በዩኒቨርሳል ፒክቸርስ የተሠራው ..ካው ቦይ ኤንድ አልየንስ.. 36.4 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የሶኒ ፒክቸርስ ስራ የሆነው ..ዘ ስመርፍስ.. 36.2 ሚሊዮን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ አስመዝግበዋል፡፡ የሆሊዉድ ፊልሞች ገቢ ከሰሜን አሜሪካ ይልቅ በሌላው ዓለም ከፍተኛ ድርሻ ሊኖረው የቻለው y3D ፊልሞች ተቀባይነት በመጨመሩና ብራዚል፣ ቻይና እና ራሽያ አዳዲስ የገበያው መናሐሪያዎች በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ ዘንድሮ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ በዓለም ዙሪያ የሆሊውድ ፊልሞች የሰበሰቡት ገቢ ሁለት ጊዜ ሪከርድ መስበሩን የዘገበው ሮይተርስ ..ፓይሬትስ ኦፍ µÊbþÃN:- ስትሬንጅ ኦፍ ታይድስ..
በ260.4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሪከርድ ካስመዘገበ በኋላ የሃሪ ፖተር 8ኛና የመጨረሻ ፊልም ..ሃሪ ፖተር ኤንድ ዘ ዴዝሊ ሃሎውስ ክፍል 2.. በ314 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሪኮርዱን እንደሰበረው አመልክቷል፡