መንግሥትና ህዝብ ሆድና ጀርባ በሆነበት፣ ሙስና በተንሰራፋበት፣ በዚች ሀገር ጉዳይ የሚመለከታቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆኑ ምሁራን በአስተሳሰብ ሳይሳተፉ በጥቂት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በተዘጋጀ ኮንትራት በተአምር ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያንም ማሳደግ አይችልም፡፡ ከገጠመን የረሃብ ማጥ ሊያወጣን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ ልትወጣ የምትችለው፤ የተረጋጋ የፖለቲካ አካሄድና ሰላም ሲኖር፤ እንዲሁም ከምንም በላይ ሙስና ከዚች ሀገር ሲወገድ ነው፡፡
ገዢው ፓርቲ የዚችን ሀገር ችግር ይፈታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ በሥልጣን ላይ እንዴት እቆያለሁ የሚል ነው ሃሳቡ፡፡
የህይወት ዘመን ተረጂ ተሁኖ፣ በልመና ሀገር አያድግም፡፡ ሀገራዊ በሆነው ጉዳይ ብሔራዊ ጥሪ ተደርጎ፤ አገር እና ትውልድን ለማዳን፤ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር ለማውጣት ርብርብ ካልተደረገ በስተቀር መፍትሔ አይመጣም፡፡ በከተማ ውስጥም የኑሮ ውድነቱን የፈጠረው ሙስና ነው፡፡ykt¥WS ገመናውን ሸፍኖት እንጂ ሁሉም ችግረኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በቀን ሁለት ጊዜ አይደለም አንድ ጊዜ ጠግቦ እንኳ የሚያድር የለም፡፡
በዚህች አገር ላይ የተፈጠረውን ችግር እኛ ኢትዮጵያWÃNM\ አለም አቀፉም ኅብረተሰብ ተረባርቦ መፍታት ካልቻለ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቀውስ ይፈጠራል፡፡