Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 12:14

በፖለቲካና በቃላት ጨዋታ ችግሮች አይፈቱም..

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አቶ ሙሼ የኢዴፓ ሊቀመንበር
ድርቅ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፤ ይሁን እንጂ ድርቅ በተከሰተበት አገር ሁሉ ረሃብ ይፈጠራል ማለት አይደለም፡፡ በቂ ክትትልና ዝግጅት ቢኖር ኖሮ፤ ድርቅ የዜጎችን ህይወት እንዳይፈታተን ማድረግ ይቻላል፡፡ በአገራችን ግን፤ በድርቅ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን የረሃብ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ መንግስት ከመናገሩ በፊት፤ ከተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ድርቅና ረሃብ እንደተከሰተ ስንሰማ ቆይተናል፡፡ ይህም፤ በመንግስት በኩል ትኩረት ሳይሰጠው እንደቆየ የሚያሳይ ነው፡፡ የችግሩ ምንነት ቀድሞ እንዲታወቅ በማድረግ፤ ችግር ሳይባባስ መፍታት ይገባ ነበር፡፡

በአንዳንድ ቦታ በድርቅ ምክንያት ብዙ ከብቶች መሞታቸው፤ በተለይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ ከባድ አደጋ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቅርቡ ከብቶች እየሞቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ መንግስት ስለ ድርቅ ሁኔታውና ስለ ረሃብ አደጋው ቀድሞ አለማሳወቁ በጣም አሳሳቢ ሆኖብናል፡፡ የከብቶች መሞት፤ የድርቁ ሁኔታ ውስብስብና አሳሳቢ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ የሞት አደጋው ወደ ሰዎች ከመዛመቱ በፊት፤ መንግስት እርዳታ የማመቻቸትና የሰዎች ህይወት እንዳይጠፋ የመከላከል ሃላፊነት አለበት፡፡ ዜጎች እንዳይሞቱብን ነው እኛ ምንፈልገው፡፡ ነገር ግን ከጊዜያዊ እርዳታ በተጨማሪ፤ የሚያዛልቅ መፍትሄም ያስፈልጋል፡፡ በየአመቱ እንዲህ ዓይነት ቀን እየመጣ ዜጎቻችንን የሚላስ የሚቀመስ ነገር እያሳጣና ህይወት እየቀጠፈ መቀጠል የለበትም፡፡ ሁሉም ዜጋ ተረባርቦ እንደዚህ ዓይነቱን ችግር መመከትና መከላል ይጠበቅበታል፡፡
ድርቅ የተፈጥሮ ጉዳይ ቢሆንም፤ የመንግስት ራሱ የሚያራምደው የኢኮኖሚ ፖሊሲም ችግር የሚፈጥር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ መንግስት በአርሶ አደሩ ዙሪያ እየሰራ ነው ሲባል የምንሰማ ቢሆንም፤ በሚፈለገው መንገድ ለውጥ እያመጣ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ ድርቅ በአሜሪካም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በሌሎች አገሮችም በየጊዜው ይከሰታል፡፡ ድርቅ እንዳይከሰት ማድረግ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ ማድረግ፤ የተለያዩ የስራና የምርት ዘዴዎችን በመጠቀም ረሃብ እንዳይከሰት ወይም እንዳይባባስ ማድረግ ችለዋል፡፡
አምና ሁለት ሚሊዮን የነበረው የረሃብ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 4.5 ሚሊዮን መጨመሩ አሳሳቢ ነው፡፡ ነገር ግን ቁጥሩ ባይጨምር እንኳ፤ ከአመት አመት ዜጎች ተራቡብኝ ብሎ ሁልጊዜ እርዳታ መለመንም አሳፋሪ ነው፡፡ እስከ ስንት ዘመን ነው የምንለምነው፡፡ ሁልጊዜ ምጽዋት ጠያቂ የምንሆነውና እንደሌሎቹ አገራት፣ እንደሌሎቹ ማህበረሰቦች ችግራችንን ለመፍታት ከመጣር ይልቅ ኃላፊነታችን የማንወጣ ሆነን መታየት የምንቀጥለው እስከመቼ ነው?
የምግብ እርዳታ መለመንና ማከፋፈል ጊዜያዊ መፍትሄ ነው፡፡ ዘላቂ መፍትሄ ግን አይደለም፡፡ ሰዎች ተርበዋል፤ ተጠምተዋል፤ ተቸግረዋል... በተለይ ደግሞ ህፃናትና አረጋውያን፡፡ በፍጥነትና በአግባቡ የምግብ እርዳታና ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ለዘላቂ መፍትሄ እንቅፋት እየሆነ ያለው የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው፡፡ የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ካልተስተካከለ፤ በተለይ አርሶ አደሩን ምርታማ በሆኑ ቦታዎች ካለሰፈረ፣ በዘመናዊ እርሻ ምርታማነት የሚያድግበትን ሁኔታ ካላመቻቸ፣ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ካልተደረገ፣ ገበሬዎች ዝንታለማቸውን ምርታማ ባልሆኑ መሬቶች ላይ ታስረውና ተቀይደው እንዲቆዩ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ካልተቀየረ፤ ድርቅ ሁልጊዜ ከረሃብ ጋር እጣፈንታችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡ አሁን፤ አዎ፤ ሰዎች እየተራቡ ነው፤ የኑሮ መሰረት የሆኑ ከብቶች ሞተዋል፡፡ ቅድሚያ የሰዎችን ህይወት የማዳን ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ ከዘላቂ መፍትሄ አንፃር ስናየው ደግሞ፤ ከአመት አመት ከድርቅ ጋር ረሃብ መባባሱ፤ መንግስት ፖሊሲውን ማስተካከል እንደሚጠበቅበት ያሳያል፡፡
አሁን የተከሰተው ችግር የምግብ እጥረት እንጂ ረሃብ አይደለም የሚባለው አነጋገር፤ የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡ ይሄ በኢህአዴግም የለመደ ነው፡፡ የተለያዩ የውጭ መንግስታትም ሲሉት የነበረ ነው፡፡ በድርቅ የሰው ልጅ እንደቅጠል ሲረግፍ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እጥረት ተከሰተ ብለው የሚናገሩ ነበሩ፡፡ የቃላት ጨዋታ ነው፡፡ መንግስት ከእንደዚህ ዓይነት የቃላት ጨዋታ ወጥቶ፤ ትኩረቱን ወደ ዋናው ጉዳይ በማድረግ ችግሮቹን በአስቸኳይና በአፋጣኝ የሚፈታ አቅጣጫ መያዝ አለበት፡፡ በፖለቲካና በቃላት ጨዋታ፤ ችግሮች አይፈቱም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፤ ዛሬ አለም በደረሰበት የቴክኖሎጂ ምጥቀት፤ የቃላት ጨዋታ ማምለጫ አይሆንም፡፡ የተለያዩ መንግስታትና አለማቀፍ ተቋማት በሳተላይት ተከታትለው በሚያገኙት መረጃ፤ በሱዳንና በሶማሊያ፣ በኢትጵያና በኬንያ ምን ያህል ድርቅ እንደተከሰተ አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ እንደቆዩም ተናግረዋል፡፡ መንግስት፤ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጥ ከቆየ፤ በአባይና በወቅታዊ ጉዳዮች ራሱን ወጥሯል ማለት ነው፤ የክልሎች መንግስታትና አስተዳደሮች ስራቸውን እየተወጡ አይደለም ማለት ነው፡፡ ይህ አደገኛ ሁኔታ ነው፡፡ ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት ቢደረግ ኖሮ፤ ረሃቡ እንዳይባባስ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡
ዘላቂው መፍትሄ ግን የመንግስትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማስተካከል ነው፡፡ በ4.5 ሚሊዮን ህዝብ ላይ የምግብ እጥረት እንጂ ረሃብ አልተከሰተም ብሎ መናገር ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም፡፡ 8 ሚሊዮን ደግሞ የሴፍቲ ኔት ተረጂ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የአርሶ አደሮች ቁጥር፤ የእርሻ ኢኮኖሚው መሸከም ከሚችለው በላይ እንደሆነ ነው የምናምነው፡፡ አርሶ አደሩ ዝናብ በሚጠብቅ የእርሻ ስርአት ውስጥ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮውን መቀጠል የለበትም፡፡ ቀስ በቀስ ወደ ዘመናዊ እርሻ ብቻ ሳይሆን ወደ ኢንዱስትሪና ወደ አገልግሎት ክፍለ ኢኮኖሚዎች መግባት የሚችልበት ስርዓት እንዲፈጠር ነው የምናሳስበው፡፡
መንግስት የሚፈልገው አርሶ አደሩ ከመሬቱ ጋር ተሳስሮ እንዲቆይ ነው፤ ይህ አሰራር ትክክል አይደለም ብለን እናምናለን፡፡ የትኛውም አገር ተዙዋዙረን እንዳየነው፤ አገራቱ በኢኮኖሚና በእድገት ለመሻሻል የቻሉት bxþNdST¶Ãላይz¤>N ነው፡፡ በአርሶ አደር የተመራ ኢኮኖሚ የትም ደርሶ አያውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ  ከጠቅላላው ህዝብ 83 በመቶው አርሶ አደር ነው፡፡ መሬት ኖሮት የሚያርሰው 10 በመቶ አይሞላም፡፡ ሌላው ጥገኛ ነው ማለት ነው፡፡ ጥገኛው ለረሃብና ለተለያዩ ችግሮች ይጋለጣል፡፡ መንግስት lኢንዱስትሪW ለአገልግሎት ክፍለ ኢኮኖሚዎች ዘርፍ ትኩረት መስጠት ይኖርበታል፡፡ ሴፍቲኔት ምናምን እያሉ አርሶ አደሩ ከመሬቱ ጋር ተሳስሮ እንዲቆይ ማድረግ አግባብ አይደለም፡፡
መፍትሄው ለገጠሩ ብቻ ሳይሆን ለከተማውም ነው፡፡ የአገራችን ከተሞች ውስጥ በኑሮ ውድነትና በችግር የሚሰቃየው ሰው እጅግ ብዙ ነው፡፡ መንግስት ሊገልፀው የማይፈልገው ቢሆንም፤ በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች የሰማነው መረጃና በዓይናችን በግንባር የምናየው ሁኔታ ነው፡፡ በቤታችን፣ በሰፈራችን፣ በየቀያችን፣ በአካባቢያችን የኑሮ ችግር አለ - ያፈጠጠ ያገጠጠ፡፡ ከኢኮኖሚ ድቀቱ፣ ከዋጋ ግሽበቱና ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ ልመና በከተማው እየተስፋፋ ነው፡፡  ድሮ በማይታይ ደረጃ፣ የአገራችን ከተሞች ተርበዋል - በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ፡፡ መንገዶች ላይ፤ መነቃነቅ በማይቻልበት ሁኔታ ነው ልመናን እያየን ያለነው፡፡ የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ ከመሆን ይልቅ፤ የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሰለባ እየሆነ ነው - ህዝባችን፡፡ የከተሞቻችን ችግር፤ ጎዳና ተዳዳሪነትን፣ ሴተኛ አዳሪነትን፣ ዘረፋንና ውንብድናን ነው የሚያስፋፋው፡፡ lኢኮኖሚÃêEW ችግር መንግስት ራሱ ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው፡፡
መንግስት የሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ መለወጥ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ፣ በስራ ፈጣሪነትና በንግድ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ብዙ ህዝብ አለ፡፡ ይሄ ዘርፍ ትኩረት ስለተነፈገው ነው፤ ፋብሪካዎች የማይስፋፉት፣ ኢኮኖሚው የማያድገው፤ አገር የማይበለጽገው፡፡ መንግስት ሌሎች ዘርፎች ላይ የሚሰጠውን ትኩረት እነዚህም ላይ መስጠት አለበት፡፡ ህዝቡ በጥረቱ ለኑሮው የተሻለ ገቢ ይፈጥራል፤ አልፎ ተርፎም መንግስት ከህዝብ የሚፈልገውን የግብር ገቢ ያገኛል - መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የሚያግዝ፡፡ ህዝቡ ለኑሮው የተሻለ ገቢ እንዲፈጥር ሁኔታው ሳይመቻችለት፤ ያለችውንም ሃብት ለመሰረተ ልማት ትውላለች እየተባለ መንግስት ተቀራምቶ የሚወስድ ከሆነ፤ የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ግሽበቱ አይቃለልም፡፡ መንግስት ሁልጊዜ ከገቢው በላይ ወጪ እያወጣ፤ በከፍተኛ የበጀት ጉድለት ችግሮቹን እያባባሰ ይቀጥላል፡፡

Read 6090 times