Sunday, 31 July 2011 14:19

በFBI¸የሚፈለገው የዓለማችን ቁጥር አንድ ነውጠኛ

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(2 votes)

ሙሉ ስሙ ጀምስ ጄ በልገር ይባላል፡፡ ዕድሜው 81 ሲሆን፣ አይሪሽ አሜሪካዊ ነው፡፡ ትውልዱም በደቡብ ቦስተን በምትገኘው ሳዊዚ በምትባል ከተማ ውስጥ ነው፡፡ በተወለደበት ከተማ የአንድ ወንጀለኛ ቡድን ውስጥ በመታቀፍ አሀዱ ብሎ የተለያዩ ወንጀሎችን መስራት የጀመረው በልገር፤ ኋላ ላይ ..አይሪሽ ሞብ.. የተባለ የተደራጀ የወንጀል ቡድን ውስጥ መሪ ሆነ፡፡

አዛውንቱ በልገር ቁመናው እጅግ ያማረ እና የተለየ ግርማ ሞገስ እንዳለው ሲጠቀስ፣ ፀጉሩም ወርቃማ ቀለም ነው፡፡
ምንም እንኳን የወንጀለኞች መሪ ቢሆንም ለሚወዱት እጅግ ደግና አፍቃሪ እንደሆነም ይነገራል፡፡
በርካታ አድናቂዎችና አፍቃሪዎች ያሉት አዛውንቱ ወንጀለኛ ..ዊይቲ.. የሚል ቅጽል ስምም ቸረውታል፡፡ እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ በርካታ ወንጀሎችን የሠራ ሲሆን፣ በተለይም የአደንዛዥ ዕ ዝውውርን፣ በሕገወጥ መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ ኩባንያዎች ስሞቹን እየቀያየረ በማጭበርበር እና በ19 ሰዎች ግድያ በጥብቅ የሚፈለግ የዓለማችን አደገኛ ወንጀለኛ ነው፡፡
በልገር በርካታ ወንጀሎችን የሠራው በተወለደባት በሳውዚ ሲሆን፣ የአሜሪካ የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (FBI) እርሱን ለማግኘት ደቡብ ቦስተንና ሳዊዚን በሙሉ ማሰስ ጀመሩ፣ በፖሊስ እየታደነ መሆኑ የገባው በልገርም እ.ኤ.አ በ1995 ደቡብ ቦስተንን ለቆ ወጣ፡፡ ቦስተንን ለቆ ከወጣ በኋላ ዱካውን እየተከተሉ ሊያጠምዱት የሚሯሯጡትን የ FBI ፖሊሶች ለመሸሽ፣ ከአንዱ ስቴት ወደ ሌላ ስቴት ስሙንና አድራሻውን እየቀያየረ ማምለጥ ጀመረ፡፡ የ FBI ፖሊሶች መረጃ የመለዋወጥ ግንኙነታቸውን ሚስጢራዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቢያደርጉትም በልገርን በቀላሉ በእጃቸው ማስገባት አልሆነላቸውም፡፡
ይሁንና ጂን ክሎኒ የተባለ ስለ በልገር ለ FBI መረጃ ያቀብል የነበረ ግለሰብ፤ መልሶ በልገር ከ FBI ፖሊሶች እንዲያመልጥ መረጃ እንደሚሰጥ ደርሰውበት ወደ ዘብጥያ አውርደውታል፡፡
በተጨማሪም የ FBI ፖሊሶች የተለያዩ ወንጀሎችን የፈፀሙ የ..አይሪሽ ሞብ.. አባላትን በቁጥጥር ስር ማድረግ የቻሉ ሲሆን፣ በልገር ግን የውሃ ሽታ ሆኖባቸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከ60 ሺህ የሚበልጡ በጥብቅ የሚፈለጉ ወንጀለኞች ራሳቸውን ደብቀው እንደሚኖሩ የሚገልፀው ኢንተርፖል የተባለው ዓለም አቀፍ የፖሊስ አካል፣ ከ188 የኢንተርፖል አባል አገሮች ያጠናቀረው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ከእነዚህ ከሚታደኑ ወንጀለኞች መካከልም በጣም ጥቂት የሚባሉት በጣም በከፍተኛ ወንጀል የሚፈለጉ ሲሆን፣ በልገርም ከእነዚህ መካከል ይካተታል፡፡
የበልገር እስካሁን አለመያዝ ሲታይ እንደ ምሣሌ የሚጠቀሰው ..አትላንቲክ.. በተባለ የአሜሪካ መጽሔት፤ ቢን ላደን በአሜሪካዊያን ወታደሮች ከመገደሉ በፊት አሜሪካ የፓኪስታን መንግስት ቢን ላደንን መያዝ አለመቻሉን በተመለከተ ባቀረበችው ወቀሳ፣ ..የፓኪስታን መንግስት ኦሳማ ቢን ላደንን መያዝ ያልቻለው ልክ FBI በልገርን መያዝ እንዳልቻለው ነው.. በማልተ በአሜሪካ የፓኪስታን አምባሳደር ገልፀው ነበር፡፡
ይህም ውጤታማ ያልሆነ የበልገር አደን በሌላ አገር የተደበቁ ወንጀለኞችን አድኖ መያዝ ከባድ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም የ FBI የቦስተን ቅርንጫፍ በልገርን ለመያዝ ብቻ አንድ ግብረ ኃይል ቡድን አቋቁሞ ነበር፡፡ እስካሁን ድረስ ቡድኑ ከዩናይትድ ስቴትስ ጀምሮ በደቡብ አሜሪካና በኢሲያ ማደኑን ተያይዞታል፡፡ በቅርቡም ግብረ ኃይሉ በአውሮፓ ውስጥ የአደን መረቡን እንደሚዘረጋ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን በአውሮፓ የተደራጀ የፖሊስ ኃይል እያለም ወንጀለኞች ከተደራጀ የፖሊስ ተቋማት ተደብቀው ይኖራሉ፡፡ በመሆኑም አደኑ በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ይገለፃል፡፡
ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከፖሊሲ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ፣ ወንጀለኞች ለማደን አስገዳጅ ደንቦች ተግባራዊ እንዳይሆኑ አድርጓል፡፡ ይህም ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ ሊቃረን የሚችል ደንብ አውጥቶ ወንጀለኞችን መያዝ አለመቻሉ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር በልገር ይኖርበት ወደነበረው ደቡብ ቦስተን ሳውዚ ዛሬውኑ ቢሄድ ሊደበቅበት የሚችል በርካታ ቦታዎች አያጣም፡፡ የዶላር ሱቆች፣ የመጠጥ መደብሮች፣ ትላልቅ ሆቴሎች፣ የቁማር መጫወቻ ስፍራዎች እና የተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በአንዱ ሊሸሸግ ይችላል፡፡
እ.ኤ.አ በ1995 FBI በበልገር ላይ ያዘጋጀው የክስ ፋይል ብዛት ከ13ሺህ በላይ በሆኑ በተለያዩ ሰነዶች የተዘጋጀ ነበር፡፡ ክሱን ለማቅረብ እንዲረዳው በልገር ቦስተን ውስጥ ስላለው ሃብቶች መረጃ በመሰብሰብ ያውቁታል ተብሎ ከሚገመቱ ሰዎችም መረጃ በምስጢር አሰባስቦ ነበር፡፡ ታዲያ ምን ዋጋ አለው በልገር እንደሚፈለግ የ FBI መረጃ አቀባይ በሆነው በጂን ክሎኒ ቀድሞ መረጃ ደርሶት ስለነበረ ከሴት ጓደኛው ጋር ቦስተንን ተሰናብቶ ወጣ፡፡
በበልገር ጉዳይ ዙሪያ መረጃ የሚያጠናክሩ ቡድኖች፣ በዋነኛነት የአዳኝ ቡድኑ ግብረ ኃይል አባላትን በበልገር ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ሲፈልጉ፣ በቤተሰቦቻችን ላይ አደጋ ይደርስብናል በማለት ስማቸው እንዲገለጽ አይፈልጉም፡፡
በበልገር ላይ የተጠናቀረውን የክስ ፋይል ይዘት በዝርዝር ቢታወቅ፣ የግለሰቡን ገጽታን ለማስቀመጥና በአሁኑ ወቅት በምን ዓይነት ሁኔታ ተሸሽጐ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ማግኘት ያስችላል፡፡
አንዳንዶች ቢልገር ከማፊያም በላይ እንደሆነ ሲገልት፣ የእርሱ ሁለንተናዊ ጉዳይም በቀላሉ የማይታይና የተወሳሰበ ነው ይላሉ፡፡ በ2001 በማሳቹሴት ግዛት ውስጥ ለ18 ዓመታት የሴኔት አባል የሆነው ዊሊያም የተባለው የበልገር ወንድም ቦስተን ውስጥ ለፌዴራል አቃቤ ሕግ በሰጠው የምስክርነት ቃል፣ ከበልገር ጋር የመነጋገር አጋጣሚ ያገኘው አንድ ጊዜ መሆኑን እና ወቅቱም በልገር ራሱን ከሰወረበት ቀናት ብዙም ያልራቀ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡
ከስድስት ዓመት በኋላ የፌደራል አቃቤ ሕግ፣ ከበልገር ጋር በተያያዘ በወንድሙ በዊሊያም ላይ ምንም የወንጀል ምርመራ ላለማድረግ ውሳኔ ላይ ሊደርስ ቻለ፡፡ ሪቻርድ ቲሃን የተባሉ የበልገር ልዩ አዳኝ ግብረ ኃይል አስተባባሪ ሲናገሩ፣ ..በደቡብ ቦስተን ሳዊዚ  በልገርን በተመለከተ ሰዎችን ፈልጐ ለማነጋገር አዳጋች ነው፡፡ ምክንያቱም የፖለቲካ ገደብና የአካባቢው ነዋሪ ለበልገር ቤተሰብ ካለው ክብርና ታማኝነት የተነሳ ነው.. ይላሉ፡፡
ምንም እንኳን ግብረ ኃይሉ በደቡብ ቦስተን ሳዊዚ ጥቂት ሰዎችን የማነጋገር ዕድሉ ቢገጥመውም፣ ያገኘው መረጃ ቢኖር በልገር አሁን የሚገኘው አውሮፓ ውስጥ ነው የሚል ድፍን ያለ መረጃ ብቻ ነበር፡፡ ቀደም ሲል በበልገር ቡድን ውስጥ ተባባሪ የነበረ ግለሰብ ለ FBI ግብረ ኃይል በሰጠው ቃል፤ በቡድኑ ውስጥ መከፋፈል በተፈጠረ ጊዜ ከቡድኑ ራሱን ማግለሉን ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ በ1970ዎቹ ገደማ በልገር ሃሰተኛ ፓስፖርቶችን እንደሚሰበስብ እና በነዚህም የባንክ አካውንቶችን እና የከበሩ እቃዎችን ማስቀመጪያ ሳጥኖችን በአሜሪካ ከተሞችና በአውሮፓ ጭምር ለመክፈት መቻሉ ተረጋግጧል፡፡
የበልገርን ጉዳይ ከሚመረምሩት መካከል አንዱ፤ ..በልገር የተጠቀሱትን የማጭበርበርያ ዘዴዎች በተወሰነ ደረጃ ያውቃቸዋል፡፡ በተለይ የሰራውን የወንጀል ክብደት እያጤነ፣ ቀሪውን ህይወቱን ተሰውሮ ሊኖር እንደሚችል ያውቃል.. በማለት ገልጿል፡፡
የበልገር ወላጆች የአይሪሽ ስደተኞች በመሆናቸው በዚህ የተነሳ በልገር የአይሪሽ ፓስፖርት ባለቤት ለመሆን ችሏል፡፡ በመሆኑም በአይሪሽ ፓስፖርት እንደ ልቡ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ይችላል፡፡ በሌላም በኩል በአውሮፓ በ25 አገራት ባለው ስምምነት መሠረት ያለ ፓስፖርት ከአንዱ አገር ወደ ሌላው መጓጓዝ ይቻላል፡፡ ይህም በልገር ከአንዱ የአውሮፓ አገር ወደ ሌላው ዱካውን እያጠፋ እንዲኖር ያስችለዋል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1984 እስከ 1994 ድረስ ብቻ በርካታ ጊዜያት ወደ አውሮፓ መሄዱ ታውቋል፡፡ ወደ አውሮፓ ሲሄድ እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ካሽ ገንዘብ በቦርሳው ጭኖ እንደ¸NqúqSM የ FBI መረጃ ያስረዳል፡፡ በልገር ለመጨረሻ ጊዜ በአይን የታየው እ.ኤ.አ በ2002 በለንደን ሜሪዲያን ሆቴል ውስጥ በሚገኝ ጂምናዚየም ተቀጥሮ ሲሰራ እንደነበር አንድ የአይን እማኝ ለፖሊስ ተናግሯል፡፡
በልገር በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ እንዳለ ቢገመትም በመላው ዓለም በ FBI እየታደነ ይገኛል፡፡ ..ይሁንና በዚህ yGlÖÆላይz¤>NÂ የኢንተርኔት ዘመን ወንጀለኞች ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደ ልብ መንቀሳቀስ መቻላቸው በቀላሉ በፖሊስ እንዳይያዙ አድርጓቸዋል.. በማለት የኢንተርፖል ሴክሪተሪ ጀነራል ሮናልድ ኬ. ኖብል ይናገራሉ፡፡
ኬኖብል አያይዘውም፣ ..በተለያዩ አገራት ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ችግር መኖሩ ጉዳዩን የበለጠ አወሳስቦታል፡፡ በመሆኑም አለም አቀፍ ፖሊሶች ድንበር የሚሻገሩ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጋራ ተባብረው መስራት ይኖርባቸዋል.. በማለት ተናግረዋል፡፡
የ FBI ባለስልጣኖችም ቢሆን ወንጀለኞች ድንበር ከተሻገሩ በቀላሉ ሊገኙ አለመቻላቸውን ሲገል፤ ምክንያቱ ደግሞ በየአገሮቹ ያለው ሕግ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና FBI የአውሮፓ ፖሊሶች በልገርን በማደኑ ተግባር እንዲተባበሩት ጠይቋል፡፡
..በአውሮፓ እጅግ የተደራጁና ከተለያዩ አገራት የመጡ ወንጀለኞች ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓ ማህበር እነዚህን ወንጀለኞች አድነን እንድንይዝ ማዘዣ ሰጥቶናል፡፡ ይሁንና የምርመራና የፍለጋ ዘዴያችን እጅግ የላቀ መሆን አለበት.. በማለት የኢሮፖል (yxWéፖሊስ) ዳይሬክተር ሮብ ዋይን ራይት ይገልፃሉ፡፡ በአውሮፓ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የአንድ አገር ፖሊስ ተጠርጣሪው ወንጀለኛ የገኝበታል በተባለበት አገር ጋር ከሚገኙ ፖሊሶች ጋር ለተወሰነ ጊዜ ወንጀለኛውን አብረው እንዲፈልጉ የሚፈቅድ ሕግም በአውሮፓ ወጥቶ ነበር፡፡
ይሁንና ሁልጊዜ ቀና የሆነ የትብብር መንፈስ እንደማይታይ የኢሮፖል (የአውሮፓ ፖሊስ) ባለስልጣን ይናገራሉ፡፡ በተለይ ትብብር የተጠየቀው አገር ፖሊሶች ከማያውቋቸው የፖሊስ አካላት ጋር ተባብረው ለመስራት አለመፈለግና ችላ ባይነት መኖር ወንጀለኞች ተደብቀው እንዲኖሩ xSችላ*cêL”” በሌላም በኩል የአንዱ አገር ፖሊስ የሌላውን አገር ፖሊስ በጥርጣሬ የማየት ችግርም ሁኔታውን አወሳስቦታል፡፡ ነገር ግን ሁሉም አገራት ሊያውቁ የሚገባው ወንጀለኞች ወንጀለኝነታቸው ወንጀል በፈፀሙበት አገር ብቻ ሳይሆን በየሄዱበት አገር ተመሳሳይ ድርጊት የሚፈጽሙ መሆናቸው ነው በማለት ባለስልጣኑ ያስረዳሉ፡፡
FBI ከሶስት አስርት አመታት በላይ የሚፈልገውን ቀንደኛ ወንጀለኛ ለማግኘት ያልወጣው ዳገት ያልቧጠጠው አቀበት የለም፡፡ ነገር ግን አሁንም በልገር አልተገኘም፡፡ ..ለመሆኑ እርሶ በሚኖሩበት አካባቢ በልገርን አይተውታል?.. በማለትም  FBI ይጠይቃል፣ ምናልባት በልገርን ሰዎች ለይተው ሊጠቁሙ ይችላሉ ያለውን መረጃም ገልጿል፡፡ በልገር ውሻ ይወዳል፣ ምንም አይነት የክሬዲት ካርድ አይጠቀምም፡፡ የልብ በሽተኛ በመሆኑ መድሀኒት ይወስዳል፡፡ አነጋገሩ ጐርነን ያለ ሲሆን፣ የቦስተኖች ቅላ አለው፡፡ ሁልጊዜ ሰዎች ተሰባስበው ሲያወሩ የወሬው መሪ በልገር ነው፡፡ አንዳንዴ እያወራ እያለ ወሬውን ያቋርጣል፡፡
ውጫዊ ገጽታውን በተመለከተ FBI ሲገልጽ፣ አዘውትሮ ፀጉሩን ቀለም ይቀባል፣ ፂሙንም ሙልጭ አድርጐ ይላጫል፤ ..ፐርሰናሊቲውን.. ለመቀየርም ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ የሚያከናውን ነው፡፡ ልክ እንደ ወጣት በቡትስ ጫማው ውስጥ ረጅም ጩቤም ይሸጉጣል፡፡
FBI በጥብቅ ከሚፈልጋቸው 10 አደገኛ ወንጀለኞች ውስጥ በልገር እጅግ በጣም አደገኛው ነው፡፡ ..በበልገር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ቤተሰቦች ግለሰቡ ተይዞ ለፍርድ ሲቀርብ ማየት ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም በልገርን መያዝ ያበቃለት ነገር ሊሆን አይችልም.. በማለት የ FBI ከፍተኛ ባለስልጣን ይገልፃሉ፡፡
ዛሬ በደቡብ ቦስተን የአካባቢው ነዋሪዎች አዲስ እንግዳ ለሆነ ሰው ስለ በልገር ማንነት ለመናገር በጣም ይፈራሉ፡፡ አደጋ ይደርስብናል በሚል ፍራቻ፡፡ ነገር ግን በልገር በአሁኑ ወቅት እድሜው በጣም የገፋ በመሆኑና እንደ ወጣት እንደ ልቡ ተንቀሳቅሶ ለማምለጥና ለመሸሸግ የማይችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ አንድ ቀን በእጃችን ላይ ይወድቃል በማለት የ FBI ባለስልጣን ይናገራሉ፡፡

 

Read 6231 times