የሶኖስ ሙዚቃ ማጫወቻዎች ያለ ገመድ በርቀት የሚገናኙበት ..ኔትዎርክ.. ያላቸው በመሆኑ ማንኛውም ቦታ ሰክተን ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሲዲ ሆነ አይፖድ ከማናቸውንም አይነት የሙዚቃ ማጫወቻዎች ጋር አገናኝተን መጠቀም የምንችል ሲሆን ሁሉንም ሲስተም ከርቀት ሆነን በገመድ አልባው መቆጣጠሪያ አማካኝነት ማዘዝ እንችላለን፡፡
በኢንተርኔት ከሚሰራጩ የሬድዮ ፕሮግራሞች ጋር አገናኝተንም ሙዚቃ ልንሰማበትና የራሳችንን የዘፈን ማጠራቀሚያ ላይብረሪም መፍጠር የምንችል ሲሆን ዋጋው 999 ዶላር (17,000 ብር ገደማ) እንደሆነ ታውቋል፡፡