በሁለት ዓመት ውስጥ 10 ፊልሞች ለመስራት ያቀደው ፊፍቲ ሴንት፤ በቅርቡ ..ቲንግስ ፎል አፓርት.. የተሰኘ አዲስ ፊልሙን ለዕይታ ያበቃል፡፡ ራፐሩ በፊልም ኩባንያው አማካኝነት ከብሩስ ዊልስ፣ ዲኔሮና ከሌሎች ታላላቅ ተዋናዮች ጋር እየሠራ መሆኑን ዘ ፋይናንሻል ታይምስ አትቷል፡፡የ36 ዓመቱ ፊፍቲ ሴንት የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን ከ8 ዓመት በፊት ለገበያ ያበቃ ሲሆን እስካሁን ያወጣቸው አልበሞች ከ25 ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ በዓለም ዙሪያ ሸጧል፡፡