Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 12:21

..ሰዎች... የህክምና ተቋምን በማመን ላይ ናቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም መካከል አፋጣኝ የሆነ እና ሁሉንም አገልግሎት ያካተተ የማህጸን ሕክምና በመላው አገሪቱ ከትላልቅ ሆስፒታሎች ራራቅ ባሉ አካባቢዎች እንዲሰጥ የሚያስችለው (Comprehensive Emergency Obstetric and New Born care)  የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት  በአገሪቱ ከዋና ከተሞች በእርቀት ላይ ያሉ እናቶች እና ሕጻናት በአቅራራቢያቸው በሚገኙ የህክምና ተቋማት ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የታቀደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከኢፊድሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስርና እርዳታ ከሚያደርጉ አካላት ጋር በመተባበር የጽንስና ማህጸን ህክምና ባለሙያዎችን ቀጥሮ በማሰማራራት በ12 አካባቢዎች በሚገኙ የህክምና ተቋማት የህክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ላይ ሲሆን ከፊሎቹንም አስመርቆአል፡፡
አቶ መብራራቱ ማሴቦ ከደቡብ ብሄር ብህረሰቦች ዳውሮ ዞን ተርጫ የመጣ ተመራራቂ ነው፡፡ በሙያው አድቫንስ የጤና መኮንን ሲሆን ላለፉት ስምንት አመታት በጤና መኮንንነት ›ÑMÓKA›M፡፡ ..ተርጫ ከአዲስ አበባ ወደ አምስት መቶ አስራራ አምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ አካባቢ ስትሆን በአዋሳ ወይንም በሆሳእና በኩል በመጉዋዝ የምትገኝ ናት፡፡ ዞኑ ከሌሎች ዞኖች ለየት የሚያደርገው የመሬቱ አቀማመጥ እጅግ አስቸጋሪ የሆነበት ተራራራራማ እና በኦሞ ወንዝ የተከበበ ደሴት ነው፡፡ በመሬቱ አቀማመጥ የተነሳም ከፍተኛ የሆነ የመንገድ ችግር ያለበት ስለሆነ ህብረተሰቡ በተለይም እናቶች ብዙ ችግሮችን ሲጋፈጡ የኖሩበት ነው፡፡ በአካባቢው አንዲት እናት ስታረግዝ ሁሉም ሰው ሴትየዋ በሰላም እንደምትገላገል ወይንም እንደማትገላገል በጥርጣሬ የሚጠብቅበት ሁኔታ ያለበት ነበር፡፡ እናቶች ወደከፍተኛ ሕክምና የሚተላለፉበት አጋጠሚ ቢኖር በመንገድ እና በባለሙያ እጥረት ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉት በቁጥር በርካታ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ.. እኔ የማልረሳው ነገር በጤና ጣቢያ በምሰራራበት ወቅት አንዲት እናት 120 ኪሎ ሜትር ተጉዛ ጤና ጣቢያ ከደረሰች በሁዋላ ማዋለድ ስላልተቻለ ወደከፍተኛ ሕክምና እንድትሄድ ግልጽ መኪና ከአስተዳደር ተለምኖ ወደ ቀጣዩ የህክምና ተቋም 170 ኪሎ ሜትር ተጉዛ ገና ሐኪም ቤት ደጃፍ ስትደርስ ነበር እጃችን ላይ ያረፈችው፡፡ የዛችን እናት አስከሬን ጭነን በሄድንበት መኪና መልሰን ጭነን ነበር ¾}SKeነው፡፡ በኢሶግ የተመቻቸው ስልጠና ከመሰጠቱ  ከስድስት ወር በፊት በሆስፒታሉ ደርሰው የሞቱት እናቶች ቁጥር 24/ሀያ አራራት ሲሆን ስልጠናው መሰጠት በጀመረበት ጊዜ ግን አሰልጣኙ የህክምናው ባለሙያ እያስተማረን ይሰራራ ስለነበርና የቀዶ ሕክምናው አገልግሎት መሰጠት ስለተጀመረ ሁለት እናቶች... ያውም ከአቅም በላይ በሁነ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ ይህ እንግዲህ ወደህክምና ተቋም በመምጣት አገልግሎት ካገኙት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ስልጠናው የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ ከፍተኛ ጥቅም እያስገኘ በመሆኑ ሰዎች በቤታቸወ ውስጥ መውለድን ትተው የህክምና ተቋምን በማመን ላይ ናቸው፡፡..


ከጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ተወክለው በምረቃው ላይ የተገኙት አቶ ሓይሉ ጥሩነህ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ኦፊሰር እንደሚሉት ..በጋምቤላ ስልጠናውን የወሰዱት ሁለት ባለሙያዎች ናቸው፡፡ በጋምቤላ አካባቢ የእናቶችና የህጻናት ጤና  ክትትል ቀድሞ ከነበረው በተሻለ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ቀደም ሲል ወደ ጤና ተቋማቱ በመምጣት ብቻ አገልግሎቱን ያገኝ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በጤና ኤክስንሽን ሰራራተኞች አማካኝነት በየወረዳው ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ ተፈጥሮአል፡፡ በጋምቤላ ያው የጤና አገልግሎት ከበፊቱ ሲነጻጸር በጣም በተሸለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ አሁን ደግሞ በጽንስና ማህጸን ጤና በኩል በተሸለ ሁኔታ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱ ቀደም ሲል ይሰጥ የነበረውን የህክምና ሽፋንና ደረጃውን በተሻለና ሰፋ ባለ ሁኔታ ለማቅረብ ያስችላል.. ብለዋል፡፡
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የጤና ቢሮውን ወክላ የመጣችው ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ እንደገለጸችው ..በቤንሻንጉል ጉሙዝ እናቶችን ለከፍተኛ ችግር ይዳርግ የነበረውን ባህል ወይንም ልማድ ለመለወጥ ተሞክሮአል፡፡ ቀደም ሲል አንዲት ሴት ስትወልድ ወደጫካ ሄዳ የምትገላገልበት እንዲሁም በቤት ውስጥ በከፍተኛ ችግር የሚወልዱበት ሁኔታ ነበረ፡፡ አሁን ግን የጤና ኤክስንሽን ከተጀመረ በሁዋላ ቢያንስ እርጉዝዋ ሴት ወደቤት ገብታ መውለድ እንዳለባት ብዙዎች አምነው እየተገበሩት ነው፡፡ በቤት ውስጥም ሲወልዱ በሰለጠኑ አዋላጆች የሚገላገሉበት ሁኔታ ተፈጥሮአል፡፡ ላለፉት ስድስት ወራራት  በኢሶግ የተሰጠው ስልጠና ከመጀመሩ በፊት እናቶች ወደ ኦሮሚያ ጊምቢ ሆስፒታል እየተላለፉ የሚወልዱበት ሁኔታ ነበር ፡፡ በጤና ጣቢያ ደረጃ ያሉት ግን እንደ ሚፈጠረው አጋጣሚ ወይ በሰላም ይገላገላሉ አለዚያም ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡ አሁን ግን ወደሌላ የህክምና ተቋም መሄድ ሳያስፈልጋቸው በአቅራራቢያቸው ሆስፒታል ውስጥ የሚገላገሉበት ሁኔታ ተፈጥሮአል፡፡ ክልሉ ህብረተሰቡን በማስተማር ግንዛቤ እየለወጠ የሚገኝበት ሁኔታ እና አገልግሎቱም በመሻሻል ላይ የሚገኝበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡..
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት እንደገለጹት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር፣ WHO,  UNFPA,  UNICEF , WORLD BANK  ጋር በመተባበር የጀመረው  የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና የማካሄደው በአስራራ ሁለት ቦታዎች ነው፡፡ አሰልጣኞች የተመደቡትም በኦሮሚያ ሶስት ቦታ፣ በደቡብ ሁለት ቦታ፣ በጋምቤላ በቤንሻንጉልና ጉምዝ አንድ ቦታ፣ በአፋር አንድ ቦታ፣ በሶማሌ በትግራራይ በአማራራ ሁለት ቦታ ሲሆን ስፍራራው የተመረጠውም የክልል የጤና ቢሮዎች ባመኑበት ሁኔታ ነው፡፡ ከአዲስ አበባና ድሬደዋ በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች በተካሄደው የሐኪሞች ስልጠና /26/ሀያ ስድስት  የሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ለምረቃው የበቁት በዱፍቲ፣ ዱራራሜ፣ ጋምቤላ፣ ኩዩ፣ ፓዌ እና ተርጫ ሆስፒታል የሰለጠኑ እና በዚያው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው፡፡ የአፋጣኝ እና የተሟላቀዶ ሕክምናን የጨመረ የጽንስና ማህጸን ሕክምና በርቀት ላሉ እናቶች የማዳረስ ስራራው እንዲሰራራ የታቀደው
•uÉI[ እና ቅድመ ምረቃ ያለውን የጤና ሙያተኞች ቁጥር በመጨመር፣
•uÉI[ ምረቃ የጤና መኮንኖችን በአጭር ጊዜ ትምህርት በማስተርስ ደረጃ አገልግሎቱን በስፋት የሚያዳርሱበትን ስራራ በመስራራት፣
•በስድስት ወር ጊዜ አስፈላጊውን“ መሰረታዊ የሚባሉትን እውቀት እና አመለካከት በመያዝ አገልግሎቱን በተቻለ መጠን ሊያዳርሱ የሚችሉ ሙያተኞችን በማፍራራት ነው፡፡
አፋጣኝ እና በሁሉም ቦታ አስፈላጊውን የማህጸን ህክምና የመስጠት ፕሮጀክት ዋና አላማ እውቀት ያላቸው የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ከዚህ በፊት አገልግሎቱ በማይሰጥባቸው እሩቅ አካባቢዎች በመሄድ በእያንዳንዱ ቦታ ቢያንስ ሁለት ሐኪሞችን እንዲያሰለጥኑና በቆይታቸውም የሚያጋጥማቸውን ድንገተኛም ሆነ ድንገተኛ ያልሆነ ማንኛውንም አይነት ሕክምና እንዲሰጡ ማስቻል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎቱንና የጥራራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲቀጥል የሚያስችል ሁኔታዎችንም መፍጠርን አላማው ያደረገ ነው፡፡  
በስልጠናው ቆይታ ወቅት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥባቸወ በተመረጡት እና ለሐኪሞች ስልጠና በተሰጠባቸው በርቀት በሚገኙ አካባቢዎች ወደ 1592አንድ ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት በላይ የማዋለድ ስራራ የተሰራራ ሲሆን ወደ 530 የሚደርስ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ተሰጥቶአል፡፡ ከዚህ ውስጥ ወደ 352 የሚሆነው አጣዳፊ የሆነ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሲሆን 138 የሚደርሱት ደግሞ ከማዋለድ ውጭ ሌሎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎቶች ናቸው ፡፡
የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ከሰተ ብርሀን አድማሱ እንደገለጹት የእናቶችንና የሕጻናትን ጤና ማሻሻል አንዱ ቁልፍ ተግባር መሆኑ በመንግስት ከፍተኛ እምነት የተደረገበት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ባደረገችው ጥረት የህጻናት ሞት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶአል፡፡ በኤችአይቪ፣ በቲቪ፣ በወባ በመሳሰሉት በሽታዎች ምክንያት ለህልፈት ይዳረጉ የነበሩ እናቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ተደርጎአል፡፡ በሚሊኒየሙ የልማት ግብ መሰረት ትኩረት ከሚጠይቁት ነገሮች አንዱ የእናቶችን ሞት መቀነስ ሲሆን ለዚህ ከሚረዱት መካከል የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ማዳረስ አንዱ ነው፡፡ ሌላው የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚረዳው የሚሰጠውን የወሊድ አገልግሎት በማጠናከር ነው፡፡ ለዚህም ግብ መሰረታዊ የሆነ አፋጣኝ የማህጸን ሕክምናን ማስፋፋት አስፈላጊ ነው፡፡ለዚህም እንዲረዳ የህክምና መገልገያ አቅርቦትን ማሟላት የባለሙያዎችን  ችሎታን ማዳበር ስለሆነ በቀጣዮቹ ሁለት አመታት እስከ 2000/ሁለት ሺህ የሚደርሱ በስራራ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎችን የማሰልጠን እቅድ አለ፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን የአዋላጅ ነርሶችን ቁጥር መጨመር አንዱ እቅድ ሲሆን በቀጣዮቹ አምስት አመታት ወደ ስድስት ሺህ የሚደርሱ በማዋለድ ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራራት እቅድ }õ›M፡፡በቀጣዮቹ አመታት  በአንድ ጤና ጣቢያ ቢያንስ ሁለት አዋላጅ ነርሶች እንዲኖሩ ታቅዶአል፡፡ የረዥም ጊዜ እቅዱ እስኪተገበር ድረስ ባለው ጊዜ ችግሩን ለመፍታት የሚያስችለው እርምጃ በሌሎች አካላት የሚታገዘውና በኢሶግ ክኒካል ድጋፍ እየተደረገለት በመካሄድ ላይ ያለው የህክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን በጽንስና ማህጸን ህክምናው ዘርፍ አፋጣኝ የሆነ እና የተሟላ የህክምና እርዳታ እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡ ይህም በሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ከተቀመጡት አንዱ የሆነውን የእናቶችን ሞት የመቀነስ ተግባር ከታለመው ግብ ለማድረግ ያስችላል፡፡

 

Read 5316 times Last modified on Saturday, 23 July 2011 00:09