Saturday, 24 November 2012 11:26

የጋምቤላ ሬዲዮ በቴክኒሺያን እጦት ተቋረጠ

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(1 Vote)

በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመቱ ቅርንጫፍ ሲተላለፉ የቆዩ ሶስት የጋምቤላ ሬዲዮ ፕሮግራሞች ለአስር ቀናት በቴክኒሽያን እጦት መቋረጣቸውን የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ማርቆስ ጉደታ ገለን፡፡
በመዠንገር፣ አኝዋክና ኑዌር ቋንቋዎች ከሰኞ እስከ እሁድ ከመቱ ቅርንጫፍ ይተላለፉ የነበሩ የጋምቤላ ፕሮግራሞች በቴክኒሺያን እጦት መቋጣቸው እንዳሳዘናቸው የሬዲዮው ጋዜጠኞች ገልፀው ድርጅቱ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
በ1987 ዓ.ም የአኝዋክና ኑዌር፣ በ2003 ዓ.ም የመዠንገር ቋንቋዎች ስርጭት በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዢን ድርጅት መቱ ቅርንጫፍ መተላለፍ መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

Read 2787 times