Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:42

በአ.አ 125ኛ አመት ትያትሮች ተወዳድረው ተሸለሙ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አዲስ አበባ ከተማ የተመሰረተችበትን 125ኛ አመት በማስመልከት ተከጋጅቶ በነበረው እየታዩ ያሉ ትያትሮች ውድድር የተመረጡ ትያትሮች ልዩ ሽልማት ተሰጣቸው፡፡ ዋፋ ኮሙኒኬሽን ባስተባበረው ውድድር የተሳተፉት ስምንት ትያትሮች “ምርጥ” በመባል በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድረው ተሸልመዋል፡፡በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ከትናንት ወዲያ ማታ በተደረገው የሽልማት ሥነ ሥርዓት በምርጥ የተውኔት ፅሁፍ የኃይሉ ፀጋዬ “ቤተሰቡ” አንደኛ፣ የዘካርያስ ብርሃኑ “የበዓል እንግዶች” ሁለተኛ፣ የአለልኝ መኳንንት “የፍቅር ካቴና” ሦስተኛ ሆነው 125ኛ አመቱን የሚያንፀባርቅ የወርቅ፣ የብርና እና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸልመዋል፡፡ በምርጥ አዘጋጅ የዳግማዊ አይሳ ቤተሰቡ፣ የዘውዱ አበጋዝ “የበአል እንግዶች” ሁለተኛ፣ የገነት አጥላው ዝግጅት የሆነው “ጓደኛሞቹ” ሦስተኛ ሆነው ተሸልመዋል፡፡ 

በምርጥ ፕሮዳክሽን እና ምርጥ ሴት ተዋናይ የብሔራዊ ትያትሩ ሕንደኬ ትያትር አንደኛ ሲሆን በምርጥ ሴት ተዋናይ የሐገር ፍቅር ትያትሯ “የበአል እንግዶች” ተዋናይት ትእግስት ግርማ የተሸለመች ሲሆን በሌሎች ዘርፎችም ሌሎች ትያትር ቤቶች ሲሸለሙ በጀትን ጨምሮ በአጠቃላየ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ተደንቋል፡፡ 
ሽልማቱ ሐሙስ ማታ ሲከናወን የወጣቶች በተለያዩ የኪነጥበብ ዘርፎች ተወዳድረው ተሸልመዋል፡፡

Read 3197 times