ኤልሳቤጥ ካሁን ቀደም ከፍተኛ አድናቆት ባተረፈውና በኢትዮጵያ ሬዲዮ በተላለፈው ..የማዕበል ዋናተኞች.. ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ከዋና ገፀ-ባህርያት የአንዷን በመጫወትና በሌሎችም ሥራዎች ታዋቂነትን ማግኘቷ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በሚጀመረው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ከሷ ሌላ አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም፣ ሽመልስ አበራ፣ ስናፍቅሽ ተስፋዬ፣ ውባለም አለባቸው፣ ሐረገወይን እሸቱ፣ ጀምበር አሰፋ፣ ትዕግስት ግርማ እና ሌሎች ከሰባት በላይ ተዋንያን ይሳተፋሉ፡፡ ዘወትር ቅዳሜ የሚደመጠው ድራማ ሐሙስ ሐሙስ ይደገማል፡፡
በተያያዘ ዜና በረሽድ ጀማል ተደርሶ በእስጢፋኖስ ከበደ የተዘጋጀው ..የሶስት ወር ምርኮኛ.. የተሰኘው ኮሜዲ ቴአትር የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ይመረቃል፡፡ ቴአትሩ ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩር ነው፡፡