Sunday, 24 July 2011 07:27

ከመፃህፍት አለም..

Written by  ስብሃት ገ/ እግዚያብሔር.
Rate this item
(3 votes)

ደራሲ ፍለጋ የሚዋትቱ ገፀባህሪያት
የተከበራችሁ አንባቢያን :-
አንድ - የዛሬ ጽሑፋችን literature ማንበብ ለሚወዱ ሰዎች መደሰቻ (ምናልባትም መደነቅያ) ይሆናሉ ብ የምገምታቸውን ስራዎች ባጫጭሩ ይቃኛል፡፡
ኢጣልያዊው Luigi Pirandello (1867-1963) ሀያኛው ክፍለ ዘመን ካበቀላቸው Original (ፈር - ቀዳጅ) ደራስያን አንዱ ነው ይባላል፡፡

ከስራዎቹ ሁሉ ይበልጥ ዝነኛው Six Characters in Search of an Author የሚባለው ተውኔት ነው፡፡ አንድ የታወቀ ደራሲ ስድስት ገፀባህሪያት ያሉበት ተውኔት ግማሹን እንደፃፈ ይሞታል፡፡ እነዚህ ስድስቱ ገፀባህሪያት ..ደራሲው ምናብ ውስጥ እጣ - ፈንታችን ያቀደልንን ህይወት እስከ መጨረሻ መኖር አለብን፡፡.. ይባባላሉ ..ስለዚህ፣ የተፃፍነውን ግማሽ ኑሮ አንብቦ ሲያበቃ፣ የቀረውን ግማሽ ለመኖር እንችል ዘንድ እንዲጽፈው ያስፈልጋል..፡፡ ይህን ደራሲ ፍለጋ ስድስቱም በየፊናቸው በሮማ ጐዳናዎች ይዘዋወራሉ...
ፒራንዴሎ የፃፋት አጭር ልቦለድ The Sense of Service (የማገልገል መንፈስ) ትላለች፣ እቻትና ከነአራት ገፀባህሪãCê””
አንዲት የመካከለኛው መደብ ሴት ወይዘሮ በእድሜ እኩያው የሆነች ሰራተኛ አለቻት፡፡ ተመላላሽ፡፡ ሁለቱም የአራት አመት ሴት ልጆች አሉዋቸው፣ አብረው ሲጫወቱ የሚውሉ፡፡
አንድ ቀን የእመቤትዮዋ ልጅ አራተኛ አመትዋ ሲከበርላት ተውሏል፡፡ ሁለቱም አንድ አንድ አሻንጉሊት የልደት ስጦታ ተቀብለዋል፡፡
የእመቤትዋ ልጅ አልጋዋ ውስጥ ስትገባ፣ አሻንጉሊትዋን ..ነይ እንግዲህ እንተኛ፡፡ ትራስ ላንተርስሽና ተረት እነግርሻለሁ.. ስትላት፣ ሰራተኛዋ ልጅዋን ይዛ ወደ ቤትዋ ታዘግማለች፡፡
ሲበሉ ነው የዋሉት መቸስ፣ አልራባቸውም፡፡ ልጅዋ አሻንጉሊትዋን እንዲህ ትላታለች ..በግራሽ በኩል ልተኛ ወይስ በቀኝሽ? የቱ ይመችሻል? ነገ ልብስሽን አጥብልሽና ሽክ ብለሽ እኔንና እማዬን አስከትለሽ...
ሁለት
Elias Canetti (1905-19?) በጀርመንኛ የፃፈው ረዥም ልቦለድ Auto Dafe ይባላል (..ኑዛዜ..) ዋናው ገፀባህሪ አንድ አዛውንት የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ብቸኛ ሰው ስለሆኑ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ባለ አራት ፎቁ ቤተመፃሕፍት ውስጥ ነበር፡፡
አንድ ቀን፣ ቤተመፃሕፍቱ ሊዘጋ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው፣ ከየት እና በየት በኩል እንደመጣ የማይታወቅ እብደት ሰፈረባቸው፡፡
..ትቼው ከሄድኩ በኋላ ቤተመፃሕፍቱ ባዶውን በሆነበት ሰአት ቃጠሎ ቢነሳስ?.. የሚል ስጋት አስጨነቃቸው ..ያን የመሰለ የእውቀትና የጥበብ ክምችት!..
አስበው፣ አውጥተው አውርደው፣ ፕሮፌሰራችን ቤተመፃሕፍቱN አእምሮዋቸው (mind) ውስጥ ተሸክመው ወስደው፣ እቤታቸው ሊያሳድሩትና ጧት በመክፈቻው ሰአት አሁንም አእምሮዋቸው ውስጥ ተሸክመው ወደ ሁልጊዜ ቦታው ሊመልሱት...
ሶስት
እንግሊዙ Lewis Carroll (1832-98) ዋናዋ ገፀባህሪ የሰባት አመት ልጅ የሆነች ልቦለድ ፃፈ፡፡ እሱ የፃፈው ለልጆች ነበር፣ አዋቂዎችም ከልጆች እኩል የሉዊስ ካሮል ቲፎዞ (አድናቂ) ሆኑ፡፡
እቺን Alice in Wonderland (..አሊስ በተአምራት አገር..) የተባለችውን ድንቅ ልቦለድ ንግስት ቪክቶሪያ አነበቡዋት፡፡ ወድያው ቲፎዞ ሆኑና፣ የዚህ ደራሲ ስራዎች በሙሉ ነገ ጧት ከቁርሳቸው ጋር እንዲቀርቡላቸው አዘዙ፡፡
ነገ ጧት Professor Dodgson (የልቦለድ ብእር ስማቸው Lewis carroll የሆነ) የፃፍዋቸውን አምስት ቅጽ የሚሞሉ yMathematics መፃህፍት ለንግስቲቱ አበረከቱላቸው፡፡
አራት
እንግሊዙ Sir Arthur Conan Doyle (1859-1930) የህክምና ዲግሪውን ከጫነ በኋላ የግል ክሊኒክ ከፈተ፡፡ ገና ጀማሪ በመሆኑ፣ ስሙን እስኪተክል ድረስ ጥቂት ታካሚ ብቻ ስለሚመጣለት፣ በትርፍ ጊዜው አጫጭር ልቦለድ ለመፃፍ አቀደ፡፡ ኮናን ዶይል እጅግ የሚያስገርመው yMathematics እና የፍልስፍና መምህር ነበረ፡፡
መምህርና አስተሳሰቡ Sherlock Holmes ለሚባለው ዝነኛ የልቦለድ ገፀባህሪ ምንጭ (ወይም መሰረት) ሆነ፡፡ ሸርሎክ ሆምዝ ከጓደኛው ጋር ተዳብለው 221b Baker street ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ዶክተር Watson  Afghanistan በሀኪምነት ዘምቶ፣ ውጊያ ላይ እግሩ የቆሰለ (እና የጀግንነት ሊሻን የተሸለመ) በጣም ረጋ ያለ ሰው ነው፡፡
የለንደን ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት Scotland yard ይባላል፡፡ በዚያን ዘመን ከአለም ከተማዎች ሁሉ ትልቅ የነበረችው ለንደን አንድ ሚልዮን ህዝብ ይኖርባት ነበር፡፡ እዚህ ውስጥ ሸርሎክ ሆምዝ ብቸኛው (እና በአለም የመጀመሪያው) የግል ዲቴክቲቭ ነው፡፡ ሙያው ከስኮትላንድ ያርድ መርማሪ መኮንኖች ጋር ብዙ ጊዜ ያገናኘዋል፡፡
The strand የሚባል ወርሀዊ መጽሔት ነበረ፡፡ የሸርሎክ ሆምዝን አንድ ታሪክ እንደ ቋሚ አምድ ያስተናግዳል፡፡ ታሪኮቹን ሁሉ ሸርሎክ ሆምዝ ይሰራቸዋል፤ Watson ይጽፋቸዋል፡፡ የሸርሎክ ሆምዝ ቲፎዞዎች ከመብዛታቸው የተነሳ፣ Strand Magazine ለሽያጭ በሚወጣበት ሰአት የገዢው ሰልፍ መርዘሙና መጠማዘዙ ያስገርም ነበር፡፡  
አመቱ ሲያልቅ ደግሞ፣ የአስራ ሁለቱ ወራት ታሪኮች በአንድ መጽሐፍ ይታተሙ ነበር፡፡ በዚህ አኳኋን The Adventures of Sherlock holmes ...
እስከ አሁን እንግዲህ ዶክተር ኮናን ዶይል የታወቁ ሀኪም ሆነዋል፣ ለሸርሎክ ሆምዝ ጊዜ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል ሸርሎክ ሆምዝ አበቃ ብለው አስታወቁ፡፡
በነጋታው ጧት አዘጋጁ ራሱ ክሊኒካቸው ድረስ መጣ፡፡ ..እባክዎትን፣ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩትን የሸርሎክ ሆምዝ ቲፎዞዎች በድንገት ኩም አያድርጉብን፡፡ እርስዎ የፈለጉትን ያህል እንከፍላለን፡፡.. አላቸው፡፡
(..ምንም ቢጓጓ ሊከፍለኝ የማይችለውን ዋጋ ጠይቄው፣ በሱ እምቢታ ብገላገል አይሻለኝም?.. ብለው አሰቡ፡፡ ሰውን እምቢ ማለት የማይሆንላቸው፣ እንግሊዞች the perfect gentleman የሚሉዋቸው አይነት ሰው ናቸው)
..ለአንድ ታሪክ ሀያ አምስት pounds sterling ትከፍሉኛላችሁ?.. አሉ፡፡
ምንም ሳያንገራግር ..እንከፍላለን.. አላቸው፡፡ ተያዙ!
አስራ አንድ የሸርሎክ ሆምዝ ታሪኮች ፃፉ፡፡ አስራ ሁለተኛዋና የአመቱ የመጨረሻዋ ታሪክ ውስጥ ሸርሎክ ሆምዝን Professor Moriarty የሚባሉ የከረሩ ጋንግስተር ይገድሉታል፡፡ የታሪኩ ርእስ His last Bow (|lመጨረሻ ጊዜ እጅ ነስቶን መጋረጃው sþzU´)  
አቤት lSir Arthur Conan  Doyle የደረሱዋቸው መልእክቶች! የትዝብት፣ የንዴት፣ የሀዘን፣ እና ስድብ በየአይነቱ!
ከብዙ አመት በኋላ ሚስታቸው የሸርሎክ ሆምዝን ትንሳኤ በጣም በጣም እመኛለሁ አሉዋቸው፡፡ ደራሲው ..እንዴት እናስነሳቸው?.. ቢሉ፣ በጣም ተአማኒ የሚሆን ታሪክ ነገሩዋቸው፡፡
The Strand ውስጥ የሚስተናገደው ወርሀዊ አምድ የመጀመሪያ እትሙ The Return of Sherlock Holmes የሚል ታሪክ ነበር፡፡
አምስት
Jaroslav Hasek የሚባል የ Poland ተወላጅ The Good Soldier Schweik በሚል ርእስ Satirical novel ፃፈ፡፡ (..መልካሙ ወታደር ሽቬክ.. የሚል ምፀታዊ ልቦለድ)
ዘመኑ አንደኛው የአለም ጦርነት የተጧጧፈበት ወቅት ነው፡፡ በአንድ በኩል ራሽያ እና አንዳንድ ለሷ ታዛዥ የሆኑ ትናንሽ የምስራቅ ኤሮፓ አገሮች ተሰልፈዋል፤ ለረዥሙ ጦርነት፡፡ በሌላው በኩል ደግሞ ጀርመን እና ለእሱ ታዛዥ የሆኑ ሌሎች የምስራቅ ኤሮፓ አገሮች፡፡
የወታደር ሽቬክ አገር ፖላንድ ያን ጊዜ German Empire በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ትናንሽ አገሮች አንዷ ናት፡፡
በሰላም ጊዜ ሽቬክ ውሾች ገዢና ሻጭ ነበረ፡፡ የእለት እንጀራውን የሚያገኘው በሚከተለው ዘዴ ነበር፡፡ መጀመሪያ መጽሔቶች የሚሸጥበት ሱቅ ይገባል፡፡ ውሻ የጠፋባቸው ሀብታሞች ሰዎች የውሻውን ስምና መልክ እና ክብደት ዘርዝረው ..ይህን ውሻ በዚህ አድራሻ ለሚያመጣልኝ ሰው ወሮታውን እከፍላለሁ.. የሚሉበትን ገጽ ከፍቶ፣ ምን አይነት ውሻ የት እንደሚፈለግ ያጠናል፡፡ ለዚህ ጉዳይ ሁለት ወይ ሶስት ውሾች (የተፈለገው ክብደት ያላቸው) እየገመተ ለጥቂት ቀን ይከታተላቸዋል፡፡ ከዚያ መልካም ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት፣ ውሻውን (ዋን) ሰርቆ ወደ ቤቱ ይወስዳቸዋል፡፡ ፀጉራቸውን መሔቱ ላይ እንደተመለከተው አስመስሎ ይቀባቸዋል፡፡ ወድያውም የተፃፈለትን ስማቸውን ያስተምራቸዋል፡፡
በልዩ ልዩ ወራትና ቀናት አንዳንዱን ውሻ ለተለያዩ አምስት ስድስት ሰዎች ይሸጣል፡፡ ..እዚህ ከተማ የሚኖሩትን ውሾች አብዛኛዎቹን አውቃቸዋለሁ.. ይላል፡፡
ይህ የሰላም ጊዜ ኑሮ አልከፋውም፡፡ የሽቬክ ዋና ምኞትና ናፍቆት ግን በባቡር መጓዝ ነበር፡፡ ታድያ ገንዘብ ከየት ይምጣ? በዚያ በትልቁ የአለም ጦርነት የራሽያ ወገን እያሸነፈ መጥቷል፡፡ ስለዚህ ጀርመኖቹ ያለቀባቸውን ወታደር ለመተካት አሰሳ ሲደረግ፣ ሽቬክ በአፈሳ ተይዞ ወታደር ሆነ፡፡ የፖላንድን ድንበር አልፎ ሩቅ Hungary እሚሉት አገር እንዲሄድ የተወሰነ መሆኑን የሚገልጽ ትእዛዝ ደረሰው፡፡
እድሜ ለጀርመን ንጉሰ ነገስት፣ ወታደር ሽቬክ እንደልቡ በባቡር የመመላለስ እድል መጣለት! ማንም የጦር መኮንን ቢያነጋግረው፣ ሽቬክ “Permission to report, sir” ይላል፡፡
መናገር ሲፈቀድለት “I am a certified idiot” ብሎ ከኪሱ ሀኪም የፈረመበት የምስክር ወረቀት አውጥቶ ያሳያል፡፡ እውነትም ሰርቲፊኬቱ ..ይህ ሰው የመጨረሻ አእምሮ ዘገምተኛ መሆኑን እናረጋግጣለን.. ይላል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ታድያ፣ ይህ idiot ወታደር ለራሱ የሚበጀውን አነጣጥሮ ያውቃል፡፡ ወታደር ሽቬክ ብቻውን ሆኖ የጀርመን ንጉሰ ነገስትን ድል ያደርገዋል፡፡ ንጉሱ ስንቁንና የባቡር ጉዞ ገንዘቡን እየከፈለለት፣ ሽቬክ አምስት አመት ሙሉ በባቡር ተመላለሰ፡፡
በነፃ ነዋ ያውም!
ቸር ይግጠመን

 

Read 8278 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 08:33