Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:56

ውሻዋን ለማስታመም ኮንሰርት ሰረዘች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የግራሚ ተሸላሚዋ አሜሪካዊት ዘፋኝ ፊዮና አፕል፣ ውሻዬ በሞት አፋፍ ላይ ነች በማለት የኮንሰርት ዝግጅቶቿን ሰረዘች።
በብራዚል ሊካሄድ የታሰበውን የ12 ቀን ኮንሰርት የሰረዘችው ሳምንት ብቻ ሲቀረው ነው። በፌስቡክ ለአድናቂዎቿ ባስተላለፈችው የሚያስተዛዝን መልዕክት፣ በውሻዋ የመሞቻ ሰዓት ከአጠገቧ መራቅ እንደማትፈልግ ገልፃለች። ጃኔት ብላ የሰየመቻትን ውሻ ከ10 አመት በፊት በሎሳንጀለስ እንዳገኘቻት ፊዮና ስትተርክ፣ በሌሎች ውሾች ተነካክሳና ተጎሳቁላ ነበር ብላለች።

ሰው ላይ የማትደርሰው ጃኔት፤ ሃዘን ሲሰማኝና ልቤ ሲሰበር ከጎኔ የማትለይ አፅናኜና ታማኝ ጓደኛዬ ናት ብላለች ፈተና። ጃኔት ከሁለት አመታት ወዲህ ደረቷ ውስጥ በወጣባት እጢ ስትሰቃይ ቆይታ የሞት አፋፍ ላይ ደርሳለች የምትለው ፊዮና፤ አሁን ከአጠገቧ መራቅ አልችልም በማለት ኮንሰርቶቿን ለመሰረዝ መወሰኗን አስረድታለች። የሁላችንም ማንነት የሚገለፀው በምርጫዎቻችን እና በውሳኔዎቻችን ነው የምትለው ፊዮና፤ ከፍቅርና ከጓደኝነት በፊት ሥራን የማስቀድም ሰው አይደለሁም፤ ከቤት ሳልወጣ ጃኔትን ለመንከባከብ ወስኛለሁ ብላለች። ፊዮና ከ15 አመት በፊት ባሳተመችው የመጀመሪያ አልበም ግራሚ ከመሸለሟም በተጨማሪ ከ2 ሚ. በላይ ኮፒ ሸጣለች። ከዚያ ወዲህ በሰራቻቸው አራት አልበሞች ግን ብዙም ተወዳጅነት አላገኘችም።

Read 4082 times