Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 11:39

“አንድነት” በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ነገ ውይይት ያካሂዳል

Written by 
Rate this item
(7 votes)

የገዥው ፓርቲ አፈናና ጭቆና መባባሱና የተቃዋሚ ፓርቲዎች
..በውይይቱ ላይ የሚነሱ ነጥቦች ናቸው
የፓርቲው ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ በአገሪቱ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታም መታገዷን ፓርቲው አስታወቀ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ነገ በጽ/ቤቱ ውይይት ሊያካሂድ ነው፡፡ ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ሃሳቦች በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ ፓርቲው የአገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ ለሚያደርገው ውይይት ይረዳል ተብሎ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሚቀርበውና ሶስት ዋና ዋና የፖለቲካ ነጥቦችን ስላካተተው የውይይት መነሻ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲናገሩ፤ “በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል፤ ይህንን ሁኔታም ለህዝቡ ለማሳወቅና በመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ለመነጋገር ውይይቱ ተጠርቷል፡፡” ብለዋል፡፡

በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይነሳሉ የተባሉት 3 ዋና ዋና ነጥቦች…የአገሪቱ ህዝብ ሁኔታ፣ የፓርቲዎች ሁኔታ (የገዥውም የተቃዋሚዎችም) እና የምህዳሩ ሁኔታ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የአገሪቱ ህዝብ ያለበት ሁኔታን አስመልክቶ በሚያነሱት ነጥብ ላይ ህዝቡ በቂ መረጃ የሌለው፣ ያልተደራጀና ብሶቱን በማጉረምረም ከመግለጽ የተሻለ ነገር ማድረግ ያልቻለ መሆኑን የሚጠቁሙ ሃሳቦች እንደሚነሱ ዶ/ር ነጋሶ ተናግረዋል፡፡ 
ህዝቡ እየደረሰበት ያለውን በደልና የኑሮ ውድነቱን ተሸክሞ እያጉረመረመ ከመኖር በዘለለ አንዳችም ትርጉም ያለው ንቅናቄ ሲያደርግ አለመታየቱን የተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ፤ በዚህ በኩል የእስልምና እምነት ተከታዮች እያካሄዱት ያለው ንቅናቄ የተሻለ ነው ብለዋል፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የገዥውም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በዶ/ር ነጋሶ የሚነሳው የውይይት መነሻ ሃሳብ መድብለ ፓርቲ አለመኖሩን፣ ዲሞክራሲያዊ ያልሆነና አፋኝ ገዥ ፓርቲ መኖሩን፣ ገዥው ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማይከተልና አፋኝ ሥርዓት መሆኑን፤ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎች እራሳቸው ጥንካሬና ጽናት የሚጐድላቸውና የተበጣጠሱ እንደሆኑ የሚያመለክቱ ናቸው ተብሏል፡፡
በገዥው ፓርቲ በኩል ከምርጫው በፊትም ሆነ በምርጫው ወቅት ፍትሃዊና የተስተካከለ የምርጫ ሂደት አለመኖሩን የሚያመለክቱ ነጥቦችም እንደሚነሱ ተገልጿል፡፡ ከፕሬስ ነፃነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችም በውይይቱ ላይ እንደሚያነሱ ዶ/ር ነጋሶ በዚሁ ጊዜ ተናግረዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የፓርቲው ልሣን የሆነው “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ በአገሪቱ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታም እገዳ እንደተጣለበት ከፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Read 4059 times