡፡ አርቲስቷ ለኪሳራ የተዳረገችው ቅብጠት በተሞላው ህይወቷ እንደሆነ ቢነገርም አርቲስቷ ግን አትቀበለውም፡፡ በቅርቡ በቤተሰቧ አኗኗር ላይ ያተኮረ ተከታታይ የቴሌቭዥን ቶክ ሾው ለማቅረብ ዝግጅቷን ያጠናቀቀችው ቶኒ ብራክስተን፤ ወደፊት ለምትሰራው አልበም ከአሳታሚ ኩባንያ ጋር በ20 ሚሊዮን ዶላር ተዋውላለች፡፡ 
እነዚህ ገቢዎች ከገባችበት ዕዳ እንድትወጣ ያግዟታል ተብሏል፡፡ የግራሚ ሽልማትን ከአንድ ጊዜ በላይ ያገኘችው ቶኒ ብራክስተን፤ በሰራቻቸው ስድስት የሙዚቃ አልበሞች ከ60 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች በመሸጥም ስኬታማ ሆናለች፡፡

 

Read 4693 times Last modified on Saturday, 17 November 2012 12:14

Latest from