Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:27

ስውር መንገደኞች.. ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ዛሬ ይጀመራል

Written by 
Rate this item
(4 votes)

..የሶስት ወር ምርኮኛ.. ቴአትር ይመረቃል
አልሳቤጥ መላኩ ወደ ትወናው ተመለሰች
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በርካታ መጣጥፎችን በመጻፍ የሚታወቀው አንተነህ ይግዛው የጻፈው ..ስውር መንገደኞች.. የሬድዮ ድራማ፤ ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት በፋና FM 98.1 እና በክልል FM ጣቢያዎች መደመጥ ይጀምራል፡፡ ዘካርያስ ብርሃኑ ባዘጋጀውና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፕሮዲዩስ ባደረገው የ52 ሳምንት ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ከ6 ዓመት በላይ ከትወና መድረክ ርቃ የነበረችው ተዋናይት አልሳቤጥ መላኩ ከሰባት ዋነኛ ተዋናይ አንዷ በመሆን ትተውናለች፡፡

ኤልሳቤጥ ካሁን ቀደም ከፍተኛ አድናቆት ባተረፈውና በኢትዮጵያ ሬዲዮ በተላለፈው ..የማዕበል ዋናተኞች.. ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ከዋና ገፀ-ባህርያት የአንዷን በመጫወትና በሌሎችም ሥራዎች ታዋቂነትን ማግኘቷ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በሚጀመረው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ከሷ ሌላ አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም፣ ሽመልስ አበራ፣ ስናፍቅሽ ተስፋዬ፣ ውባለም አለባቸው፣ ሐረገወይን እሸቱ፣ ጀምበር አሰፋ፣ ትዕግስት ግርማ እና ሌሎች ከሰባት በላይ ተዋንያን ይሳተፋሉ፡፡ ዘወትር ቅዳሜ የሚደመጠው ድራማ ሐሙስ ሐሙስ ይደገማል፡፡
በተያያዘ ዜና በረሽድ ጀማል ተደርሶ በእስጢፋኖስ ከበደ የተዘጋጀው ..የሶስት ወር ምርኮኛ.. የተሰኘው ኮሜዲ ቴአትር የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ይመረቃል፡፡ ቴአትሩ ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩር ነው፡፡

Read 8347 times