Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 16 July 2011 11:53

የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ መጽሐፍ ወጣ

Written by 
Rate this item
(11 votes)

admass negasoበኢህአዴግ መታለላቸው እንደሚቆጫቸው ይናገራሉ
• ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ለፕሬዚዳንትነት ታጭተው ነበር
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ህይወት የሚተርከው ..የነጋሶ መንገድ.. የተሰኘ አዲስ መሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ በኢህአዴግ ለ10 ዓመት መታላለቸው እንዳስቆጫቸው በመሐፉ የተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ፤ ..ኢህአዴግ ሶሻሊዝምን ጠረጴዛ ሥር የከተትነው በ84 ዓ.ም ነው፤ የምንመራው በነጭ ካፒታሊዝም ነው.. ማለቱ ዱብ ዕዳ ሆኖባቸው እንደነበር ገልዋል - ከፓርቲው  የወጡበት ዋናው ምክንያትም ይሄው እንደሆነ በመጠቆም፡፡

በጋዜጠኛ ዳንኤል ተፈራ ተፎ ለንባብ የበቃው መሐፍ፤ የዶ/ር ነጋሶን የህይወት ታሪክ ከትውልዳቸው ጀምሮ የሚተርክ ሲሆን ከደምቢዶሎ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፤ ከጀርመን የስደት የፖለቲካ ትግል እስከ ኢህአዴግ አባልነትና ርዕሰ ብሄርነት እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ድረስ የወጡትንና የወረዱትን የፖለቲካ መንገድ ያስቃኛል፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ታሪካቸውን በተናገሩበት በዚህ መሐፍ፤ እሣቸው ለርዕሰ ብሔርነት ¬tW ወደ ስልጣን ከመውጣታቸው በፊት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ለርዕሰ ብሔርነት ተጠቁመው እንደነበርና ..የኢትዮጵያ ህዝብ ሴት ርዕሰ ብሔር ለመምረጥ ዝግጁነት የለውም.. በሚል ሃሳቡ ውድቅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ነጋሶ ወደ አንድነት እንዴት እንደገቡ፤ ስለ 97ቱ ምርጫና የ ..ቅንጅት.. ፓርቲ ውድቀት እና ሌሎች በርካታ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በመጽሐፉ አብራርተዋል፡፡ ነጋሶ ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲና ኒዮሊበራሊዝምም ተናግረዋል፡፡ ጋዜጠኛ ዳንኤል ተፈራ መሐፉን ለማዘጋጀት ሦስት ወር የፈጀ ቃለምልልስ ከዶ/ር ነጋሶ ጋር ያደረገ መሆኑን ጠቁሞ ነጋሶ ታሪካቸውን በልግስና ስለነገሩት ምስጋናውን በመግቢያው ላይ አስፍሯል፡፡ ..የነጋሶ መንገድ.. በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ አንባቢያን ስለመሃፉ ይዘት ግንዛቤ ይጨብጡ ዘንድ አለፍ አለፍ ብለን በገ 5 ላይ አውጥተነዋል፡፡

 

Read 6530 times Last modified on Monday, 18 July 2011 11:44

Latest from