Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 06:52

ኖርዌይ በፍንዳታና በታጣቂ ጥቃት ተሸበረች

Written by 
Rate this item
(4 votes)

የመንግስት መስሪያቤቶች በበዙበትና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በሚገኝበት ህንፃ ትናንት ከሰአት በኋላ በተከሰተ ከፍተኛ ፍንዳታ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተሰጋ ሲሆን፤ ብዙም ሳይቆይ ጠ/ሚሩ ንግግር ያሰሙበታል ተብሎ ይጠበቅ በነበረ የፖለቲካ ፓርቲ ስብሰባ ላይ አንድ ታጣቂ በተኩስ እሩምታ በርካታ ወጣቶችን ገደለ፡፡

ፍንዳታውን ተከትሎ፤ የፖሊስ ልብስ ያደረገ ታጣቂ በከተማዋ ዳር በሚካሄደው የፖለቲካ ፓርቲ የወጣቶች ስብሰባ ላይ ጥቃት ማድረሱ ኖርዌይን እንዳሸበረ የአገሪቱ ብሄራዊ ፖሊስ ቃልአቀባይ ሲናገሩ፤ በፍንዳታው ስንጨነቅ እንደገና ይሄ ተጨመረበት ብለዋል፡፡
በዋና ከተማዋ ኦስሎ እምብርት ላይ በሚገኘው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ህንፃ አቅራቢያ የነበሩ ሰዎች፤ እዚያ በድንጋጤ እንደተረበሹ በሰጡት ምስክርነት በተከታታይ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታዎች አካባቢውን እንዳናወጡት ተናግረዋል - ድምፁ በመላ ከተማዋ ቢያስተጋባም፡፡ በፍንዳታው ከተጎዱት ህንፃዎችን መካከል አንዱ የሆነው የነዳጅ ሚኒስቴር መስሪያቤት በእሳት የተያያዘ ሲሆን፤ ከፍንዳታዎቹ የወጣው የጭስ ደመና በከተማዋ ላይ ሽቅብ ይታያል፡፡
በፍንዳታው ስንት ሰዎች እንደሞቱም ሆነ እንደተጎዱ በትክክል ለመናገር ገና መረጃ እንደሌላቸው የተናገሩት የፖሊስ ቃለአቀባይ፤ የፍንዳታው ምክንያትም ገና እየተመረመረ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በፍንዳታው ከተጎዱት በርካታ ሰዎች መካከል ሁለቱ የሞቱ ሲሆን፤ ዴይሊ ቴሌግራፍ ትናንት ምሽት ባሰራጨው ዘገባ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተው ይሆናል የሚል ስጋት እንደተፈጠረ ገልጿል፡፡ ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበው፤ ከዋናው የመንግስት መስሪያ ቤት ህንፃ አጠገብ፤ በፍንዳታ የተገለበጠች መኪና መኖሯና በአካባቢዋ ያሉ ግንባታዎች ክፉኛ መጎዳታቸው በግልፅ የሚታይ ሲሆን፤ ፍንዳታው በመኪና የተጠመደ የአሸባሪዎች ፈንጂ ሊሆን ይችላል የሚል መላምት አስነስቷል፡፡
የመንግስት መስሪያቤት ህንፃዎቹ ሁሉ በቁመት ጎልቶ በሚታየው ረዥም ህንፃ ውስጥ በ16ኛው ፎቅ ላይ የጠ/ሚ ቢሮ እንደሚገኝ የገለፀው ኒውዮርክ ታይምስ፤ ጉዳት እልደረሰባቸውም ብሏል፡፡ መስሪያቤቶቹ እንዲዘጉና ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ከተደረገ ሲሆን፤ አደጋው በጣም ከባድ እንደሆነ በመጥቀስ ቲቪ2 በተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ መግለጫ የሰጡት ጠ/ሚ ስቶልተነበርግ፤ ፍንዳታው የሽብር ጥቃት ነው ብሎ ለመናገር ገና በቂ መረጃ እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና የአገሪቱ የዜና ተቋማት እንደዘገቡት፤ የቴሌቪዥን ጣቢያውም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በፖሊስ ተዘግቶ ታሽጓል - አጠራጣሪ እሽግ ነገር ተገኝቷል በሚል፡፡
ከከተማዋ ዳር ሲካሄድ በነበረው የፖለቲካ ፓርቲ የወጣቶች ስብሰባ ላይ፤ ጠ/ሚሩ እንደሚገኙ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም፤ በስብሰባው ላይ አንድ ታጣቂ በተኩስ እሩምታ ጥቃት ሲፈፅም በቦታው አልነበሩም፡፡ የዜና ተቋማት እንደገለፁት ከሆነ፤ በጥቃቱ አምስት ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል፡፡

 

Read 5035 times Last modified on Friday, 05 August 2011 14:16